በቡና ኤክስፖርት ሪከርድ ተመዘገበ

(ስንታየሁ ግርማ)

ኢትዮጵያ 8.7 በመቶ እድገት በማስመዝገብ በአለም የመጀመሪያዋ ስትሆን ኡስቤኪስታን፣ ኔፓል፣ ህንድ፣ ታንዛኒያ፣ ጅቡቲ፣ ላኦስ፣ ካምቦዲያ፣ ማይኔማር እና ፊሊፒንስ 7.6%፣ 7.5%፣ 7.2%፣ 7.2%፣ 7%፣ 7%፣ 6.9%፣ 6.9%፣ 6.9 በመቶ በማስመዝገብ ከ2 እስከ 10 ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በአለም በፍጥነት በማደግ የመጀመሪያዋ ሃገር እንደሆነች ዐለም ባንክ አስታውቋል፡፡ ይህ አስደናቂ እድገትና ልማት የዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ትኩረት እየሳበ ነው፡፡

በ2017 እ.ኤ.አ በአለም ከፍተኛ እድገት ከተመዘገበባቸው ውስጥ የቡና ኤክስፖርት ይገኝበታል፡፡ ሪከርድም ተሰብሯል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን መረጃ እንደሚያመለክተው በ2009 በጀት ዓመት 225493.5 ቶን ጥሬ ቡና ኤክስፖርት ተደርጎ 881.64 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ ከ2008 በጀት ዓመት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር በመጠን26992.5 (13.6%) እና በገቢ በ159.6 ሚሊዮን ዶላር (22.1%) ብልጫ ያለው በመሆኑ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡

የቡና ኤክስፖርት መዳረሻ 57 ሃገራት ሲሆኑ በመጠን እና በገቢ ደረጃ ከ1-3 ድርሻ ያላቸው አገራት፡-

ቁ. ሃገር መጠን በቶን ድርሻ በመቶኛ ገቢ በሚሊዮን ዶላር ድርሻ በመቶኛ
1 ጀርመን 40292.4 17.9 140 15.9%
2 ሳኡዲ አረቢያ 36551.31 16.2 132.91 15.1%
3 አሜሪካ 20297.42 9.2 116.71 13.2%

ጃፓን፣ ቤልጂየም፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ኢጣሊያ፣ ኢንግላንድ፣ ፈረንሳይ እና ሱዳን ከ4-10 ያለውን ደረጃ በቅደም ተከተል ይዘዋል፡፡ አስሩ ሃገራት በመጠን 86.07% እና በጊ 84.61% ሸፍነዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ኤክስፖርት ከተደረገው ቡና ውስጥ በቡና ዓይነት በምናይበት ጊዜ የሚከተለውን መረጃ እናገኛለን፡

1/ የታጠበ….84350 ቶን……68,221.22 (80.9%)

2/ ያልታጠበ….156650….157,102.4ቶን (100.3%)

3/ ስፔሻሊቲ ቡና

ቁ. የቡናው አይነት መጠን በቶን ገቢ በሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድርሻ

በመጠን

ድርሻ

በገቢ

1 ሲዳሞ 72,715.78 322.86 32.2% 36.6%
2 ለቀምቴ 61,105.21 170.49 27.1% 19.3%
3 ጅማ 40,720.84 103.47 18.1% 11.7%
4 ይርጋጨፌ 12,306.51 75.98 5.5% 8.6%
5 ሊሙ 11,364.24 58.58 5.0% 6.6%
6 ሐረር 11,102.84 64.08 4.9% 7.3%
ድምር 225,493.96 881.79

በአጠቃላይ ለኤክስፖርት ማደግ ዋና አስተዋፅኦ ካደረጉት መካከል የተጀመሩ የቡና ሪፎርም ስራዎች እና በአለም ገበያ እስከ ሶስተኛው ሩብ ዓመት የተሻለ የቡና ዋጋ ስለነበር ነው፡፡

ይሁንና የኢፌዴሪ መንግስት በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ኢትዮጵያን በቡና ኤክስፖርት ከአለም ሁለተኛ ለማድረግ በተያዘው የተለጠጠ እቅድ አንፃርና ካለን አቅም አንፃር የተጀመሩ አበረታች እንቅስቃሴዎች የበለጠ ተጠናክረው እና የተጀመረውን የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ትግል በሚቀጥለው ዓመት የበለጠ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

በበጀት ዓመቱ ከዘርፉ የሚታየውን የገነነ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ለመቀነስ በተደረገው ጅምር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ ቡና ዝውውር ንግድ ቁጥጥር በተደረገው ጥረት ህገ-ወጥ ቡና ተወርሶ ከተሸጠው 35 ሚሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል፡፡

*********

Guest Author

more recommended stories