Category Archives: Human Rights

የችግሩ መንስዔው ፍርሃት – መፍትሄው ነፃነት ነው

የውይይት መፅሔት አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ በኢትዮጲያ እየታየ ላለው ግጭትና አለመረጋጋት መፍትሄ ለማፍለቅ ሁላችንም ቅንነቱ ሊኖረን እንደሚገባ በመግለፅ የራሱን የመፍትሄ ሃሳብ አቅርቧል። በፍቃዱ የሚያቀርበው የመፍትሄ ሃሳብ “አሁን ሁሉንም ኃይልና እድል የተቆጣጠረው ሕወሓት/ኢህአዴግን” ነፃ የሚያወጣ ስለሆነ ፓርቲው ለዚህ ፍቃደኛ መሆን እንዳለበት ይገልፃል። በዚህ ረገድ ዋናው ነጥብ ለመፍትሄው ስለሚያስፈልገው ቅንነት ወይም የገዢው ፓርቲ ፍቃደኝነት አይደለም። ለቅንነትማ እንደ እሱና … Continue reading የችግሩ መንስዔው ፍርሃት – መፍትሄው ነፃነት ነው

ኢህአዴግን የማይቃወም የደርግ ደጋፊ ነው

በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የሕዝብ ተቃውሞና አመፅ እየታየ ነው። በሕዝቡ የተቃውሞ እንቅስቃሴ እና መንግስት እየወሰደ ካለው እርምጃ አንፃር የሀገሪቱ ምሁራን አቋምና ተግባር ምን መሆን አለበት? በዚህ ረገድ ምሁራኑ ሁለት አማራጮች አሏቸው። አንደኛ፡-የመንግስትን አቋምና እርምጃ በመደገፍ የህዝቡን እንቅስቃሴ ማውገዝ፣ ሁለተኛ፡-ከሕዝቡ ጋር በመሆን የመንግስትን አቋምና እርምጃ መቃወምና መተቸት። ነገር ግን፣ አብዛኞቹ የሀገራችን ምሁራን አንዱን ወገን በመደገፍ ወይም በመቃወም ሃሳብና … Continue reading ኢህአዴግን የማይቃወም የደርግ ደጋፊ ነው

ኢህአዴግ፡ አፍን ይዞ ከኋላ መጫን ለማፈንዳት

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተሰጡ ያሉ ሃሳቦችና አስተያየቶች በአብዛኛው በተቃራኒ ፅንፍ ላይ የቆሙና በጭፍን እሳቤዎች ላይ የተመሰረቱ ናቸው። አብዛኞቹ የግል/ውጪ ሚዲያዎች የመንግስትን አምባገነንነት ከመዘከርና በግጭቱ የተጎዱና የሞቱ ዜጎችን ቁጥር ከመቁጠር ባለፈ ሲዘግቡ አይስተዋልም። የመንግስት ሚዲያዎች ደግሞ በንብረትና በፀጥታ ኃይሎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በመዘገብና የችግሩን አስከፊነት በማጣጣል ላይ ተጠምደዋል። ሁሉም ክስተቶችን ከመዘገብና አንዱን ደግፎ ሌላውን ከማውገዝ በዘለለ … Continue reading ኢህአዴግ፡ አፍን ይዞ ከኋላ መጫን ለማፈንዳት

ከኢህአዴግ እና ከፌስቡክ ማን ያሸንፋል?

የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ አመራሮችና ደጋፊዎች፤ “ከኢህአዴግ በስተቀር ኢትዮጲያን ለመምራት የሚያስችል አቅም ያለው ፓርቲ የለም”፣ እንዲሁም “በፌስቡክ (Facebook) የመንግስት ስልጣን መያዝ አይቻልም” የሚሉ አስተያየቶችን በተደጋጋሚ ሲሰጡ ይሰማል። ለምሳሌ፣ “ኢትዮጲያ የማን ናት፡ የወጣቶች ወይስ የባለስልጣናት” በሚል ርዕስ ባወጣሁት ፅሁፍ ላይ ከተሰጡ አስተያየቶች አንዱ እንዲህ ይላል፤ “Except EPRDF nobody is qualified to lead Ethiopia at this time. So … Continue reading ከኢህአዴግ እና ከፌስቡክ ማን ያሸንፋል?

ህገ መንግስቱን የሚጻረረው የሠራዊት ግንባታ ሰነድ ከሥራ ይታገድ (ሜ/ጄነራል አበበ ተ/ሃይማኖት)

(አበበ ተክለሃይማኖት – ሜጀር ጄነራል) ግልፅ ደብዳቤ – ለክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጉዳዩ – “የሰራዊት ግንባታ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ” የሚለው መጽሐፍ ስለማገድ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር በተለያዩ ግዜያት ለመጠቆም እንደሞከርኩት፤ አንዳንድ ግዜ እንደተቋም ሌላ ግዜ በከፍተኛ መኮንኖች ፀረ ህገ-መንግስት የሆኑ ድርጊቶች እየተስተዋሉ ነው፡፡ የአገራችን መከላከያ ተቋም ሕገ-መንግስቱ እና ሕገ-መንግስቱን ብቻ መሰረት አድርጐ መንቀሳቀስ ሲገባው በግላጭ ሕገ-መንግስቱን የመጣስ … Continue reading ህገ መንግስቱን የሚጻረረው የሠራዊት ግንባታ ሰነድ ከሥራ ይታገድ (ሜ/ጄነራል አበበ ተ/ሃይማኖት)

