Category Archives: History

ከኢትዮጵያዬ ወደ ኢትዮጵያችን

(ቴዎድሮስ ደረጄ (ዘበደሌ) ጠቅለል አድርጎ “የኢትዮጵያውያን እይታ” እያሉ ማተቱ ትንሽ ከባድ ቢሆንም ጎልተው በሚወጡ ነገራት ላይ ተነስቼ እይታዬን አቀርባለሁ ። በታሪክ ድርሳናት ኢትዮጵያ በውል መቼና እንዴት ተመሰረተች? ስሟስ እንዴት ኢትዮጵያ ተባለ? በሚለው ስምምነት ላይ ያልተደረሰ ቢሆንም እያንዳንዱ ኢትዮጵያ ከተመቸው የታሪክ ክምር እያፈሰ ኢትዮጵያዬ የሚለውን እየሳለ እዚህ ደርሷል። ይህ ኢትዮጵያችን ወደሚለው ከፍ ይል ዘንድ ግዜ እሚጠይቅ … Continue reading ከኢትዮጵያዬ ወደ ኢትዮጵያችን

የብሔር ፖለቲካ፣ የኢትዮጲያ ታሪክና የመሪዎቿ ተጠያቂነት

“በአንድ ሀገራዊ ጀግና ላይ እንኳን መግባባት ያቅተን?!” ይህ ባለፈው ሳምንት በአንዱ የፌስቡክ ገፅ ላይ ያነበብኩት ነው። በእርግጥ ፅሁፏ አንድ ዓ.ነገር ናት። በጥያቄው ውስጥ የታጨቀው ሃሳብ ግን የአንድ ክፍለ ዘመን ታሪክ ያህል ረጅምና ውስብስብ ነው። ጉዳዩ ከጄ/ል ጃጋማ ኬሎ ሞት ጋር ተያይዞ እንደተነሳ መገመት ይቻላል። በተለይ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በአንዱ ወገን በጄ/ል ጃጋማ ሞት የተሰማን ሀዘን … Continue reading የብሔር ፖለቲካ፣ የኢትዮጲያ ታሪክና የመሪዎቿ ተጠያቂነት

በመከላከያ ሰራዊታችን የፖርቲ ፖለቲካ ገለልተኝነትና ተያያዥ ጉዳዮች [ክፍል 2]

(ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሽፈራው) (የዚህን ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ) 9/ በሰራዊቱ ዉስጥ ገለልተኝነትን የሚሸረሽርና ለኢህአዴግ የወገነ አሰራር አልነበረም፡፡ የመከላከያ ሰራዊት ግንባታ ሰነዱ የሰራዊቱን ገለልተኝነት የሚሸረሽር ስለመሆኑ በሰራዊት ግንባታ ሰነዱ ላይ ዉይይት በተደረገባቸዉ ጊዜያትም ሆነ  ከዚያ  በኋላ በሰራዊቱ ዉስጥ አንድም ጊዜ ቅሬታ ሲቀርብ  አልሰማሁም፡፡ በሰራዊቱ ዉስጥ በነበርኩበት ወቅት በመመሪያዉ ላይም ሆነ በአፈጻጸም ረገድ … Continue reading በመከላከያ ሰራዊታችን የፖርቲ ፖለቲካ ገለልተኝነትና ተያያዥ ጉዳዮች [ክፍል 2]

አገራችን ኢትዮጵያ ያጠላባት አደጋና ስለ መውጫዋ አቅጣጫዎች

(በላይ ደርሸም) አጠቃላይ አገራችን ኢትዮጵያ ግዙፍ ፈተና ተደቅኖባታል፤ ዜጎችዋ ግዙፍ ፈተና ተደቅኖብናል፡፡ ከዚህ ፈተና ልንወጣ የምንችለው በራሳችን ጥረትና ብልህነት ብቻ ነው፡፡ እንባችንን ልናደርቅ የምንችለው እርስ በርሳችን ተመካክረን በምንደርስበት አግባቢ መንገድ ብቻ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ሁሉም በየራሱ ጉዳይ ተጠምዷል ወይም ቅድምያ የሚሰጣቸው ብሄራዊ ጥቅሞች አሉት፡፡ አጋር የሚባሉት ከጎናችን ይቆማሉ ወይም መፍትሄ እንዲመጣ ያደርጋሉ በሚል ተስፋና ስሌት … Continue reading አገራችን ኢትዮጵያ ያጠላባት አደጋና ስለ መውጫዋ አቅጣጫዎች

የህዳሴው ግድብ እና አለም አቀፍ ህግ

(በስንታየሁ ግርማ)  የአሜሪካው ሁቨር ግድብ እ.ኤ.አ በ1929 እና በ1930ዎቹ በአሜሪካ ተከስቶ የነበረው የኢኮኖሚ ድቀት ወቅት የተገነባ ግድብ ነው፡፡ ግድቡን ለመገንባት በ10000ዎች የሚቆጠሩ አሜሪካኖች የተሳተፉ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሰውተዋል፡፡ ግድቡ ለኔቨዳ ለአርዞንያ እና ለካርፎርኒያ ወዘተ ምእራብ ግዛቶች ዋነኛ የሀይል እና የብልፅግና ምንጭ ሲሆን በየዓመቱ በሚሊዬን የሚቆጠሩ ቱሪስቶች መናኽሪያ በመሆን በአሜሪካ ብልፅግናም ከፍተኛ አስተዋፆኦ አድርጓል፡፡ በተለይም … Continue reading የህዳሴው ግድብ እና አለም አቀፍ ህግ

ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች አሁንስ ምን ይሉ ነበር ይሆን?

