የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ጎንደር ዘርን መሰረት ኣድርጎ ዜጎች ላይ ለደረሰው ጥቃት ለምን በይፋ ኣላወገዘም? ለምንስ በEBC ሊታይ ኣልተፈቀደም? የኢትዮጵያ መንግስት የትግራይ ህዝብ ለትውልዶች ከኖርበት የሰሜን ጎንደር ኣካባቢ በዘርኞች ሲጠቃ እና ሲፈናቀል ህዝቡን ለማገዝ ግዴታው እየተወጣ ነውን? ሕገ መንግስት በግላጭ ተጥሶ እንዲህ ኣይነት ከባድ ወንጀል በዜጎች ላይ ሲፈጸም ሽክሙ ለትግራይ ክልላዊ መንግስት ብቻ ለምን ተተወ? ለመሆኑ ይህ ሁሉ ውነጀል እየፈጸሙ እና እያስፈጸሙ ያሉትን በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ ኣመራሮች ተጠያቂ ለማድረግ እንዴት ኣልተቻለም?

የአማራ ክልል መንግስት በክልሉ በኣንድ ብሄር ላይ የተፈጸመውን ከባድ ጥቃት በይፋ ለማውግዝ ለምን ተሳነው? የአማራ ክልል መንግስት በኣንድ ብሄር ላይ የሚፈፀም ጥቃት እንዳለ ለምን እውቅና መስጠት ተሳነው? የአማራ ክልል መንግስት ፖሊስ ፣ምልሊሻ እና የኣካባቢውን መስተዳድሮች ወንጀል ሲፈጸም ለምን ተባባሪ ሆኑ? የአማራ ክልል መንግስት በህዳር ወር በሽንፋ እና ኣካባቢው ነዋሪ በሆኑት በትግራይ ተወላጆች ላይ በጠራራ ፀሃ የደረሰው ጥቃት ኣምኖ ሲያበቃ መፍትሄ ለመስጠት ለምን ኣልፈለገም?

መታወቅ ያለበት ጉዳይ

ይህ ኣሁን የተፈጠረው ሁኔታ በጊዚያዊነት በትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ቢሆንም ትምክህተኞች ድንበር ስለሌላቸው እነዚህ ኣስፋፊ የትምክህት ሃይሎች እድል ያገኙ ቀን በሌሎች ህዝቦችም እንደሚፈጽሙት ምንም ጥርጥር የለውም።

እዚህ ላይ ልብ ሊባልበት የሚገባ ነገር ቢኖር በኣንድ ብሄር ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት የሚያስተውሉ የሌላው ብሄር ተወላጆችም ነግ በኔ ብለው ሳይወዱ በኣማራ ህዝብ ላይ ከፍ ያለ ጥርጣሬ መፍጠሩ ኣይቀሬ ይሆናል። ይህ ተማምኖ እና ተቻችሎ ለመኖር ብሎም የጋራ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ምኞት ላላቸው ህዝቦች የማይበጅ ኣሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

በመሆኑም ሰፊው የኣማራ ህዝብ በውስጡ ያሉት ብስሙ የሚነግዱትን ዘረኞች እና ክድሮ ስርኣቶች የተራረፉትን ትምክህተኞች ለራሱ ሲል እና ለራሱ ሲል ብቻ ኣንቅሮ ሊተፋቸው ይገባል። ድሮ ብስሙ ሲነግዱ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሲያጣሉት ነበር ኣሁንም በውስጥና በውጭ ሆነው ከሌሎች ህዝቦች ጋር ሊናቁሩት ሌት ተቀን እየሰሩ ያሉትን የጥፋት ሃይሎች ከማንም በላይ ሊፋለማቸው ይገባል።

እነዚህ የጥፋት ሃይሎች ለኣማራው ህዝብ ደህንነት እና ነፃነት ኣስበው ኣያውቁም ለወደፊትም ኣይሳቡም። የሚያስቡ ቢሆን ኖሮ የህዝቡ ንብረት የሆኑት ውሃን ጨምሮ ሌሎች ብክልሉ የሚገኙትን የህዝብ ጠቋማት ኣይቃጥሉም ኣያፈርሱም ነበር፣ የኣማራው ህዝብ የሆኑ የግል መኪኖች ፣ ንብረቶች ወዘተ ባላፈረሱ ነበር። የኣማራ ተወላጅ የሆኑትን ባልገደሉ ነበር። ስለሆነም ከማንም በላይ በዘላቂነት የሚጎዱት የኣማራን ህዝብ ስለሆነ ህዝቡ ሊታገላቸው ይገባል እንላለን።

