“መብቱን የማይጠይቅ ተማሪ ለመፍጠር አይደለም የታገልነው” ፍቃዱ ተሰማ – የኦሮሚያና የኦህዴድ አመራር

ባለፉት ወራት በኦሮሚያ በተከሰተው ተቃውሞ የደረሰው ሰብዓዊ ጉዳት እየተጣራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ቢሮ ሀላፊና እና የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የፍቃዱ ተሰማ በተለይ ለHornAffairs ኦሮምኛ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ገለጹ፡፡

‹‹የሞቱትን፤ የቆሰሉትን፤ ሆስፒታል ከገቡ የሞቱትንም ሆነ በጥቅሉ የክልሉ መንግስት እያጣራ ይገኛል፡፡ ይሀ ተጣርቶ ሲያልቅ የክልሉ መንግስት አስፈላጊ በሆነ አካል የምንገልጽ ይሆናል›› ብለዋል አቶ ፍቃዱ፡፡

በቃለምልልሱ አቶ ፍቃዱ ‹‹የኦሮሞ ህዝብ…የዚህ ፌዴራሊዝም ግንድ ነው፡፡ እንዲሁም በፌዴራላዊ መንግስታችን ውስጥም የፌዴራሊዝሙ እምብርት የኦሮሞ ህዝብ ነው፡፡ ለራሱ አይደለም ለሌላውም ጥላ ነው፡፡›› ያሉ ሲሆን፤ የተለያዩ ወቅታዊና መሠረታዊ ጉዳዮችን ዳስሰዋል፡፡

ሙሉ ቃለ-መጠይቁ (ቪዲዮና ጽሑፍ) ሆርን አፌይርስ ኦሮምኛ ላይ የቀረበ ሲሆን፤ የአማርኛ ትርጉሙን እዚህ አቅርበናል፡፡

 

 

ሆርን አፌርስ፡- አቶ ፍቃዱ ተሰማ፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ እና የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ለቃለ-ምልልሱ ፍቃደኛ በመሆኖ አመሰግናለሁ:: የሰሞኑ ተቃውሞ የምን ተቃውሞ ነበር? ማንን የሚቃወም ነበር? ማስተር ፕላኑን ነበር የሚቃወሙት ወይስ? የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትን ነበር የሚቃወሙት ወይስ? የፌዴራሉን መንግስት ነበር የሚቃወሙት ወይስ? የአዲስ-አበባ ከተማ አስተዳደርን ነበር የሚቃወሙት ወይስ? አካባቢያቸው የሚያስተዳድረው አስተዳዳሪዎችን ነበር የሚቃወሙት ወይስ? ኦህዴድን እንደ ፖለቲካ ድርጅት ነበር የሚቃወሙት ወይስ? የፌዴራሊዝም ስርዓቱን ነበር የሚቃወሙት ወይስ? ማንን ነበር የሚቃወሙት? ምንን ነበር የሚቃወሙት? ይሀን በተመለከተ ምን ማወቅ እንችላለን?

አቶ ፍቃዱ ተሰማ:- እኔም አመሰግናለሁ:: ሆርን አፌርስ በኦሮሚያ ክልል ተከስቶ በነበሩ ጉዳዮችን በተመለከተ እንዲህ አይነት ፕሮግራም ማዘጋጀቱ ለተመልካቹም ሚዛናዊ እና ትክክለኛ መረጃ ለማቅረብ ያስችላል ብለን ስለምናስብ እኔም በጣም አመሰግናለሁ:: ሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል ተከስቶ የነበረውን ጉዳይ የምን ተቃውሞ ነው ብለን መውሰድ እንችላለን የሚለው ነገር ላይ ጉዳዩን በአትክክል ለመረዳት በሁለት ከፍሎ ማየት አስፈላጊ ነው::

