​ከኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

የድርጅታችን የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከታህሳስ 3 ቀን ጀምሮ ላለፉት 17 ቀናት አገራችን የምትገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ሰፊና ዝርዝር የሁኔታዎች ግምገማ አካሂዷል፡፡ ስራአስፈፃሚ ኮሚቴው በዚህ ስብሰባ ቀደም ሲል የተጀመረው የመታደስ ሂደትና የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁምበአገራችን የሚታዩ የቆዩና ወቅታዊ ችግሮችን ከነዝርዘር መገለጫቸው በመለየት በመንስኤና መፍትሄዎቻቸው ላይ መክሮ የሃሳብ አንድነትና መተማመን ፈጥሯል፡፡ […]

​የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አካሄደ

(አብዱረዛቅ ካፊ) ከታህሳስ15 እሰከ ዛሬ ታህሳስ 19/2010ዓ.ም የተለያዩ ርዕስ-ጉዳዮችን ሲገመገም የነበረውን የኢሶህዴፓ (የኢትዮጲያ-ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ) ማዕከላዊ ኮሚቴ  መደበኛ ስብሰባ ከሰዓት በኋላ ተጠናቀቀ። ስብሰባውን የመሩት የኢሶህዴፓ ሊቃመንበርና የክልሉ ም/ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ መሀመድ ኢሳቅና የኢሶህዴፓ ም/ሊቀመንበርና  የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ መሀሙድ ኡመር ሲሆኑ፤ በጉባኤው ላይ ከነበሩት አጀንዳዎች መካካል በ2010ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም በተላይ በውሃ፣ በእንስሳት መኖ፣ በግብርና፣ በትምህርትና […]

የኢትዮ-ሶማሌ የፓርቲና የክልል አመራሮች የተፈናቃዮች መልሶ ማቋቋም ውሳኔ አሳለፉ

(አብዱረዛቅ ካፊ) የኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሩና የክልሉ ካቢኔ አባላት የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመርና የኢ.ሶ. ህ.ዴ.ፓ ሊቃመንበር አቶ መሀመድ ረሺድ ኢሳቅን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ሶማሌና ከኦሮሚያ ክልሎች የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቄያቸው የሚመለሱ ውሳኔ አሳልፏል። ወሳኔው የተላለፈው ዛሬ ቅዳሜ ኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራርና የክልሉ ካቢኔ አባላት ዛሬ  ቅዳሜ ባካሄዱት […]

የህወሓት መግለጫ ጭማቂ – 8  ነጥቦች

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በመስከረም የመጨረሻ ሳምንት የጀመረውን ግምገማ ትላንት ጨርሷል። በተለይ ባለፉት አራት ሳምንታት የነበሩት ተከታታይ የሂስና ግለሂስ መድረኮች የድርጅቱን ሊቀመንበርና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን በመቀየር እንደተጠናቀቀ HornAffairs – English በተከታታይ ሲዘግብ ቆይቷል። የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት የግምገማውንና የአመራር ሽግሽጉን መጠናቀቅ አስመለክቶ ዛሬ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። 1) የአቋም መግለጫው የድርጅቱን ቁመና እንዲህ ሄሶታል:- “ካለፉት ጥቂት ኣመታት ወዲህ ስትራቴጂካዊ […]

የኢትዮጵያ ሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ለዞኖች ጋዜጠኞችና የቀረጻ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል

(አብዱረዛቅ ካፊ) የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ለክልሉ ዞኖችና ወረዳች የሚሰሩ ጋዜጠኞችና የካመራ ቀረጻ ባላሙያዎች በልማታዊ የሚዲያ አዘጋገብ፤ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለ3ቀናት ያህል ሲሰጥ የነበረውን የሙያ ሥነ-ምግባር አቅም ግንባታ ሥልጠና በዛሬ እለት በድርጅቱ የሥልጠናና አቅም ግንባታ አደራሽ አገባድዷል። በመዝግያ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝቶ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የመገናኛ ብዙሃን አጀንሲ ዋና […]