(ሕሉፍ ሓጎስ [email protected]) መግቢያ ‹‹ታሪክን መማር ለሁሉ ሰው ይበጃል፤ ለቤተ መንግስት መኰንን ግን የግድ ያስፈለጋል››– ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ በመጀመርያ የነጋድራስ ገብረ ሕወይት ባይከዳኝን ሥራዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ጥረት ላደረጉ ለልጅ ልጃቸው ለወ/ሮ ዓይናለም አሸብር ገብረሕይወትና የሀገራችን ምሁራን በተለይም የታሪክ ምሁር ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ እና የስነ-ምጣኔ ምሁር ለኢኮኖሚስቱ ዶ/ር ዓለማየሁ ገዳ ታላቅ ምስጋናዮንና … Continue reading ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች አሁንስ ምን ይሉ ነበር ይሆን?

ኢህአዴግ ቀባሪ እንጂ መካሪ አይሻም

በዘንድሮው ዓመት በተለያዩ የሀገራችን አከባቢዎች የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር መከሰቱ ይታወቃል። የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ጥያቄዎቻቸውን አቅርበዋል። በዚህ አጋጣሚ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በዜጎች ላይ የአካል ጉዳት፣ የሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት ደርሷል። በመሆኑም፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚከተሉትን የመፍትሄ ሃሳቦች ተግባራዊ ማድረግ ያሻል፡፡ 1ኛ፡- ነፃ ምርጫ በማካሄድ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ማድረግ፣ … Continue reading ኢህአዴግ ቀባሪ እንጂ መካሪ አይሻም

ተራማጅ ህገ-መንግስት

(ስንታየሁ ግርማ ([email protected])) የኢፌዴሪ ህገመንግስት ተራማጅ ህገመንግስት ሊያስብሉት የሚችሉ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ይዟል፡፡ ከሌሎች የተለየ የራሡ ገፅታዎችም አሉት፡፡ ከህገመንግስት መግቢያ ስንጀምር እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች ሰለሚል የህገመንግስት ባለቤቶች ቤሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መሆናቸውን ያሣያል፡፡ ህገመንግስቱ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሃረሰቦች፣ ህዝቦች አንቀፅ በአንቀፅ የተወያዩበት እና ያፀደቁበት ስለሆነ ባለቤቶቹ እነሱ … Continue reading ተራማጅ ህገ-መንግስት

ወልቃይት እንኳን ህዝቡ መሬቱም ትግራዋይ ነው – ከታሪክ መዛግብት

(አስፋው ገዳሙ ([email protected])) 1/ መግቢያ የኢትዮጵያ ክልሎች አወቃቀር ሁሉንም ኢትዮጵያውያን አብረውና ተከባብረው እንዲኖሩ የሚያስችል ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር፡፡ በተለያዩ ወቅቶች ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ ገዢዎች ለህዝቡ ምቾት ሳይሆን ለራሳቸው በሚመች መልኩ ሃገሪቱን ሲስተዳድሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የአሁን መንግስትም ለራሱ በሚመቸው መልኩ እያስተዳደራት ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ብዙ ሰዎች፣ በተለይም የጎንደር ተወላጆች በደርግና በአጼ ሃይለስላሴ ወደ ነበረው አከላለል ካልተመለስን እያሉ … Continue reading ወልቃይት እንኳን ህዝቡ መሬቱም ትግራዋይ ነው – ከታሪክ መዛግብት

የጎንደሩ ዓመፅ ለምን ኣሁን ሆነ? ዋና ዋና መነሻ ምክንያቶች

በ”ጥያቄ ኣለኝ ጓዶች”(የብዕር ስም) በቅርብ ግዝያቶች በተለያዩ አከባቢዎች መልካቸዉና ይዘታቸው የተለያየ ዓመፆች እየታዩ ነው፤ ለግዜው ግን ትኩረቴ የጎንደሩ ላይ ነው። በጎንደርና ኣካባቢው የተነሳው ላይ ያተኮርኩበት ምክንያት ጎንደር የዚህ ሁሉ ማእከል ስለነበረችና ሌሎቹ በዋናነት የዚህ ተቀጥያ ስለነበር ምንጩን መረዳት ሌላዉን መረዳት ያስችላል ከሚል እሳቤ ተነስቼ ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከሌሎች ለየት ባለ መልኩ ዘር ተኮር ጥቃቶች … Continue reading የጎንደሩ ዓመፅ ለምን ኣሁን ሆነ? ዋና ዋና መነሻ ምክንያቶች