ህዝባችን በአጠቃላይ በኦህዴድ/ኢህአዴግ ቆራጥ አመራር በመመራት በተለያዩ ሰርዓቶች ላይ የነበሩትን ጥያቄዎች ለመመለስ መራራ ትግል አካሄዷል:: በዚህ ትግል ውስጥም ብዙ የህይወት መሰዋዕትነትን ከፍሏል:: ከዚህ በመነሳትም የራሱን አዲስ ስርዓት ገንብቷል:: በዚህ በገነባው አዲስ ስርዓት ውስጥ የፖሎቲካ: የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መብቶች ጥያቄ በጥቅሉ ተመልሶለታል:: መልስ ብቻም ሳይሆን ሌላ ድል የሚመኝ ህዝብ: ተጫማሪ ልማት የሚጠይቅ ጠያቂ ህዝብ: ለመብቱ በዬትኛውም ወቅት የሚሞግት ህዝብ ያለበት ስርዓት ገንብቷል:: ለዚህም ነው ህዝባችን የፖሎቲካ መብቶች ድል አግኝቷል የምንለው:: ለረጅም ዓመታት ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ጥያቄ የነበረው ህዝባችን: ይሀው ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱ ከ100 ዓመታት በላይ በነፍጠኛ ስርዓት ተነፍጎ ሲጮቀን መቆየቱ ይታወቃል:: ከዚህ በመነሳትም አዲስ ስርዓት ገንብቷል:: የራሱን ክልል ከመመስረት ጀምሮ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ይገኛል:: ይህ ታሪክ ከ100 ዓመት ቡኃላ የተመለሰለት በመሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ከተቀዳጃቸው ትላልቅ ድሎች መካከል አንዱ ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል::

ሁለተኛ: በቀድሞ ሥርዐቶች ውስጥ ይጨቆን የነበረው ቋንቋውም በተለያዩ መንገዶች እንዲያድግ የመንግስት የስራ ቋንቋ: ህግ የሚፀድቅበት ቋንቋ: ህግ የሚተሮጎምብት ቋንቋ: ህግ የሚፈፀምበት ቋንቋ: ከክልሉ መንግስት የስራ ቋንቋነትም አልፎ በሚሊዬን የሚቆጠሩ (ከ8 ሚሊዬን በላይ) ብዙ የኦሮሞ ልጆች የሚማሩበት የትምህርት ቋንቋ: ብዙ መፅሓፍቶች የሚታተሙበት ቋንቋ: ከስርዓት ባለፈም የጥናትና የምርምር ቋንቋ: የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቋንቋ: የሚዲያ ቋንቋ መሆን ችሏል::

ባህሉንም ስናይ ከገዳ ስርዓት ጀምሮ ባለፉት ስርዓታት ውስጥ በደረሰበት ጭቆና ተቀብሮ የነበረው ወጥቶ እንዲበለፅግ፡ የኦሮሞ ልጆች የሚሸማቀቁበት ሳይሆን የሚኮሩበት፡ ኢሬቻ ብንል፤ ገዳ ብንል በይፋ ወጥቶ በአደባባይ የሚኮሩበት እንዲሆን ያስቻለ ስርዓት ነው፡፡ በጥቅሉ በማንነቱ የሚኮራ፤ በማንነቱ ላይ በራሱ የሚተማመን ህዝብ የፈጠረ ተደርጎ ይታያል፡፡ በኢኮኖሚም እንዲሁ ብዙ ድሎች መጥቷል፡፡ አረሶ-አደሩ የመሬት ባለቤት ብቻም ሳይሆን በመሬቱ አምርቶ የሚያገኝ፤ ማንም ሰባራ ሳንቲም የሚወስድበት ሳይሆን ለራሱ ስላመረተ ብቻ የሚሸለምበት (የሚበረታታበት)፤ የሚከብርበት፤ ያመረተዉንም ለራሱ የሚጠቀምበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

ሀገራችን ዕድገት ውስጥ ናት ሲባልም የኦሮሞ ህዝብና የኦሮሚያ ክልል ድርሻ ትልቅ ነው፡፡ ትምህርትን ስናይ በትምህርት ቤቶችና በሚማሩ ዜጎችም ስናይ በአጠቃላይ የሚሊዬኒየም ዴቬሎፕመንት ጎል (Millenium Development Goal) ማሳካት ላይም የኦሮሚያ ክልል ላቅ ያለሚና ያለው ሲሆን በሀገሪቱ ውስጥ ባለው ዕድገት ውስጥም ትልቅ ድርሻ እንዳለው ይታወቃል፡፡

