በአፍዴር ዞን፤ ራሶ ወረዳ የመልሶ ማቋቋም መጠሊያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ

(አብዱረዛቅ ካፊ)

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉና በራሶ ወረዳ የኢትዮጵያ ሶማሌ ወገኖች የምግብ፤ የመድሃኒትና የቤት ቁሳቁስ ድጋፍ ተሰጥቷል።

በኢ.ሶ.ክ.መ. አፍዴር ዞን፤ ራሶ ወረዳ የመልሶ ማቋቋም መጠሊያ ጣቢያ የሚገኙና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮ- ሶማሌ ተወላጅ ወገኖች በዛሬ እለትበየክልሉ መንግስት የምግብ፤ መድሃኒት፤ አልባሳትና ለህፃናት የሚሆን አልሚ የምግብ አይነቶች ድጋፍ አደርጎላቿል::

በተያያዘም እርዳታው ያከፋፈሉት የክልሉ የገጠር መንገዶች ባላሥልጣን ም/ሃላፊ አቶ አብዱላሂ አብድ፤ የክልሉ ሲቪል ሴርቪስና የሥራ አመራር ኮሌጅ ዲን አቶ አብዱረሺድ ሼክ ኡመር፤ አፍዴር ዞን አስዳደርና የራሶ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ ሲሆን ለተፈናቃይ ወገኖቹ የተሰጦው እርዳታ ሩዝ፤ ስኳር፤ ቦረሽ፤ አተር፤ ዜይት፤ ስንዴና የህፃናት አልሚ ብስኩቶችና የቤት ማገልገያ ቁሳቁሶችና አልባሳትም ተካትቷል ብሏል አመራሩ።

Photo - Displaced people camp in Raso, Afder zone, Ethio-Somali region
Photo – Displaced people camp in Raso, Afder zone, Ethio-Somali region
Photo - Displaced people camp in Raso, Afder zone, Ethio-Somali region
Photo – Displaced people camp in Raso, Afder zone, Ethio-Somali region

በሌላ በኩል የክልሉ ሚዲያ ያነጋገሩትና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ ማህበረሰብ በኩላቸው የኢትዮጲያ ሶማሌ መንግስት በተከታታይ እያደረገለቸው ያለው ከፍተኛ ድጋፍ በጣም እንደተደሰቱበትና በኑሮኣቸውም ትልቅ ለውጥ እንዳመጣበትም አረጋግጧል።

በተጨማሪም የክልሉ መንግስት ላደረሱት ወገናዊ ድጋፍ የላቀ ምስገና ከማቅረባቸው ባሻገር፤ በተወለዱበትና ለረጅም አመታት የኖሩበት የአሮሚያ ክልል አከባቢዎች በህይወታቸው እንዲህ አይነት የማፈናቀል ችግር ይመጣቢናል ብለን አላሰብንም ብሏል።

በመጨረሻም የኢትዮጲያ ሶማሌመንግስትና የክልሉ ነዋሪዎች ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ ወገኖች በዘላቂነት ለመቋቋምና ሩሮኣቸው የተረጋጋ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል::

******

Guest Author

more recommended stories