Category Archives: interview

የጀርመን ሬድዮ ስለምርጫው ከሶስት ጋዜጠኞች ጋር ያደረገው ውይይት (+Audio)

የጀርመን ሬድዮ አማርኛ አገልግሎት አምስተኛውን ዙር የፌዴራልና የክልል ምርጫ በተመለከተ ከሶስት ጋዜጠኞች ውይይት አድርጎ ነበር። የራዲዮ ጣቢያው ጋዜጠኛ ሂሩት መለሰ፡- ከየማነ ናግሽ (ሪፖርተር ጋዜጣ)፣ ከ.ይልማ ኃ/ሚካኤል (የጀርመን ሬድዮ የበርሊን ወኪል) እና ከገበያው ንጉሴ(የጀርመን ሬድዮ የብራስልስ ዘጋቢ) ጋር፤ ስለቅድመ ምርጫውና ድምፅ የተሰጠበት ሂደትና ውጤቱ እንዲሁም የወደፊት ዕጣፈንታና የውጭ ኃይሎች ሚና አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ ከተነሱት መህል፡- … Continue reading የጀርመን ሬድዮ ስለምርጫው ከሶስት ጋዜጠኞች ጋር ያደረገው ውይይት (+Audio)

አባይ ፀሐዬ – ‘ልክ እናስገባችዋለን’ የተባለች ቃል ከየት እንደተወሰደች አላቃትም’ (ጽሑፍና ቪዲዮ)

ክቡር አቶ አባይ ፀሐዬ የህ.ወ.ሓ.ት/ኢህአዴግ መስራች አባል ታጋይና በአሁኑ ግዜ በሚኒስትር ማአርግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማእከል ዋና ዳይርክተር ናቸው፡፡ ከጋዜጠኛ ዘርአይ ሀ/ማርያም በኦህዴድ ታሪክና የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳዮች ቆይታ አድርገዋል፡፡ ሙሉ ቃለ-ምልልሱ ከዚህ በታች በጽሑፍ የቀረበ ሲሆን፤ ቪዲዮውን ደግሞ ከታች መመልከት ይችላሉ፡፡ —— ዘርአይ ኃ/ማርያም:- በትጥቅ ትግሉ ዘመን ኦህዴድ የኢህአዴግ አንድ አባል ድርጅት ሆኖ … Continue reading አባይ ፀሐዬ – ‘ልክ እናስገባችዋለን’ የተባለች ቃል ከየት እንደተወሰደች አላቃትም’ (ጽሑፍና ቪዲዮ)

በጦርነቱ ወቅት በመሣሪያ ግዥ ላይ የመለስ ዜናዊ ተቃውሞ አገር ለመጉዳት አልነበረም – ጄ/ል ጻድቃን [+video]

የቀድሞው ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት አፈጻፀም ሂደት ላይ የነበራቸው አቋም በወቅቱ ከነበረው የጋራ አመለካከት ሊከሰት የሚገባው ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው እንጂ አገር ለመጉዳት በማሰብ አይደለም በማለት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ገለጹት፡፡ ጄኔራሉ ይህንን የተናገሩት፤ በጦርነቱ ወቅት መለስ ለጦር መሣሪያ ግዥ በሚወጣው ገንዘብ መጠን ላይ ተቃውሞ ነበራቸው የሚለውን ስሞታ በመጥቀስ ላቀረብንላቸው በሰጡት ምላሽ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን ኤርትራ … Continue reading በጦርነቱ ወቅት በመሣሪያ ግዥ ላይ የመለስ ዜናዊ ተቃውሞ አገር ለመጉዳት አልነበረም – ጄ/ል ጻድቃን [+video]

ከቀድሞ ሠራዊት ‹‹ክሬም›› የሆነውን ክፍል እንዲቀጥል አድርገናል – ጄኔራል ጻድቃን [+Video]

የደርግ ሥርዐት መገርሰስን ተከትሎ የቀድሞው ሠራዊት እንዲበተን ቢደረግም 9,000 ገደማ ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የአዲሱ መከላከያ ሠራዊት አካል ሆነው እንዲቀጥሉ መደረጉን ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ አወሱ፡፡ ሰሞኑን ከሆርን አፌይርስ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ የቀድሞውን ሠራዊት የመበተን ውሳኔ ድህረ-ምክንያት (rationale)፤ ከአብዮታዊ ለውጥ ርዕዮተ-ዓለማዊ አመለካከት እና ከሠራዊቱ የደርግን ወንጀሎች ፈጻሚ የነበረ ከመሆኑ የመነጨ መሆኑን ጄኔራሉ አብራርተዋል፡፡ የቀድሞ ሠራዊት በመሰናበቱ የተጎዳ … Continue reading ከቀድሞ ሠራዊት ‹‹ክሬም›› የሆነውን ክፍል እንዲቀጥል አድርገናል – ጄኔራል ጻድቃን [+Video]

"ህወሓት ተተኪ የማፍራት ችግር አለበት" – አቦይ ስብሃት ነጋ

Highlights: * “አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ሕዝብ የሚሉ ሁሉ ህወሓትን ይጠሉታል።” * “ከአሜሪካንና ከእሥራኤል ጋር ያጣላን ፕሮግራማችን ነው።” * “ተወልደ የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር፤ ስዬም የመከላከያ ሚኒስትር እያሉ ኤርትራ ነፃነቷን ስታገኝ የአሰብ ጉዳይ ያለቀለት ጉዳይ ነው። ወንበር ፍለጋ ነው እንጂ የኤርትራ ጉዳይ ሰበብ ሊሆን አይችልም።” * “ህወሓት…… ለስድስት ወር ያህል ዝብርቅርቅ ያለ ፕሮግራም ተቀምጦ ነበር። … Continue reading "ህወሓት ተተኪ የማፍራት ችግር አለበት" – አቦይ ስብሃት ነጋ