ይህ ዕድገት በራሱ ጠያቂ የሆነ ህዝብ ፈጥሯል፡፡ የሚጠይቅ ህዝብ፤ አንድ ልማት ሲሰራ ተጨማሪ ልማት የሚጠይቅ፤ ማንነቱን በትክክል ያወቀ፤ መብቱ ምን እንደሆነ ያወቀ፤ ግዴታው ምን እንደሆነ ያወቀ ህዝብ ፈጥሯል፡፡ ሁሉም ነገር በሱ ተሳትፎ ብቻ ሊሆን የሚችል መሆኑን የሚያምን ህዝብ ነው፡፡ ከዚህም በመነሳት ይህን ድርጅት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት እንዲስፋፋ፤ እንዲያድግ ያደረገ፤ ድርጅቱ ድል እንዲያደርግ ያደረገ ይሀ ህዝብ ነው፡፡ መንግስትን ያቋቋመው በራሱ ድምፅ ነው፡፡ ከቀረበለት የተለያዩ የፖሊቲካ ምርጫዎች እነዚ የፖሊቲካ አማራጮች ሰላምን ሊያረጋግጡልኝ አይችሉም፤ እኩልነት ሊያመጡልኝ አይችሉም፤ ከብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋራ እንዲኖር አያስችሉኝም፤ ይሀ አማራጭ የጥፋት አማራጭ ነው፤ በጠባብ ብሔርተኝነትም ሆነ በትምክህታዊ ብሔርተኝነት የሚቀርቡትን አማራጮች የኦሮሞ ህዝብ በትክክል ስለሚያውቅ አማራጭ ሊሆኑ እንደማይችሉ በመረዳት ባለፉት 25ዓመታት ድምፅ የነፈጋቸው እሱ (ህዝቡ) ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በድምፁ ነው ይህን መንግስት የመሰረተው፡፡ በድምፁ ነው ይህን ፌዴራሊዝም የገነባው፡፡ ከመነሻው የዚህ ፌዴራሊዝም ግንድ ነው፡፡ እንዲሁም በፌዴራላዊ መንግስታችን ውስጥም የፌዴራሊዝሙ እምብርት የኦሮሞ ህዝብ ነው፡፡ ለራሱ አይደለም ለሌላውም ጥላ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት የራሱን መንግስት የሚቃወምበት ምክንያት፤ የራሱን ድርጅት የሚቃወምበት ምክንያት፤ የፌዴራሉን መንግስት የሚቃወምበት ምክንያት፤ የሚጠረጥርበት ምክንያት አንድም ቀን ተፈጥሮ አያውቅም፡፡

ይሁንና ከዚህ በፊት እንደገለፅኩት ዕድገት በፈጠረው ሂደት ለራሱ ዕድገት እንቅፋት የሆኑት የመልካም እስተዳደር ጉዳዮች ሰፊ እነደሆኑ ባለፈው 5ኛ ሀ ገራዊ ምርጫ ወቅት ባካሄድነው ወቅት ገልፆ ነበር፡፡ የሚትሰጡት አገልግሎት በቂ አይደለም፤ እየሰራቹ ያላቹ ልማት ጥሩ ቢሆንም በቂ አይደለም፤ ጠጠር መንገዶች አስፓልት ሊሆኑ ይገባል፤ የ1ኛ ደረጃ ት/ቤት ብቻ በቂ አይደለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሊመጣ ይገባል፤ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስትገነቡ ፕሪፓራቶሪ ሊመጣ ይገባል፤ ፕሪፓራቶሪ ስትገነቡ ዩኒቨርሲቲ ሊመጣ ይገባል እያለ በሁሉም ቦታዎች ሲጠይቅ ነበር፡፡ ኪሊኒክ ብቻ በቂ አይደለም ሆስፒታል ሊኖር ይገባል፤ ሆስፒታል ብቻ በቂ አይደለም ሪፌራል ሊኖር ይገባል፤ አስፓልት እኛ ጋም ሊደርስ ይገባል፤ የንፁህ መጠጥ ዉኃ አገልግሎት እና ጋም ሊደርስ ይገባል፤ መብራት በየቤታችን ሊኖር ይገባል፤ የምትሰጡት የቴሌ አገልግሎት በጥራት እኛ ጋም ሊደርስ ይገባል በሚሉ አካሄዶች የልማት ጥያቄዎችን በሰፊው ሲያነሳ ነበር፡፡

