የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በ2009 ዓመት 1.5 ሚሊየን ባለጉዳዮችን አስተናገደ

(የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ – መግለጫ)

ኤጀንሲው በ2009 በጀት ዓመት በጉዳይ 747,521 ጉዳዮችን ለማስተናገድ አቅዶ 720‚211 ጉዳዮችን አስተናግዷል፡፡ ይህም አፈጻጸሙ 96.35 ከመቶ ነው፡፡

በተገልጋይ 1,563,998 ባለጉዳዮችን ለማስተናገድ አቅዶ 1‚497‚772 ተገልጋዮችን አስተናግዷል፡፡ይህም አፈጻጸሙ 95.76 ከመቶ ነው፡፡

በተጨማሪም ኤጀንሲው ከአገልግሎትና ከቴምብር ቀረጥ ሽያጭ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብር 350 ሚሊዮን ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 322‚977.744.85 የሰበሰበ ሲሆን ይህም አፈጻጸሙ የእቅዱን 92 ከመቶ አከናውኗል፡፡

በወጪ በኩልም ብር 103.2 ሚሊዮን ወጪ ለማድረግ አቅዶ ብር 95‚097‚922.77 ወጪ አድርጓል፡፡ይህም አፈጻጸሙ 92.15 ከመቶ ነው፡፡

በተመሳሳይ ለመንግስት ፈሰስ ለማድረግ ብር 246.8 ሚሊዮን አቅዶ ክንውኑ ብር 227‚879‚817.08 ፈሰስ ተደርጓል፡፡ ይህም ከመቶ ሲሰላ የእቅዱን 92.3 ከመቶ አከናውኗል፡፡

የተጠናቀቀው የ2009 በጀት ዓመት ከባለፈው ከ2008 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በጉዳይ 81,497 በተገልጋይ 163‚443 እንዲሁም ከአገልግሎትና ከቴምብር ቀረጥ ሽያጭ ብር 48‚977‚748.85 እድገት አሳይቷል፡፡

Logo - Federal Document Registration and Authentication Agency

ለመንግስት ፈሰስ በማድረግ በኩልም ከ2008 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር ብር 30‚879‚817.08 እድገት አሳይቷል፡፡ ይህም ከአምናው ጋር ሲነጻጸር 16 ከመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡

ኤጀንሲዉ በጉዳይ በተገልጋይ፣ በገቢና ለመንግስት ፈሰስ በማድረግ በኩል የ2009 በጀት ዓመት ዕቅዱን ማሳካት የቻለው አገልግሎት አሰጣጡን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ እና አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ፤ የሰው ሃይሉን በስራ ላይ ስልጠና በመስጠት እንዲሁም የአሰራር ማንዋሉን ከወቅቱ ጋር እንዲሻሻል በማድረጉና በሁሉው ቅርንጫፎች ወጥ አሰራር እንዲሰፍን በመደረጉ ነው፡፡

በጥልቅ ተሃድሶ ውይይትም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት እቅድ አውጥቶ እና ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱ እንዲሁም የበላይ አመራሩ ክትትልና ድጋፍ ተጠናክሮ በመሰጠቱ ነው፡፡

ኤጀንሲው በቁልፍ ተግባራት ላይ ትኩረት በመስጠት፤የለውጥ መሳሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ የአመራሩና የሰራተኛው ተገልጋዩን የማገልገል ስሜት እየተጠናከረ መምጣት እና በቅርንጫፎች ጤናማ የስራ ውድድር መንፈስ እንዲሰፍን በማድረግ ለውጤቱ መገኘት አስተዋጽዎ አድርጓል፡፡

የተገልጋዩ በኤጀንሲው አገልግሎት የማግኘት ግንዛቤ ከፍ ማለት እና ተጨማሪ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች መከፈታቸዉም ለተቋሙ 2009 በጀት ዓመት ስኬታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበራቸው፡፡

ኤጀንሲው ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ የእዳና እገዳ የማጣራት አገልግሎት በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተግባራዊ መደረጉ የኢንተርኔት አገልግሎት /on-line service/ በመጠቀም ያለ ውጣ ውረድ የውክልና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችሉና በኤጀንሲው በተዘጋጁ ሞዴል ሰነዶች ካለምንም ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ አሠራር ዘርግቶ ተግባራዊ አድርጓል፡፡

ተቋሙ ለደንበኞች በድረ -ገጹ የተሟላ መረጃ በመስጠት፣ በ888 ነፃ የስልክ ጥሪ መረጃ እንዲያገኙ በማድረግ ፣ ፤ እንዲሁም በፌስ ቡክ መረጃዎችን በመለዋወጥ የተገልጋዮችን እርካታ ቀዳሚ ተግባሩ አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ተገልጋዮች ሟሟላት የሚገባቸውን ቅድመሁኔታዎች ሳያሟሉ በመቅረታቸው ጉዳያቸው ሳይፈጸም የቀሩትን ባላጉዳዮች ሳይጨምር በኤጀንሲው በቀን በአማካኝ በጉዳይ 2712 በተገልጋይ 5641 አገልግሎት እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በአገልግሎትና ቴምብር ቀረጥ ሺያጭ ብር 1‚216‚489 ገቢ ማደረጉ ታውቋል፡፡

**********

Guest Author

more recommended stories