የሌለው መለስ vs. አርከበ – የኢንዱስትሪ ልማት ንድፈ-ሀሳብ ሙግት

(Name withheld upon request) በሀገራችን ውስጥ በአሁኑ ወቅት ከቀን ወደ ቀን በግልፅ በህወሓት አዛውንቶች እየተራመደ የሚስተዋለው የኒዮ-ሊበራል ዘውግ የሆነው የአመቻች መንግስት (facilitatory state) መርሆዎችን የተቀበለ የኢኮኖሚ ልማት በተለይ ደግሞ የኢንዱስትሪ ልማቱ አቅጣጫ፣ ላለፉት በርካታ ተከታታይ ዓመታት በሃገራችን ፈጣን እድገት በተግባር ሲያስመዘግብ ከነበረው የልማታዊ መንግስት (developmental state) ፓሊሲዎች ጋር ያለው መሠረታዊ የንድፈ-ሃሳብ ልዩነት ግር ብሎዎት ከሆነ […]

የምንዛሬ ተመን ማስተካከያና ያለንበት አዙሪት

መነሻ ብሔራዊ ባንክ የምንዛሬ ተመኑን በ15 በመቶ አወረደ ዳራ የአለም ባንክ ባለፈው አመት ሚያዝያ ላይ ተወዳዳሪነትን ለማሻሻል ኢትዮጵያ የምንዛሬ ተመኗን ማውረድ (devalue) ይኖርባታል በማለት መክሮ ነበር፡፡ እንደ አለም ባንክ እምነት ብር የነበረው ተመን (19.60) ከእውነተኛ ዋጋው/አቅሙ/ (over-valued) የተጋነነ ነው፡፡ በቀላል አማርኛ አንድ ዶላር ይዞ ለመጣ ሰው 19.60 ብር ብቻ መስጠት ተመጣጣኝ አይደለም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ […]

ለምን የቡና ዕረፍት አንለውም?

(ስንታየሁ ግርማ  – Sintayehu girma76 @gmail.com) የዕረፍት ሰዓታችን የሻይ ከሚባል የቡና ቢባል የተሻለ ነው፡፡ ምክንያቶቹም፡- 1. ለአለም ዲሞክራሲ እውቀት ፍልስፍና መስፋፋት ካደረገው አስተዋፅኦ አንፃር እ.ኤ.አ. በ1964 በአሜሪካ የላብአደሩ ተደራዳሪዎች “እርስዎ የቡና እረፍት ይስጡና የሚሠጡትን ሁሉ ያግኙ” በሚል መሪቃል ከባለሀብቱ ጋር እልህ አስጨራሽ ድርድር በማድረግ “የቡና ዕረፍት” ተግባራዊ ሆኖ የላብአደሩን አካላዊ እና አዕምሮአዊ ብቃት በቡና ዕረፍት ምክንያት […]

ከአዲሱ የቡና ግብይት ጥራትና ቁጥጥር አዋጅ ማሻሻያዎች በጥቂቱ

(ስንታየሁ ግርማ) የኢፌዴሪ መንግስት በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መጨረሻ ኢትዮጵያን በቡና ኤክስፖርት ከአለም ሁለተኛ ለማድረግ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ በ2017 ዓ.ም በዘመናዊ የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ልማትና ያደገ ኢኮኖሚ ከድህነት የተላቀቀ ህብረተሰብ ተፈጥሮ ማየትን ራዕዩ አድርጎ የሰነቀው የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለስልጣን በደንብ ቁጥር 364/2008 ተቋቁሞ ወደስራ ገብቷል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ በ2009 በጀት ዓመት በርካታ ተግባራትን […]

የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በ2009 ዓመት 1.5 ሚሊየን ባለጉዳዮችን አስተናገደ

(የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ – መግለጫ) ኤጀንሲው በ2009 በጀት ዓመት በጉዳይ 747,521 ጉዳዮችን ለማስተናገድ አቅዶ 720‚211 ጉዳዮችን አስተናግዷል፡፡ ይህም አፈጻጸሙ 96.35 ከመቶ ነው፡፡ በተገልጋይ 1,563,998 ባለጉዳዮችን ለማስተናገድ አቅዶ 1‚497‚772 ተገልጋዮችን አስተናግዷል፡፡ይህም አፈጻጸሙ 95.76 ከመቶ ነው፡፡ በተጨማሪም ኤጀንሲው ከአገልግሎትና ከቴምብር ቀረጥ ሽያጭ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብር 350 ሚሊዮን ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 322‚977.744.85 የሰበሰበ ሲሆን ይህም […]