የሀብታሙ አያሌው ጉዳይ፡- “ፈጣን ውሳኔ ባለመሰጠቱ የመዳን ተስፋው እየጨለመ ይገኛል”

(ማይክ መላከ) የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ሀብታሙ አያሌው ከሃኪም ቤት ከወጣ እነሆ ዛሬ 12ኛ ቀኑ ነው። በካዲስኮ ሆስፒታል አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ቢያገኘም ህመሙን ከማስታገስ በስተቀር ማዳን አልተቻለም። ብዙዎቻችን ኪንታሮት የተለመደና በቀላሉ የሚድን በሽታ መሆኑን እናውቃለን። ነገር ግን፣ የኪንታሮት ብሽታ አራት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን፣ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ያሉት በቀላሉ ግን በሀገር ውስጥ ህክምና የሚድኑ ናቸው። … Continue reading የሀብታሙ አያሌው ጉዳይ፡- “ፈጣን ውሳኔ ባለመሰጠቱ የመዳን ተስፋው እየጨለመ ይገኛል”

የሃገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦች (ሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ትንሳኤ)

(ሌተናል ጄኔራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ) መግቢያ ከሃያ አምስት ዓመት ኢህአዴግ የደርግን መንግስት በጦርነት አሸንፎ የሀገራችንን ፖለቲካዊ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ፤ ቀስ በቀስ እያደጉ የመጡ ፖለቲካዊ ችግሮች በግልፅ ጎልተው መታየት ጀምረዋል፡፡ አሁን ገዥው ፖርቲና ፖርቲው የሚመራው መንግስትም የችግሮቹን መኖር አምኖ ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ መንገር ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይህ ሁኔታ ለማንኛውም የሀገሩን ደህንነትና ሰላም፤ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ማህበራዊ ብልፅግና፤ … Continue reading የሃገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦች (ሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ትንሳኤ)

ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 4 – “እውነትን በጉልበት”

“ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ” በሚለው ተከታታይ ፅሁፍ፤ በክፍል-1 “የፀረ-ሽብር ሽብር” – ሽብርተኝነትን በፀረ-ሽብር ዘመቻና ጦርነት/ዘመቻ መግታት እንደማይቻል፤ በክፍል-2 “ፍርሃትን በፍርሃት” – በፍርሃት የሚወሰዱ አብዛኞቹ የፖለቲካና ወታደራዊ እርምጃዎች ስህተት እንደሆኑ፤ እንዲሁም በክፍል-3 “የአሸባሪዎች ሕግ” – የሽብር ጥቃት በደረሰ ማግስት የሚወጡ አዋጆችና መመሪያዎች የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሊገድቡ እንደሚችሉ ተመልክተናል። በመጨረሻው ክፍል-4 ደግሞ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በታሰሩ እስረኞች … Continue reading ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 4 – “እውነትን በጉልበት”

ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 3 – “የአሸባሪዎች ሕግ”

በዚህ “ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ” በሚለው ተከታታይ ፅሁፍ፤ በክፍል-1 “የፀረ-ሽብር ሽብር” – የሽብር ጥቃትን በፀረ-ሸብር ጦርነት/ዘመቻ መፍትሄ ለመስጠት መሞክር በተሳሳተ እሳቤ ላይ የተመሰረተ ስለመሆኑ ተመልክተናል። በክፍል-2 ደግሞ “ፍርሃትን በፍርሃት” በሚል ርዕስ የአሸባሪዎችን ጥቃት በፈጠረው ፍርሃትና ስጋት ውስጥ ሆኖ የሚወሰድ የፖለቲካና ወታደራዊ እርምጃ ውጤቱ ሌላ ተጨማሪ ፍርሃትና ስጋት እንደሆነ አይተናል። የዚህ ክፍል ዋና ትኩረት ደግሞ “የሕዝብን ሰላምና … Continue reading ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 3 – “የአሸባሪዎች ሕግ”

ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 2 – “ፍርሃትን በፍርሃት”

“ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ” በሚለው ተከታታይ ፅሁፍ በክፍል-1 “የፀረ-ሽብር ሽብር” በሚል ርዕስ በዓለም-አቀፉ የፀረ-ሽብር ጦርነት እና በደርግ የቀይ-ሽብር ዘመቻ መካከል ያለውን ተመሣሣይነት እና የተሳሳቱ እሳቤዎች ተመልክተናል። በአሸባሪዎች ለተፈፀመ “ወንጀል” ጦርነት ማወጅና ሽብርን በሌላ ሽብር ለመመከት መሞከር ፍፁም ስህተት ነው። ምክንያቱም፣ መንግስት “በፀረ-ሽብር” ስም የሚፈጥረው ሽብር የትኛውም የአሸባሪ ቡድን ሊያደርስ ከሚችለው በላይ የከፋ ነው። በእርግጥ አሜሪካኖች አንድ ግዜ … Continue reading ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 2 – “ፍርሃትን በፍርሃት”