በም/ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል ቆለቺ ቀበሌ ተፈናቃዮችን ጎበኙ

(አብዱረዛቅ ካፊ)

በቆለቺ ጉብኝት ያደረገው ከፍተኛ የመንግስት  ልዑካን  ቡድን በኢ.ፈ.ዴሪ. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ ሲሆን የኢሕአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና የኢ.ፈ.ዴ.ሪ የአደጋ መከላከልና ሥጋት ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች ይገኙበታል፡፡

በጉበኝታቸው ወቅትም በኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል ባቢሌ ወረዳ  ቆለቺ ቀበሌ ላይ በኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዚደንት አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመርን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎችና የክልሉ ካቢኔ አባላት በደማቅ ሆኔታ አቀባበል አድርገውለታል፡፡

በም/ጠቅላይ ሚንስትር  የሚመራው የፈዴራል ልዑካን አላማ በቅርቡ በኢትዮጲያ ሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ ለተፈናቀሉና ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ኑሮ ሁኔታ ለማየትና በአከባቢው ለተፈጠረው ችግር ለመለየት ሲሆን የኢ.ፈ.ዴሪ. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንና የክልሉ ፕሬዝደንት አቶ አብድ መሀሙድ ከአካባቢው አገር ሽማግሌዎችና በቆለቺ ቀበሌ መልሶ ማቋቋም መጠለያ ጣቢያ የተደረገላቸው የኢትዮጰያ ሶማሌ ተፈናቃይ ወገኖች ጋር ውይይት አካሄዷል፡፡

 በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ አገር ሽማግሌዎችና የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በአገራችን ጠላት የአገራችን ሰላም የህግ የበላይነትንና እንዲሁም የፈዴራሊዝም ሥርዓታችን ለማደፍረስ ተብሎ የሚያቀጣጠሉ ግጭቶች ለማስወገድና ለችግሮቹ ዘላቂ መፍትሔ በሚሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቷል:: ከዚህ ጋር በተያያዘም የክልሉ አገር ሽማግሎዎች በክልሉ ህዝብ ላይ የሚደርሱ በደልና ችግሮችን አቀርቧል::

Photo - Deputy PM delegation visits Ethiopian-Somali displaced people in Kolechi kebele
Photo – Deputy PM delegation visits Ethiopian-Somali displaced people in Kolechi kebele
Photo - Deputy PM delegation visits Ethiopian-Somali displaced people in Kolechi kebele
Photo – Deputy PM delegation visits Ethiopian-Somali displaced people in Kolechi kebele

በሌላ በኩል የኢትዮጰያ ሶማሌ ተፈናቃይ ወገኖችና አገር ሽማግሌዎች የኢትዮጰያ ሶማሌ ህዝብ ሰላም ወዳድና ሌት ተቀን ህግን ለማስከበር የቆመ ማህበረሰብ መሆናቸው ጠቅሰው በተደጋጋሚ ለሚፈጠሩ ግጭቶች በፈዴራል መንግስት ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል::

በተመሳሳይም በመድረኩ ላይ የተገኙት የእምነት አባቶች የኢትዮጰያ ሶማሌ ክልል ህዝብ በቅርቡ የልማትና መልካም አስተዳደር ተጠቃሚ የሆኑና ለሀገሪቱ ህግና ደንቦች ታዛዥ  የመሆኑ ማህበረሰብ ከመሆናቸው ባሻገር የክልሉ ህዝብ በልማት ሥራዎች የሚሽቀዳደም እንጅ ለግጭቶችና ለችግር ትክረት የማይሰጥ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩሉ በሁለቱ ወንድማማች ክልሎች መካከል የተፈጠረው ደም አፍሳሽ ግጭት ዳግም እንዳይከሰትና በሁለቱም ወገኖች “የሚያጋጥሟቸው ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ፌዴራሉ መንግሥት በተለያዩ ምክክር መድረኮች በመፍጠርና ሁለቱን ህዝቦች የማስተሳሰር የመቀራረብና የማስታረቅ ሥራ እንደሚሰራ ገልፀዋል:: በንጹሃን ዜጎች ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀሙት ጥፋት አድራጊዎችም ፌዴራል መንግሥት ለህግ እንደሚያቀርብም አክሏል.

በተጨማሪም የኢህአዴግ ማዕከላዊ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በኢትዮጲያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት መንስኤ የሁሉቱ ህዝቦች አለመሆኑን ጠቁሟል:: ሆኖም ግን ጥፋት አድራግዎቹ የፌዴራሊዝም ስርዓታችን የሚጻረር ውጫዊ ጠላት ያቀነባበሩ በመሆኑና ሁለቱ የተጋጩ ህዝቦች ተመሳሳይ ባህል ሃይማኖትና ጋብቻን የሚተሳሰሩ እንድሁም ደም የሚጋሩ ወንድም እህታሞች መሆናቸውን ተናግሯል፡፡ በመቀጠልም ሁለቱ ህዝቦች በሰላም አብሮ የመኖር ባህልና የተሻለ ግንኙነት መመስረት የበለጸገች ኢትዮጲያን መፍጠር ያስፈልጋቿል ብሏል፡፡

በመጨረሻም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራው ልዑካን ቡድን ከጂግጂጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ አዲስ አበባ በሯል::

**************

Guest Author

more recommended stories