Photo - Tigrayans displaced from Metema-Yohanes town, North Gondar, in Gallabat, Sudan. Aug. 1, 2016
Photo – Tigrayans displaced from Metema-Yohanes town, North Gondar, in Gallabat, Sudan. Aug. 1, 2016

የክልሉ መንግስት ውድቀት

እዚህ ላይ መግለጽ የምንፈልገው በብኣዴን የሚመራው የክልሉ መንግስት ያኣማራውን ህዝብ እና ብክልሉ ነዋሪ የሆኑት የትግራይ ብሄር ተወላጆች ደህንነት ለማስጠበቅ ያደርገው ነገር የለም ብቻ ሳይሆ የክልሉ ምልሻ፣ ፖሊስ እና የኣንዳንድ ኣካባቢ መስተዳድሮች (በተለይም በጎንደ፣ ደባርቅ፣ ሰሜን ጎንደር እስከ መተማ) የችግሩ ተባባሪ ኣሊያም ቆሞ ተመልካች እንደነበሩ የጥቃቱ ሰለባዎች በበፊቱ ጥቃትም ኣሁንም ምስክርነታቸውን ሰጥቷል።

ይህ ብቻም ኣይደለም። የፌደራል የጸጥታ ሃይሎችም ወደ ክልሉ እንዳይገቡ ያለመፈለግ ሁኔታዎችም በተደጋጋሚ ተስተውሏል። ይህ ብስህተት ኣልነበረም፣ ሆን ተብሎ እንጂ። ለምሳሌ በመተማ እና ኣካባቢው የትግራይ ተወላጆችን ለማፈናቀል ስለተፈለገ ወደ ኣካባቢው ለመጡት የመከላከያ ሰራዊት ኣባላት በኣካባቢ ምንም ኣይነት የጸጥታ ችግር እንደሌለ ኣስመስለው የተሳሳተ መረጃ ሰጥተው በመመለስ የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ባሉበት ሁኔታ የህዝቡን ንብረት የመዝረፍ፣ የማቃጠል እና ዘርን እየመረጡ የማጥቃት ተግባር ተፈፅሟል።

ኣሳዛኙ ክህደት

በትግራይ ውስጥ ተወልዶ ለዚህ ደረጃ የደረሰው ብኣዴን ለትግራይ ህዝብ ያለው ምላሽ እንዲህ መሆኑ ለብዙዎች እጅግ ያሳዘነ ነው። ሰው በላው ስርኣትን ለመጣል በተደርገው የትንቅንቅ ትግል በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የትግራይ ልጆች በመላው የኣማራ ክልል ሲዋጉና ሲያዋጉ ድርብ ድርብርብ የሂወት መስዋእት ከፍሏል፣ የኣካል መጉደል ደርሶባቸውም ኣሁንም በስቃይ የሚኖሩ በኣሰርት ሺዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች ካለ ምንም ጥሮታ ይኖራሉ። የትግራይ ህዝብ ይህ በዋጋ የማይተመን መስዋእት በከፈለበት የኣማራ ክልል እንዲህ ኣይነት ኣጸያፊ ግፍ ሊደስበት ባልተጋብ ነበር።

እርግጥ ነው ብኣዴን ድርጅቱን ለመጥለፍ የበቃ የትምክህተኞች ኣንጃ በውስጡ መፈጠሩን ግልጽ ሆኗል። በመሆኑም ብኣዴን ውብ ታሪኩን ሳያበላሽ ጠልፈው ሊጥሉት የተቃረቡት የውስጥ ጠባብ ትምክህተኞች ሊያራግፍ የግድ ይለዋል። ድርጅቱን ተወልዶ እስኪያድግ ጉልህ ኣስተዋጽኦ ያደረጉት ኣሁንም ያልተንበረከኩት ኣንጋፋ ታጋዮች በሂወት እያሉ በወሳኝ የትግል ወቅት ድርጅቱን ከድተው በፈረጠጡት በእነ ያሬድ ጥበቡ የመሰሉ ከሃዲዎች እና ሌሎች የጥፋት ሃይሎች ትእዛዝ ሲቀበል ማየት እጅግ ኣሳዛኝ ነው።

