በአማራ ክልል ባለፉት 26 ዓመታት በኃይል ልማቱ ዘርፍ በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል

(የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል – ሐምሌ 13/2009)

በአማራ ክልል ባለፉት 26 ዓመታት እንደሌሎች የሃገሪቱ ክልሎች ሁሉ በኃይል ልማቱ ዘርፍ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

በዚህ ረገድ በተለይም ለኃይል ስርጭቱ ወሳኝ ሚና ያላቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞችና አካባቢዎች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ለአብነትም ባለ 400 ኪ.ቮ አቅም ያላቸው የባህርዳር ሁለት እና ደብረማርቆስ፣ ባለ 230 ኪ.ቮ አቅም ያላቸው የንፋስ መውጫ፣ ሞጣ፣ መተማ፣ ጋሸና፣ አዘዞ፣ ደብረማርቆስ፣ ባህርዳር እና ኮምቦልቻ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡

በተጨማሪም ባለ 132 ኪ.ቮ አቅም ያላቸው የአከስታ፣አለም ከተማ፣ኮምቦልቻ አንድ፣ ሸዋሮቢት፣ ከሚሴ እና ደብረብርሃን እንዲሁም ባለ 66 ኪ.ቮ አቅም ያላቸው የቢቸና፣ ዳባት፣ ፍኖተ ሰላም፣ ዳንግላ፣ ወረታ፣ ጎንደር አንድ፣ ደሴ፣ ወልዲያ እና ሰቆጣ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ባለፉት 26 ዓመታት ተገንብተው ለክልሉ ህብረተሰብ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

Photo - 400 kv Debre Markos power transmission station
Photo – 400 kv Debre Markos power transmission station

በአጠቃላይ በአማራ ክልል ባለፉት 26 ዓመታት ከ25 በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች አዲስና ነባሮችም የአቅም ማሳደግ ሥራዎች ተከናውኖላቸው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል ቀደም ብለው የተገነቡ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችን አቅም ከማሳደግ አኳያም የጎንደር አዘዞ፣ የኮምቦልቻ እና የባህርዳር ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ በአሁኑ ወቅት የአቅም ማሳደግ ሥራዎች በመሰራት ላይ ሲሆኑ፣ በወልዲያ እና ቆቦ አዲስ ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች እንዲሁም በደብረብርሃን አንድ አዲስ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በመገንባት ላይ ነው፡፡

የክልሉን ከተሞችና ቀበሌዎች በጥቅሉ የክልሉን ህብረተሰቦች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያም በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በክልሉ የሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ደብረብርሃን፣ ደብረማርቆስ፣ ወልዲያ፣ ሰቆጣ፣ ከሚሴ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ሞጣን ጨምሮ ከ1600 በላይ ከተሞችንና የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

በቀጣይም ፍትሐዊ በሆነ መልኩ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን ለማሳደግ ብሎም የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥን በእጅጉ ለመቀነስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

*********

Guest Author

more recommended stories