ከአዲሱ የቡና ግብይት ጥራትና ቁጥጥር አዋጅ ማሻሻያዎች በጥቂቱ

(ስንታየሁ ግርማ) የኢፌዴሪ መንግስት በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መጨረሻ ኢትዮጵያን በቡና ኤክስፖርት ከአለም ሁለተኛ ለማድረግ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ በ2017 ዓ.ም በዘመናዊ የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ልማትና ያደገ ኢኮኖሚ ከድህነት የተላቀቀ ህብረተሰብ ተፈጥሮ ማየትን ራዕዩ አድርጎ የሰነቀው የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለስልጣን በደንብ ቁጥር 364/2008 ተቋቁሞ ወደስራ ገብቷል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ በ2009 በጀት ዓመት በርካታ ተግባራትን […]

አርሶ-አደርን ከመሬቱ ከማስነሳት ይልቅ ማጠጋጋት

ቀጥሎ የማነሳው ጉዳይ ከመሰረተ-ልማት ግንባታ ጋር በተያያዘ፣ በተለይ ከመሬት ይዞታቸው ለሚፈናቀሉ አርሶ-አደሮች የሚሰጠው የካሳ ክፍያ እና የመልሶ ማቋቋም መርሃ-ግብርን በተመለከተ ሲሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልልና የፌደራል መንግስት ሃላፊዎች ፅሁፉን በጥሞና እንዲያነቡትና አስቸኳይ የማስተካከያ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ከወዲሁ ለመጠቆም እወዳለሁ። ባለፉት ሁለት ወራት ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ተከታታይ የሆነ ተቃውሞ መከሰቱ ይታወቃል፡፡ መንግስት፣ በእንደዚህ ያሉ […]

የምግብ ዋስትና ፖለቲካ እና የኢትዮጵያ ሁኔታ

በብዙ ጉዳዮች የተቃዋሚው ጎራና የኢትዮጵያ ምሁራን ኋላ እንደሚቀሩ በግሌ ስገምት ነበር:: አንዱ ምክንያቴ የመንግስትና ህዝብ አስተዳደር ጉዳዮች በተለይም ህዝብ ከሚፈልጋቸው ፕሮግራሞችና ፅንሰ ሀሳቦች ጋር በቀጥታ ያለመገናኘታቸው ነው:: ሌላኛው ምክንያት የተቃዋሚው ጎራ እራሱን ከአዳዲስና አማራጭ የፖሊሲ ሀሳቦች ጋር ከማስተዋወቅ ይልቅ እንትን ይወድቅልኛል ብሎ የሚከተል አይነት በመሆኑ ነው:: ሀገር በብቃት ለመምራት የሀገሪቱን የተሳኩና ያልተሳኩ ትልሞችን፣ የፖሊሲና የህግ […]

ኃይለማርያም ደሳለኝ:- ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል ተቃርባለች

ኢትዮጵያ በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በአገር አቀፍ ደረጃ በምግብ ራሷን ለመቻል መቃረቧን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ስታዲዬም በተዘጋጀው 23ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል የማጠቃለያ ስነ-ስርዓት ላይ እንደተናገሩት ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮግራሞች ተግባራዊ በመደረጋቸው ስኬታማ መሆን ተችሏል። ከ3 አመታት በፊት የአፍሪካ […]

ከፊንጫኣና ከወንጂ-ሸዋ ፋብሪካዎች ተጨማሪ 1.8ሚ ኩ. ስኳር ምርት ይጠበቃል

*  የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ስራ የጀመረ ሲሆን፣ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በ2006 አጋማሽ ምርት ይጀምራል፡፡ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራው የተጠናቀቀው የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ ከጥቅምት 10/2006ዓ.ም ጀምሮ ተጨማሪ ምርት እያመረተ ነው፡፡ ፋብሪካው በ2006 በጀት ዓመት 2 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ያመርታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህ የምርት መጠን በ2005 በጀት ዓመት ከተገኘው ምርት ጋር ሲነጻጸር የ900 ሺህ ኩንታል ልዩነት ይኖረዋል፡፡ ፋብሪካው በሂደት […]