በብዛት ተጀምረው ያሉ ፕሮጀክቶችም በጊዜ አያልቁም፤ ቢያልቁም ጥራት የላቸውም፤ የግብርና ታክስ ስርዓታቹ ግድፈት አለው፤ የአገልግሎት አሰጣጣቹ ግድፈት አለው፤ የመሬት አስተዳደራቹ ግድፈት አለው፤ በአጠቃላይ በፍትህ ስርዓታቹም ላይ ችግር አለ፤ ፍትህ በወቅቱ አይሰጥም፤ ፍትህ ማገኘት ላይም ትልቅ ችግር አለ በማለት በሰፊው በቀበሌ ደረጃ ሊፈቱ የሚገቡትን፤ በወረዳ ደረጃ ሊፈቱ የሚገቡትን፤ በክልል ደረጃ ሊፈቱ የሚገቡትን፤ በፌዴራል ደረጃ ሊፈቱ የሚገቡትን ጉዳዮች አንድ በአንድ በተርታ ሲያነሳ ነበር፡፡ በሌላ መንገድም ይህንኑ ሲያነሳ ቆይቷል፡፡ በዚህ ሰሞን የተከሰቱ ጉዳዮችም ፌዴራሊዝምን መቃወም ሳይሆን ለፌዴራሊዝሙ ዘብ መቆም ነው ብለን ነው የምንወስደው፡፡ ይህን መንግስት እኔ ነኝ ያቋቋምኩት፤ እኔ የፈለግኩትን ይሰራል እንጂ ለራሱ የፈለገውን ሊሰራ አይገባም ብሎ የመረጠው ነው፡፡ በትግሉ፤ በድምፁ ነው መንግስትን የመሰረተው፡፡ የድርጅታችን ፍሬ ትግል ነው ይህን አይነት ህዝብ የፈጠረው፡፡ ይህን እንደ ስኬት እንጂ እንደ ድክመትና ውድቀት አናየውም፡፡ ጠያቂ ህዝብ ለመፍጠር ነው የታገልነው፡፡ ለወደፊትም ጠያቂ ህዝብ እንዲሆን ነው፡፡ መብቱን ለማይጠይቅ ተማሪ ለመፍጠር አይደለም ትግሉ፡ ይበቃኛል ብሎ ዝም የሚል ህዝብ ለመፍጠር አይደለም የታገልነው፡፡ ለወደፊትም በሰፊው የሚጠይቅ ህብረተሰብ ለመፍጠር ነው ትግላችን፡፡ ህዝብን ፈርቶ የሚኖር መንግስት፡ አዛዡ ህዝብ እንደሆነ አውቆ የሚኖር መንግስት ለመፍጠር ነው ትግላችን፡፡ የድርጅታችን ትግል ይህ በመሆኑ እኔም እንደ ድርጅቱ አባል በድርጅታችን ትግል ፍሬ በጣም ደስተኛ ስሜት ነው የሚሰማኝ፡፡

