ፕ/ት አብዲ መሀሙድ – “ለሰላም ቅድሚያውን በመውሰድ እንሰራለን”

በአገር አቀፍ ደረጃ ለአሥረኛ ጊዜ የተከበረዉ የሠንደቅ አላማ ቀን አከባበር አስመልክቶ በኢትዮጲያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ ዋና ከተማ ጅግጅጋ ሰቴዲየም የክልሉ ርእሰ መሰተዳደርና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራር አካላት በተገኙበት ጥቅምት 6/2010 በደማቅ ሥነስርዓት ተከብሯል፡፡

በበዓሉ ሥነስርዓት ላይ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርእሰ መሰተዳደር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ሲሆኑ ትኩረት ሰጥተዉ የአስተላለፉት መልዕክት ሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ማለትም ስለ ሠንደቅ አላማ ታርካዊ አመጣጥና ትርጉም ምንነትና ጠቀሜታ፣ ስለ ሠላምና መልካም ጉርብትና እና ስለ አክራሪነትና ሽብርተኝነት የሚመለከት ነበረ፡፡

Photo - Ethio-Somali region President Abdi Omar, on Flag day, Oct 16, 2017, Jigjiga city

ሰለሆነም የኢትዮጲያ ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር በመክፈቻ ንግግሩ ላይ የአሰተላለፉት መልዕክት ስለ ሠላም ሰለ ኦሮሞና ሶማሌ ህዝቦች መልካም ጉርብትና፤ ወንድማማችነትና አንድነታቸዉ የማይነጣጠል መሆኑ፤ በግጭቱ ምክንያት በሁለቱ  ወንድማማች ህዝቦች ለይ የደረሰዉ ጉዳት የተሰማቸዉን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዉ ስለ ሰላም ያላቸዉ አቋምና ቁርጠኝነት በሚከተለዉ መልኩ ነዉ ያስተላለፉት፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ  ከምንም በላይ ሠላም አጥብቀን እንፈልጋለን፤ ፈጣሪ ሠላምና መረጋጋት እንዲያወርድልን እንለምናለን፡፡

በግጭቱ ምክንያት ከሁለቱም በኩል ህይወታቸዉ የአጡ ዜጎቻችን ፈጣሪ ምህረት እንድሰጣቸዉና ነብሳቸዉ ይማር በገነት ያኑረልን፤ የቆሰሉትም  ሙሉ ጤናቸዉ እንዲመልስላቸዉ በፈጣሪ ስም እንለምናለን፡፡

ግጭቱ ለአንዴና ለመጨረሻ በዚህ እንዲቆምና እንዲቋጭ ባለን ሙሉ  አቅምና ሀይልና ተጠቅመን የምንንቀሳቀስ ሲሆን፤ ፈጣሪም ጥረታችንና ልፋታችንን አይቶ ለሁለቱም ህዝቦች መካካል ሠላምና መረጋጋት እንዲያሰፍን እንለምናለን፡፡  

የሶማሌና ኦሮሞ ህዝቦች ወንድማማች ናቸዉ፡፡ ይህን ወንድማማችነትና መልካም ጉርብትናቸዉን ማጠናከር አለባቸዉ፡፡ በመካከላቸዉ ጥላቻና መጥፎ ስሜት እንዲኖር እንዲሁም ግጭቱን የሚያባብሱ አካላት ሁለቱም ህዝቦች በጋራ ሊታገሉ ይገባል፡፡

እኛ ጎረቤታሞችና ኩታገጠም ህዝቦች እንድሁም በጣም ረጅምና ሰፊ ድንበር የምንጋራ ህዝቦች ነን፡፡ጎረቤታሞችና በጣም ረጅምና ሠፊ ድንበር የሚጋሩና ኩታገጠም ህዝቦች ደግሞ የአንዱ ጉዳት ለሌላው ሰጋት ሲሆን የአንዱ ልማትም ለሌላው ተሰፋ ነዉ፡፡

የኦሮሞና ሶማሌ ህዝቦች አንድነት፤ ወንድማማችነት፤ ትስስርና የመደጋገፍ ባህር የማይነጣጠሉ ናቸዉ፡፡በኢኮኖሚ ረገድም በብዙ መልኩ በጣም የተሳሰሩ ናቸዉ፡፡ የኦሮሞና የሶማሌ ህዝቦች አንድነት፤ ወንድማማችነት ለመለያየትና ብሎም መልካም ጉርብትና ለማበላሸት የሚጥሩ አካላት በጣም ተሳስተዋል፡፡

ግጭቱን በዘላቂነት ለማስቆም ሁለቱም ህዝቦች ወደ ቀድሞ የተረጋጋና ሠላማዊ ኑሮዋቸዉ ለመመለስ ሁለቱ የክልል መንግሰታት ፀጥታ አካላት፣ የፌደራል መንግስት፣ መከላከያ ሠራዊት፣ ፌደራል ፖሊስና አገር ሸማግሎች እያደረጉት ላለዉ ጥረትና ርብርብ ከልብ እያመሰገንኩኝ፤

መላዉ የክልላችን ህዝብና ነዋሪዎች ይህን ተግባር በመደገፍና በመተባበር፣ ሠላምን ዋንኛዉ አጀንዳችን አድርገን በመዉሰድ፣ ሠላምን በማሰፈን ከኦሮሞ ወንድሞቻችን ጋር በሠላም አብሮ ለመኖር እኛ የኢትዮጲያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ ቅድምያ የሰላም አማራጩን በመቀበልና በመዉሰድ በመከባበርና በመቻቻል በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተና ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት አንድ የጋራ ኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ ያላት ኢትዮጵያ ለመገንባት ግንባር ቀደም ሚና እንወጣለን፡፡

*********

Guest Author

more recommended stories