ከገደብ በላይ ዕጩዎች ሲመዘገቡ – ባለፈው ምርጫና በዕጣ መሠረት ይለያሉ፡- የምርጫ ቦርድ ኃላፊ

(ምህረት ሞገስ) በመጪው ግንቦት 2007 ዓ.ም በሚካሄደው አምስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በአዲስ አበባ ብቻ 25 የፖለቲካ ፓርቲዎች 328 ዕጩ ተወዳዳሪዎችን አስመዝግበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ)፣ መላው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ንቅናቄ (መኢብን) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት)፣ የኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ) እና … Continue reading ከገደብ በላይ ዕጩዎች ሲመዘገቡ – ባለፈው ምርጫና በዕጣ መሠረት ይለያሉ፡- የምርጫ ቦርድ ኃላፊ

«የኢትዮጵያ ህዝብም ጠመንጃ የታጠቀ ጓደኛ ያገኘው በዚህ ትግል ነው»-ጄኔራል ሳሞራ የኑስ

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስር የምትታተመዋ ዘመን መፅሄት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስን እንግዳ አድርጋ ዘርዘር ያሉ መረጃዎችን ይዛ ወጥታለች። ከእነዚህ ነባርና አንጋፋ ታጋዮች መካከልም ጄኔራል ሳሞራ ለመጽሄትዋ ከሰጡት መረጃ የተወሰኑትን በመምረጥ እንዲህ አቅርበነዋል። ዘመን፡- እናመሰግናለን ጄኔራል ሳሞራ እንደሚታወቀው የህወሀት 40ኛ ዓመት መከበር ጀምሯል። እርስዎ ደግሞ በትግሉ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነዎትና እንደ ግለሰብ … Continue reading «የኢትዮጵያ ህዝብም ጠመንጃ የታጠቀ ጓደኛ ያገኘው በዚህ ትግል ነው»-ጄኔራል ሳሞራ የኑስ

ዶ/ር አሸብር – "ኢህአዴግ የምወዳደርበትን አካባቢ ቢተውልኝ የሚጐዳው ነገር አይኖርም"

የተከበሩ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በጥርስ ህክምናው ዘርፍ የተሠማሩ ባለሀብት ሲሆኑ በ2002 ምርጫ ተወዳድረው በማሸነፍ በፓርላማ ብቸኛ የግል እጩ ሆነዋል፡፡ ዶ/ር አሸብር በፓን አፍሪካ ፓርላማ ውስጥ በም/ፕሬዚዳንትነት እያገለገሉም ይገኛሉ፡፡ በግንቦቱ ምርጫ ዙሪያ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር የሚከተለውን ቆይታ አድርገዋል፡፡ አዲስ አድማስ:- በግንቦቱ ምርጫ በእጩነት ይወዳደራሉ? ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ:- በምርጫው ለመወዳደር ጓደኞቼ ፊርማ አሰባስበውልኝ ለቦርዱ አስገብተናል፡፡ ሙሉ … Continue reading ዶ/ር አሸብር – "ኢህአዴግ የምወዳደርበትን አካባቢ ቢተውልኝ የሚጐዳው ነገር አይኖርም"

በሽረ ጦርነት ዋዜማ ሻዕቢያ ተስፋ ቆርጦ ነበር – ጄኔራል ጻድቃን [+Video]

* የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ለሻዕቢያ አሉታዊ የሆነ አቋም ያለማቋረጥ ይይዙና ይወተውቱ ነበር * የህወሓት/ኢህአዴግ ሠራዊት አዲስ አበባ ሲገባ አብሮ የመጣው የሻዕቢያ ተዋጊ ብዛት 300 ገደማ ነበር በሕወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) የትግል ታሪክ እንደ ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጎ የሚወሰደው የ1981ዱ የሽረ ጦርነት ከመካሄዱ ጥቂት ወራት በፊት ሻዕቢያ በትጥቅ ትግሉ ስኬት ላይ ተስፋ አጥቶ እንደነበር ጄኔራል … Continue reading በሽረ ጦርነት ዋዜማ ሻዕቢያ ተስፋ ቆርጦ ነበር – ጄኔራል ጻድቃን [+Video]

[Video] ጄኔራል ጻድቃን – የዕርዳታ ገንዘብ ከሕዝብ ቀምተን ለመሣሪያ ስናውል አላውቅም

ከ1971 ጀምሮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት የህወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ‹‹እኔ የማውቀው ከደርግ ከሚገኘው ንብረት አብዛኛውን ከሕዝብ ስንካፈል እንጂ ከውጭ ለእርዳታ የመጣውን ገንዘብ ከሕዝብ ቀምተን ለጦር መሣሪያ ስናውል አይደለም›› አሉ፡፡ ጄኔራሉ ይህን ያሉት ባለፈው ሰኞ ጥር 30-2007 ባደረግንላቸው ቃለ-መጠይቅ ላይ፡- ለ1977ቱ ረሀብ የመጣው ዕርዳታ ለድርጅት ሥራ እንዲውል ተደርጓል ስለሚለው የዶ/ር አረጋዊ … Continue reading [Video] ጄኔራል ጻድቃን – የዕርዳታ ገንዘብ ከሕዝብ ቀምተን ለመሣሪያ ስናውል አላውቅም