በቡና ኤክስፖርት ሪከርድ ተመዘገበ

(ስንታየሁ ግርማ) ኢትዮጵያ 8.7 በመቶ እድገት በማስመዝገብ በአለም የመጀመሪያዋ ስትሆን ኡስቤኪስታን፣ ኔፓል፣ ህንድ፣ ታንዛኒያ፣ ጅቡቲ፣ ላኦስ፣ ካምቦዲያ፣ ማይኔማር እና ፊሊፒንስ 7.6%፣ 7.5%፣ 7.2%፣ 7.2%፣ 7%፣ 7%፣ 6.9%፣ 6.9%፣ 6.9 በመቶ በማስመዝገብ ከ2 እስከ 10 ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በአለም በፍጥነት በማደግ የመጀመሪያዋ ሃገር እንደሆነች ዐለም ባንክ አስታውቋል፡፡ ይህ አስደናቂ እድገትና ልማት የዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ትኩረት […]

በአማራ ክልል ባለፉት 26 ዓመታት በኃይል ልማቱ ዘርፍ በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል

(የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል – ሐምሌ 13/2009) በአማራ ክልል ባለፉት 26 ዓመታት እንደሌሎች የሃገሪቱ ክልሎች ሁሉ በኃይል ልማቱ ዘርፍ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ በዚህ ረገድ በተለይም ለኃይል ስርጭቱ ወሳኝ ሚና ያላቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞችና አካባቢዎች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለአብነትም ባለ 400 ኪ.ቮ አቅም ያላቸው የባህርዳር ሁለት እና ደብረማርቆስ፣ ባለ 230 ኪ.ቮ […]

ካፒታሊዝምን ጨርሰን ሳንገነባ ካፒታሊስቱ በዛ

(ይደነቅ ስሙ) ይህን አባባል በአንድ አጋጣሚ ከኔ በተሻለ እርከን የሚገኙና የማከብራቸው ሰው ሲናገሩት ውስጤን ቢኮረኩረው ርእስ አደረግሁት፡፡ ከዚህ አባባል ውጪ ያለው አስተሳሰብም ሆነ ትችት የግሌ ነውና የሀሳብ ባለቤትነት መብቴ ይጠበቅልኝ፡፡ ሀገራችን ባለፉት ኃያ ስድስት ዓመታት ራሱን በራሱ እያሳደገና ተፈጥሯዊ በሆነ ክስመት ወደ ተሻለ የማህበረሰብ እድገትና ርእዮተ ዓለም የሚያድግ አብዮት በመከተል እነሆ ከደረሰችበት ደርሳለች፡፡ ተበተነች ሲሉ […]

ከተስፋዉ በተቃራኒ ሰኬት እየናፈቀዉ የቀጠለዉ የቤቶች ግንባታ ፕሮግራም

(ኖህ ሙሴ) ባሳለፍናቸዉ አስራ ሁለት ዓመታት ስለኮንዶሚንየም ግንባታ ፕሮግራም ብዙ ከመባሉ የተነሳ ቃሉ ከህፃን እሰከ አዋቂዉ ከምሁሩ እሰከልተማረዉ ድረስ ከንግግሩ ያልተለየ ከሃሳቡ ጋር የተዋሃደ ሆኖ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም ሲነገርም ሆነ ሲታሰብ ከአንድ አቅጣጫ ብቻ አይደለም፡፡ ከጥሩም ከመጥፎዉም ጎኑ እንጂ፡፡ እሰቲ የፕሮግራሙ መልካምና መጥፎ ገፅታ አይተን የትኛዉ ገፅተዉ እንደሚያመዝንና በሂደትም ሊገጥመዉ የሚችለዉን አደጋ እንይና ከርእሱ ጋር እያስተያየን […]

የዴሞክራሲ አብዮትን “በኢኮኖሚ አብዮት” ማጨናገፍ አይቻልም!

ባለፈው ሳምንት “የኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት – በስህተት ላይ ስህተት በመድገም ስህተትን ማረም” በሚል ርዕስ አንድ ፅሁፍ አውጥቼ ነበር። በፅሁፉ ዙሪያ ከተሰጡኝ አስተያየቶች ውስጥ በአብዛኛው “ፅሁፉ የኢኮኖሚ አብዮቱን ዓላማና ግብ በትክክል አይገልፅም” የሚሉ ነበሩ። በመሆኑም ጉዳዩ በዝርዝር ለማብራራት እየተዘጋጀሁ ሳለ የአማራ ክልል ተመሣሣይ የኢኮኖሚ አብዮት ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን የሚገልፁ ዘገባዎች ወጡ። በዘገባው መሰረት የአማራ ክልል […]