በአካባቢ ጥበቃና በአረንጓዴ ልማት ዙሪያ የሚመክር ጉባኤ በጅግጅጋ ተጀመረ

(በአብዱረዛቅ ካፊ)

ማክሰኞ ጥቅምት 28/2010 ዓ.ም. በአካባቢ ጥበቃ፤ በአረንጓዴ ልማት ሥራዎችና እንድሁም በደን ጭፍጭፋ፤ በአፈር ማንሸራሸር፤ በህግ-ወጥ ፓርኮች ችግሮችን የሚቀረፍበትና በአጠቃላይ የተፈጥሮ ሀብት ልማት እቅዶች ለማሳካት የሚመክር የጋራ ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ በካሊ አደራሽ ተጀመሯል።

ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የክልሉ የቀበሌዎች፤ወረዳዎች፤ የዞኖች፤ የከተማ መስተዳደሮችና የክልሉ ሴክተር መ/ቤቶች ሃላፊዎችና የካቢኔ አባላቱ በጋራ የሚሳተፉበት ጉባኤ ሲሆን መድረኩ የመሩት የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር፤ የክልሉ ም/ት አፈ-ጉባኤና የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ. ሊቀመንበር አቶ መሀመድ ረሺድ እሳቅ  ናቸው።

Photo - Environment protection conference, Jigjiga
Photo – Environment protection conference, Jigjiga

በመድረኩ መክፈቻ ላይ የተናገሩት የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብድ መሀሙድ ኡመር የምክክር መድረኩ አጀንዳዎችን ካቀረቡ በኃላ፤ የጉባኤው ዋና አላማ በአካባቢ ጥበቃ፤ በአረንጓዴ ልማት ሥራዎችና እንድሁም በደን ጭፍጭፋ፤ በአፈር ማንሸራሸር ፤ በህግ-ወጥ ፓርኮች ችግሮች ላይ የሚያተኩር ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በአጠቃላይ የክልሉ ተፈጥሮ ሀብት ልማት ስተራቴጅዎችና እቅዶች በጥልቅ እንደሚገመገሙና ገንቢ የልማት ሃሳቦችን እንደሚያቀርቡም ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።

የክልሉ ቀበሌ አመራሮች በበኩላቸው የአከባቢ ጥበቃና የአረንጓ ልማት ሥራዎች ወሳኝ መሆናቸውና የደን ጭፍጭፋ፤ የአፈር ማንሸራሸር፤ የህግ-ወጥ ፓርኮች ችግሮችን የሚወግድበት ስተራቴጅዎች፤ ፖሊሲዎችና እቅዶችን በአግባቡ እንደሚያሳኩና ባሉበት ቀበሌዎች ላይ ተግባራዊ  እንደሚያደርጉም ተናግሯል። ጉባኤው ለቀጣይ ቀናት ይካሄዳል።

**************

Guest Author

more recommended stories