ህዝቡ ያነሳው ተቃውሞ ምንድነው፤ አንደኛ፡ ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ ደረጃ በደረጃ ያሉ ጉዳዮችን በማንሳት በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል የሚለው:: ሁለተኛ፡ ከማስተር-ፕላን ጋራ ተያይዞ ማስተር ፕላኑ ምነድነው አይደለም አላማው ምንድነው አይደለም ይዘቱ ምንድነው አይደለም የሚሉ ጉዳዮች በጊዜው ገና በእቅድ ደረጃ የነበረና በኛ በኩልም በቂ ማብራርያ ባለመሰጠቱ ጋራ ተያይዞ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች ሃይሎች ይህን እድል እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የማስተር-ፕላኑ ዓላማ ያልሆነ፤ የማስተር-ፕላኑ ይዘት ያልሆነ፤ የማስተር-ፕላኑ አካሄድ ያልሆነ ህዝብን ጥርጥር ውስጥ ሊያስገባ በሚችለው አኩኃን ወጣቶቻችንን በመቀስቀስ የኦሮሞ መሬት ለአዲስ አበባ ተቆርጦ እንደሚሰጥ፤ የአዲስ አበባ መስፋፋት በኦሮሚያ ዋጋ መክፈል እንደሆነ፤ ይሀ ፌዴራላዊ ስርዓት እንደወደቀ ነገር በማስመሰል ሲቀሰቀሱ ነበር፡፡ የኛ ሀገር ፌዴራሊዝም ወሰንን ማካለልና ወሰንን ስለማዋሀድ አይደለም፡፡  አስተዳደርን ስለማዋሰን ብቻ አይደለም ፌዴራሊዝማችን፡፡ ማንነትንም ያዋስናል፡፡ ማንነትንም ያዋስናል፡፡ የኛ ሀገር ፌዴራሊዝም የሚዋሰነው በማንነት ነው፡፡ በቋንቋ ነው፡፡ በባህል ነው፡፡ ባለው ማንነት ነው፡፡ በማንነት፣ በቋንቋና በባህል ላይ የተመሰረተ ነው ይህ ፌዴራሊዝም፡፡ ይህ በመሆኑ አንድ መሬት ከዚ ተወስዶ ወደዛ ሲሰጥ ከማንነት ጋራ ነው አብሮ የሚሰጠው፡፡ ስለዚህም ነው እኔ የገነባሁትን ፌዴራሊዝም ሊያፈርሱ ነው ወይ በሚል እሳቤ ለፌዴራሊዝም ዘብ በመቆም የተቃወመው፡፡ የጠረጠረውን ነገር በይፋ አውጥቶ የመረጠውን መንግስትቶ ጠየቀ፡፡ መቶ በመቶ መርጦት እኮ ነው፡፡ አሁን የሚቀርቡ አማራጮች ሁሉ ቀርቦ እኮ ነው፡ እናንተ የጥፋት ኃይል እንጂ የልማት ሓይል ልትሆኑ አትችሉም ብሎ መቶ በመቶ ድርጅቱን የመረጠው፡፡ በሚገርም ሁኔታ ከምርጫ ምዝገባ አንስቶ፤ ከምርጫ ዕለት ጀምሮ በነቂስ ወጥቶ መርጦ እንዳይረብሹት በሁለተኛው ቀን ወደ ልማት ስራው የገባው፡፡ ከዚህ የበለጠ ለድርጅቱም ለመንግስቱም ትልቅ እምነት ያለው ነው የሚመስለኝ፡፡

ድርጅታችን ያለበት ችግሮችን እራሱ ማስተካከል ይችላል ብሎ ነው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ሲያነሳ የነበረው፡፡ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ከማስተር-ፕላን ጋራ የተያያዙ ጉዳዮች ጥርጣሬ በመፍጠራቸው፤ እነዚ የጥፋት ኃይሎች ለራሳቸው ፖሊቲካ ጥቅም እንደ መልካም አጋጣሚ ስለተጠቀሙበት ይሀ ረብሻ ተፈጥሯል ብለን ነው የምናምነው፡፡ እንጂ የራሱን ድርጅት በመቃወም፤ የራሱን መንግስት በመቃወም፡ ፌዴራሊዝሙን በመቃወም ነው ብለን አናምንም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ለዚህ ፌዴራሊዝም ብዙ መሰዋዕትነት ከፍሏል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ከጅማሮው እነዛ ይሀ ፌዴራሊዝም ሊፈርስ ይገባል ብሎ ረገጠው ሲወጡ፡ ይሀ ፌዴራሊዝም መኖር አለበት በማለት ዘብ ሲቆምለት በነዚ አካላት ጭምር ሲቃጠል የነበረው የኦሮሞ ህዝብ ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ለዚህ ፌዴራሊዝም ግንድ ነው፡፡ በመሰዋዕትነት ነው የገነባው፡፡ ይሀን በመሰዋዕትነት የገነባውን ፌዴራሊዝም የሚቃወምበት ሁኔታ ተፈጥሮም አያውቅም፡፡ እነዚህ ጉዳዮች በጥቅሉ ለችግሩ መነሻ ናቸው ብለን ነው የምናየው፡፡

Photo - Fekadu Tessema, Oromia Comm Bureau head
Photo – Fekadu Tessema, Oromia Comm Bureau head

ሆርን አፌርስ፡- በዚህ ተቃውሞ ውስጥ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና እንዲሁም ከፀጥታ ኃይሎች የብዙ ሰው ህይወት እንደጠፋ ይታወቃል፡፡ በቁጥር ይታወቃሉ? ይህን ያህል ሰው ነው የሞተ ተብሎ በቁጥር ይታወቃል?