በአፍዴር ዞን፤ ራሶ ወረዳ የመልሶ ማቋቋም መጠሊያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ

(አብዱረዛቅ ካፊ) የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉና በራሶ ወረዳ የኢትዮጵያ ሶማሌ ወገኖች የምግብ፤ የመድሃኒትና የቤት ቁሳቁስ ድጋፍ ተሰጥቷል። በኢ.ሶ.ክ.መ. አፍዴር ዞን፤ ራሶ ወረዳ የመልሶ ማቋቋም መጠሊያ ጣቢያ የሚገኙና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮ- ሶማሌ ተወላጅ ወገኖች በዛሬ እለትበየክልሉ መንግስት የምግብ፤ መድሃኒት፤ አልባሳትና ለህፃናት የሚሆን አልሚ የምግብ አይነቶች ድጋፍ አደርጎላቿል:: በተያያዘም እርዳታው ያከፋፈሉት የክልሉ የገጠር […]

በአካባቢ ጥበቃና በአረንጓዴ ልማት ዙሪያ የሚመክር ጉባኤ በጅግጅጋ ተጀመረ

(በአብዱረዛቅ ካፊ) ማክሰኞ ጥቅምት 28/2010 ዓ.ም. በአካባቢ ጥበቃ፤ በአረንጓዴ ልማት ሥራዎችና እንድሁም በደን ጭፍጭፋ፤ በአፈር ማንሸራሸር፤ በህግ-ወጥ ፓርኮች ችግሮችን የሚቀረፍበትና በአጠቃላይ የተፈጥሮ ሀብት ልማት እቅዶች ለማሳካት የሚመክር የጋራ ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ በካሊ አደራሽ ተጀመሯል። ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የክልሉ የቀበሌዎች፤ወረዳዎች፤ የዞኖች፤ የከተማ መስተዳደሮችና የክልሉ ሴክተር መ/ቤቶች ሃላፊዎችና የካቢኔ አባላቱ በጋራ የሚሳተፉበት […]

​10ኛው የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ የጋራ ምክክር መድረክ በስኬት ተጠናቅቋል

(አብዱረዛቅ ካፊ) ላለፉት 5ቀናት ቀናት በጅግጅጋ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተውና የክልሉ ልማት፣ ሰላምና መልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር ታስቦ የተዘጋጀው የጋራ መድረክ ዛሬ በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ በካሊ አደራሽ በተዘጋጀው በዚሁ መድረክ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት የክልሉ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድና የኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሳዊ ፓርት (ኢሶህዴፓ) ሊቀመንበር እና የክልል ምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ […]

ፕ/ት አብዲ መሀሙድ – “ለሰላም ቅድሚያውን በመውሰድ እንሰራለን”

በአገር አቀፍ ደረጃ ለአሥረኛ ጊዜ የተከበረዉ የሠንደቅ አላማ ቀን አከባበር አስመልክቶ በኢትዮጲያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ ዋና ከተማ ጅግጅጋ ሰቴዲየም የክልሉ ርእሰ መሰተዳደርና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራር አካላት በተገኙበት ጥቅምት 6/2010 በደማቅ ሥነስርዓት ተከብሯል፡፡ በበዓሉ ሥነስርዓት ላይ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርእሰ መሰተዳደር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ሲሆኑ ትኩረት ሰጥተዉ የአስተላለፉት መልዕክት ሶስት መሰረታዊ […]

በም/ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል ቆለቺ ቀበሌ ተፈናቃዮችን ጎበኙ

(አብዱረዛቅ ካፊ) በቆለቺ ጉብኝት ያደረገው ከፍተኛ የመንግስት  ልዑካን  ቡድን በኢ.ፈ.ዴሪ. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ ሲሆን የኢሕአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና የኢ.ፈ.ዴ.ሪ የአደጋ መከላከልና ሥጋት ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች ይገኙበታል፡፡ በጉበኝታቸው ወቅትም በኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል ባቢሌ ወረዳ  ቆለቺ ቀበሌ ላይ በኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዚደንት አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመርን ጨምሮ […]