የኢትዮጵያ ሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ለዞኖች ጋዜጠኞችና የቀረጻ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል

(አብዱረዛቅ ካፊ)

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ለክልሉ ዞኖችና ወረዳች የሚሰሩ ጋዜጠኞችና የካመራ ቀረጻ ባላሙያዎች በልማታዊ የሚዲያ አዘጋገብ፤ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለ3ቀናት ያህል ሲሰጥ የነበረውን የሙያ ሥነ-ምግባር አቅም ግንባታ ሥልጠና በዛሬ እለት በድርጅቱ የሥልጠናና አቅም ግንባታ አደራሽ አገባድዷል።

በመዝግያ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝቶ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የመገናኛ ብዙሃን አጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያ አቶ ፈርሃን መሀሙድ አህመድ  “ለ3ቀናት ያህል በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች፤ በቀውስ ጊዜ የሚዲያ አሀጋገብና በአጠቃላይ አገራችን በሚትከተለው የልማታዊ ሚዲያ  ሥነ-ምግባር ዙሪያ በንቃት ሲከታተሉ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ትምህርት አላማን ወደ ከመጡበት ዞኖችና ወረዳዎች ሲመለሱ ተግባር ላይ እንድያደርጉ ጥሪያቸው አቀርቧል።

Photo - Ethio-Somali region mass media training
Photo – Ethio-Somali region mass media training

በተጨማሪም የክልሉ መገናኛ ብዙሃን አጀንሲ የዜናና ፖሮግራሞች ክፍል ዋና አርታኢ አቶ አብዲ ኡመር በበኩሉ ሰልጣኞችሁ የተማሩት ትምህርት ወደ ታችኛው ማህበረሰብ ሲወርዱ የሙያው ሥር-ምግባር እንድከተሉና አክሎም ለካመራ ቀረጻና ኤድትንግ ባላሙያዎች የሚዲያ ዋና አንቀሳቃሽ የሆነውን የሚዲያ መሳሪያዎችን በባላቤትነት ስሜት እንድጠበቁ አሳስቧል።

በሌላ በኩል የመገናኛ ብዙሃን ድርጅት ሰልጣኛቹ የሚዲያ ሥነ-ምግባር ትምህርቱ ለሥራቸውና ክህሎታቸውም በጣም ወሳኝ እንደነበረና ከዚህ የቀሰሙት የሚዲያ ትምህርትና  ሥነ-ምግባርም ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ከማረጋገጣቸው ባሻገር ለመገናኛ ብዙሃን አጀንሲ አሰልጣኞችና አመራሮችም አመስግኗል።

********

Guest Author

more recommended stories