ስለሆነም በብኣዴን ውስጥ ያሉት ኣንጋፋ እና የህዝብ ወገን የሆኑ ሌሎች ጓዶቻቸው ብኣዴን እየሄደበት ካላው የቁልቁል መንገድ ቢታደጉት ለሁሉም ይበጃል እንላለን። ይህ ካልሆነ ግን ’’ጨው ላራስህ ስትል ጣፍጥ ኣለበለዚያ ግን ድንጋይ ነው ብለው ይወረውሩሃል’’ ይሆናል ነገሩ።

መንግስት ማድረግ ያለበት

የኣማራ፣ የትግራይም ሆነ የሌላው ክልል ህዝቦች ከመልካም ኣስተዳደር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች እያነሱ እንዳሉ ግልጽ ነው። መንግስትም ያምናል። ኢህኣዴግ የህዝብ ጥያቄ በተፈለገው ፍጥነት ተገቢ ምላሽ መሰጠት ያለመቻሉ ህዝቡ ተስፋ እየቆረጠ ኣልቡልተኞችና ፀረ ህዝብ ሃይሎች ለሚነዙት የጥፋት ፕሮፓጋንዳ መጋለጡ ከግዜ ወደ ጊዜ ውዥምብር ውስጥ የሚገባ ሰው እየጨመረ እንደሆነ የማይካድ ሃቅ ነው። በሃገሪቱ በተለያዩ ኣካባቢዎች የሚታየው ህገወጥ ሰልፍ፣ ረብሻ እና ንብረት የማውደም ሁኔታ የዚህ መገለጫ ነው።

ስለሆነም መንግስት ከቃላት ባለፈ ውስጡን ኣስተካክሎ በየጊዜው እያደገ የሚሄድ ያለው ይህዝቦች ፍላጎት እና ጥያቄዎች በብቃት ለመመለስ ያሚያስችል ኣደረጃጀትና የኣገልጋይነት ስሜት የተላበሱ ቢሮክራቶች ማፍራት እና በየመዋቅሩ መመደብ ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ ነው። ሁሉም የኢህኣደግ ኣባል ድርጅቶችም በውስጣቸው ያለውን የበሰበሱትን የኣመራር ኣባላት ማስወገድ ይንሮባቸዋል።

ኪራይ ሰብሳቢዎች እና በየደረጃው የሚገኙ ብልሹ የኣመራር ኣባላትን የመጠየቅ ጉዳይ ወቅት ጠብቆ የሚመጣ ነገር ሳይሆን ቀጣይነት እና ግልጽነት ባለው ሁኔታ ተጠያቂ የሚሆኑበት ኣሰራር እንዳለ ልህዝቡ ብግልፅ ለማሳየት ቁርጠኝነቱን በተግባር ማስመስከር ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ግን ኣሁንም ’’ጨው ላራስህ ስትል ጣፍጥ ኣለበለዚያ ግን ድንጋይ ነው ብለው ይወረውሩሃል’’ የሚለውን የኣገራችን ኣባባል በኢህኣዴግም ይሰራል።

ጊዜ የማይሰጥ እርምጃ

ኣሁን የመንግስት ስልጣን እና የድርጀት ነፃነት ጭምብል ለብሶ በህዝቦች ላይ ዘምቶ ያለው የክልሉን መንግስት የተቆጣጠረው የጥፋት ሃይል መንጥሮ የማውጣት እና በህዝብ ፊት ማጋለጥ ብሎም ለጥፋቱ ተገቢ ፍርድ የመስጠት ስራ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል እንላለን። ብኣዴኖች ከዚህ ገዝግዞ ሊጥላቸው ከተቃረበው ጽንፈኛ እና ትምክሕተኛውን ሃይል ድርጅታቸውን የሚያድኑበት ዛሬ መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል። ይህ እርምጃ ካልተወሰደ በህዝቦች ላይ ገና ተጨማሪ ጥፋት እንደሚያደርስ ግልጽ ሊሆን ይገባል። ከኣሁን ቀደምም ብዙ ዜጎች ማስጠንቀቃቸውን ይታወሳል። ኣሁንም እንደዚሁ።

ወግድ ለዘረኞች እና ፀረ ህዝቦች!

********

ገብረ ሥላሴ ኣርኣያ ኣብ ሃገራዊን ዞባዊን ከምኡውን ዓለም ለኻዊ ፖለቲካ ጉዳያት ዝከታተል፣ ኣብዝኾነ ፖለቲካዊ ውዳበ ዘይነጥፍ ውልቀ ሰብ እዩ። ንሃናፃይ ሪኢቶ ኣብ [email protected]

more recommended stories