አቶ ፍቃዱ ተሰማ፡ ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡ በመጀመሪያ ህዝቡ በአግባቡ ጥርጣሬ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ጥያቄ ማንሳቱን እንዳለ እንውሰደውና ሌሎቸ አካላቶች ግን ለረብሻና ለራሳቸው ዓላማ በመጠቀም በሰላማዊ መንገድ መነሳት እየተቻለ መፈጠር የሌለበተ ነገር ተፈጥሮ የዜጎቻችን ህይወት፡ በአካል ላይም፤ በወደደመው ንብረትም ጉዳይ ድርጅታችን በተለያዩ  ጊዜያት የክልሉ መንግስትም በግል በሰጠው መግለጫ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን ስንገልፅ ቆይተናል፡፡ ሀዘን መግለፅ ብቻም አይደለም ይሀ ጥፋት የደረሰባቸውን አካላት ማጠናከርና መልሶ-ለማቋቋምም መንግስት ቁርጠኛ ነው፡፡ ከጎናቸው እንደሚቆምም በተለያዩ ጊዜያት ሲገልፅ ቆይቷል፡፡ መፈጠር የሌለበት ነገር ነው የተፈጠረው፡፡ በዚ በጣም አዝነናል፡፡ በዚ ምክንያት ውድ ህይወታቸውን ላጡ ሁሉ በጣም ነው የማዝነው፡፡ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላ የኦሮሞ ህዝብ ብርታትን እመኛለሁ፡፡ እነዚ አካላት ጎን መንግስት ለመቆም ዝግጁ መሆኑን በዚህ ሚዲያም ተጠቅሜ ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡

በሌላ በኩል በዚህ ሂደት ውስጥ ስንት ሰው ሞተ እንዴት ሞተ የሚሉትን ጉዳዮች የተለያዩ የፖለቲካ አካላት ለራሳቸው ፖሊቲካዊ ጥቅም ሊሰጥ በሚችል መልኩ የተለያዩ መግለጫዎችን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ እኛ እንደ ህዝባዊነታችን ከዚ ጉዳይ ጋራ ብቻ ተያይዞ፤ መፈጠር ከሌለበት ረብሻ ጋራ ብቻ ተያይዞ ከፀጥታ አካላትም ይሁን፤ በህብረተሰቡ ውስጥ በተፈጠሩ ጉዳዮችም ይሁን፤ ጦር መሳሪያ ይዘው ከፀጥታ አካላት ጋራ ሲታኮሱም ይሁን፤ በመካከል በተደረገ ፍልሚያም ይሁን፤ በመሀከላቸው በተከፈተው ተኩስ ይሁን የሞቱት እነ ማን እንደሆኑ ዜጎቻችን በመሆናቸው ጠቅላላውን በተጨባጭ አጣርተን ከነምክንያት የሞቱትን፤ የቆሰሉትን፤ ሆስፒታል ከገቡ የሞቱትንም ሆነ በጥቅሉ የክልሉ መንግስት እያጣራ ይገኛል፡፡ ይሀ ተጣርቶ ሲያልቅ የክልሉ መንግስት አስፈላጊ በሆነ አካል የምንገልፀ ይሆናል፡፡ ይሀ በተደጋጋሚም መግለጫ የተሰጠበት ጉዳይ በመሆኑ ዜጎቻችን እንደ ሞቱ ግልፅ ነው፡፡ ጉዳት እንደ ደረሰባቸውም ግልፅ ነው፡፡ ሊደበቅ አይችልም፡፡ አንድ ዜጋችንም ይሙት መቶም ይሙት ሀዘናችን አንድ ነው፡፡ የአንድም ሰው ህይወት መጥፋት አልነበረበትም፡፡ ይህ በመፈጠሩም በጣም አዝናለሁ፡፡ ያሉትን ጉዳዮች በተመለከተ ግን አሰፈላጊ ሲሆን በአስፈላጊው አካል የሚገለፅ ይሆናል፡፡