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ተጠናቀቀ

በዕለቱ በተያዙት አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይቶ በማፅደቅ ሥራውን የጀመረው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በገጠር የበጋ ሥራዎች አፈፃፀምና የመኽር ሥራ ዝግጅትን ከክልሎች በቀረቡት እና ከማዕከል በተካሄዱ የሱፐርቪቪን ሪፖርቶች ላይ ተመስርቶ ገምግሟል፡፡ በ9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ በአፅንኦት ተገምግሞ በየደረጃው የሚገኘው አመራር ሚናውን በተገቢው መንገድ በሚወጣበት እና የአርሶአደሩን ተሳትፎ ማዕከል ባደረገ አኳኋን በፍጥነት እንዲሻሻል አቅጣጫ የተቀመጠበት ዋነኛው ጉዳይ የግብርና ምርትና ምርታማነት […]

የመስኖ ግድቦች ግንባታ ክፉኛ ተጓትቷል

* በ2007 ዓ.ም የትልልቅ መስኖ ሽፋን ወደ683ሺ340 ሄክታር ለማድረስ ግብ ተጥሏል። * እስከአሁን በተከናወኑ ሥራዎች 220ሺ ሄክታር ለማልማት የሚያስችል አቅም ተፈጥሯል። (የማነ ገብረስላሴ) የአምስት ዓመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በተጀመረበት 2003 ዓ.ም የአገሪቱ የትልልቅ መስኖ ሽፋን ሁለት ነጥብ ሁለት በመቶ ነበር። በእቅዱ ዘመን መጨረሻ ማለትም በ2007 ዓ.ም ሽፋኑን ወደ 15ነጥብ4 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ ነው። ይህ ማለት በወቅቱ […]

የግብርና ምርት ዕድገት እንደዓምና «ወገቡን እንዳይዝ» እየተመከረ ነው

ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የሰብል ምርት ውስጥ ከ 30 እስከ 35 በመቶ የሚሆነው የሚመረተው በአማራ ክልል ነው ። በ2003 /2004 የምርት ዘመን በክልሉ 75 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት በ 2004/2005 የምርት ዘመን ለማሳካት የታሰበው 109 ሚሊዮን ኩንታል ቢሆንም የምርት መጠኑ ወደ 74 ነጥብ 96 ሚሊዮን ኩንታል ዝቅ ብሏል። በክልሉ […]

የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ተወሰነ

(በዘሪሁን ሙሉጌታ) ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ከቤንሻንጉል ክልል ተፈናቅለው በጎጃም ፍኖተሰላም አካባቢ እንዲሰፍሩ የተደረገው በስህተት መሆኑን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ። የተፈናቀሉት በሙሉ ቀደም ሲል ወደነበሩበት እንዲመለሱ መወሰኑንም አስታወቁ። የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አህመድ ናስር በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ሰሞኑን ከክልሉ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ የአማራ ተወላጆች በሙሉ እንዲመለሱ መወሰኑን ገልፀዋል። […]

የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ተመፅዋች ሆኑ

“ከእነ ቤተሠቤ እዚህ ለመድረስ ያየሁትን ፈተና ፈጣሪ ያውቀዋል፡፡ ቤተሰቤ ከቁጥር ሳይጐድል ለአገሬ መሬት በቅቻለሁና ከእንግዲህ የፈለገው ይሁን” አሉኝ፤ ከቤኒሻንጉል ክልል ያሶ ወረዳ ተፈናቅለው በፍኖተ ሰላም ድንጋያማ መጠለያ ውስጥ ያገኘኋቸው አዛውንት፡፡ በአማራ ክልል የከሠላ ወረዳ ተወላጅ የኾኑት አዛውንት፤ ኑሮ አልቃና ቢላቸው በ1997 ዓ.ም ሦስት ልጆቻቸውን ከትዳር አጋራቸው ጋር ይዘው፣የትውልድ ቀያቸውን ለቀው የተሻለ ሥራ ይገኝበታል ወደ ተባሉበት […]