የስኳር ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ሽፈራው ጃርሶ ጋዜጣዊ መግለጫ (+Audio)

በእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ የሀገሪቷን ግዙፍ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም እና ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ የስኳር ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ጄኔራል ሚኒስተር ሽፈራው ጃርሶ ለጋዜጠኞች የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ (ኦዲዮ)፡፡ ለአድማጭ ያጥር እና ይመች ዘንድ የጥያቄዎቹን ዝርዝርና የአቶ ሽፈራው ጃርሶ መልስ የሚገኝበትን ደቂቃ ዘርዝረን አስፍረናል፡፡ [የመጀመሪያው 15 ደቂቃ የአቶ ሽፈራው ጃርሶ መክፈቻ ገለጻ ነው] ጥያቄዎች እና ምላሹ የሚገኝበት ደቂቃ […]

ሚኒስትር ሽፈራው:- በቅርቡ ለሚመረቀው ተንዳሆ ስኳር መዘግየት ህንዶችን ወቀሱ

በሚንስትር ማዕረግ የስኳር ኮሬፖሬሽን ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ሽፈራው ጃርሶ በግንባታ ላይ ያሉትን 10 የስኳር ፕሮጀክቶች ጎብኝተው ለተመለሱ ጋዜጠኞች ግንቦት 13 2006 በሰጡት ሰፊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከዳሰሷቸው ጉዳዮች አንዱ – ዘግይቶ እየተጠናቀቀ ያለው የተንዳሆ የስኳር ፕሮጀክት መዘግየት ላይ የሰጡት ማብራሪያ ነበር፡፡ ተንዳሆ ስኳር ፕሮጀክት ግንቦት 30 ይጠናቀቃል ያሉት አቶ ሽፈራው በፕሮጀክቱ ስለተሳተፉት የህንድ ድርጅቶችና የብድር […]

ከፊንጫኣና ከወንጂ-ሸዋ ፋብሪካዎች ተጨማሪ 1.8ሚ ኩ. ስኳር ምርት ይጠበቃል

*  የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ስራ የጀመረ ሲሆን፣ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በ2006 አጋማሽ ምርት ይጀምራል፡፡ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራው የተጠናቀቀው የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ ከጥቅምት 10/2006ዓ.ም ጀምሮ ተጨማሪ ምርት እያመረተ ነው፡፡ ፋብሪካው በ2006 በጀት ዓመት 2 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ያመርታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህ የምርት መጠን በ2005 በጀት ዓመት ከተገኘው ምርት ጋር ሲነጻጸር የ900 ሺህ ኩንታል ልዩነት ይኖረዋል፡፡ ፋብሪካው በሂደት […]

የማኅበረ-ቅዱሳን ሪፖርት| የዋልድባ ገዳምና የወልቃይት ስኳር ልማት ጉዳይ [Amharic]

መንግስት በትግራይ ክልል ወልቃይት ወረዳ የጀመረው የስኳር ልማት ፕሮጀክት በአካባቢው የሚገኘውን ጥንታዊው ዋልድባ ገዳም ላይ ጉዳት ያደርሳል በሚል ሲያወዛግብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ የተለያዩ አካላት መግለጫ የሰጡ ሲሆን፤ ባለፈው ሳምንት ደግሞ ማኅበረ-ቅዱሳን ሪፖርቱን አቅርቧል፡፡ ሪፖርቱ በዋልድባ ገዳም ሕልውና ላይ አደጋ እንደሌለ ቢያመለክትም በአቅራቢያው በሚገኙና ዝምድና ባላቸው ሦስት ቤተክርስቲያኖች በፕሮጀክቱ ሳቢያ እንደሚነሱ ይጠቁማል፡፡ መንግስት ጉዳዪን ያስተናገደበትን […]