ሆርን አፌርስ፡- ተቃውሞውና ረብሻውን ለማስቆም ጥረት በሚደረግበት ወቅት የሰላም ማስከበሩ ሂደት አካላት ሚና ይታወቃልን? እነ ማን ናቸው? አጋዚ የሚባለው ነበር ወይስ?

አንደኛ፡ ረብሻው በስፋት በአንዴ በብዙ ቦታዎች በሚነሳበት ወቅት እነዚ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ሁሉንም ቦታ ለማዳረስ ከቁጥራቸውም ጋራ በተያያዘ ችግር ነበር፡፡ ከዚሀ በመነሳትም በፀጥታ ማስከበሩ ሂደት በቅድሚያ የተሳተፈው ሚሊሻችን ነው፡፡ በየመንደሩ ያሉ ሚሊሻዎቻችን፡፡ የኦሮሚያ ክልል ሚሊሻ ማለት ነው፡፡ ባለበት ሰፈር፤ ቀበሌና ወረዳ መጀመሪያ በፀጥታ ማስከበር ሂደቱ ተሳታፊ የነበረው ሚሊሻችን ነው፡፡ በተከታይነት የክልሉ ፖሊስ ነው፡፡ በመቀጠል የክልሉ አድማ-በታኝ ፖሊስ ነው፡ በቁጥር ጥቂት ቢሆኑም፡፡ ከነዚህ አካላት አቅም በላይ ሲሆን በስፋቱ ሁሉንም ቦታ ማዳረስ ስለማይቻል ረብሻው አንድ ቦታ ሲጀምር፤ ሌላ ቦታም ይቀጣጠል ስለ ነበር፤ አካሄዱም በጣም አደገኛ የነበረ በመሆኑ መንገድ መዝጋት ነበር፤ ከሚሊሻ በማስገደድ ጦር መሳሪያዎችን መቀማት ነበር፤ በጦር መሳሪያ መደገፍ ነበር፤ ከዚህም አልፎ ማረሚያ ቤቶችን በመስበር እስረኞችን የማስለቀቅ ጥረት ነበር፤ የአስተዳደር ተቋማትን ማፍረስ ነበር፤ ፖሊስ ጣቢያን ሰብሮ ትጥቅን መውሰድ ነበር፡፡ ጉዳዩ እየከፋ ሲሄድ ፌዴራል ፖሊስም እነዚህን የፀጥታ አካላት ለማገዝ በተለያዩ ቦታዎችና ረብሻ በተነሳባቸው ቦታዎች በሰላም ማስከበሩ ሂደት ላይ ተሳትፏል፡፡

ከነዚህ አካላት በላይ በሆነበት አከባቢዎች ደግሞ ተጨማሪ ኃይልም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተሳትፏል፡፡ አጋዚ የሚባለው ሳይሆን – አጋዚ በኃይልም ይህን ቦታዎች ሁሉ ማዳረስ አይችልም ነበር፡፡ ቁጥሩንም ስናየው በቁጥርም ትንሽ ነው፡፡ ሚናውም ይህ አይደለም፡፡ በሰላም ማስከበር ሂደቱ የተሳተፉት ሚሊሻ፤ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ፤ ፌዴራል ፖሊስ እና እንዲሁም የሀገር መከላኪያ ሰራዊት ባሉበት አከባቢዎች በተወሰነ ደረጃ ማለት ነው፡፡ ሁሉም በተለያዩ ጊዜያት ሳይሆን ባሉበት አከባቢ ነው የተሳተፉት፡፡ ለምሳሌ፤ ምስራቅ ውስጥ ምስራቅ ዕዥ የሚገኘው የሀገር መከላኪያ ሰራዊት በአከባቢው የሰላም ማስከበር ሂደት ውስጥ በዬትኛውም ወቅት ድጋፍ ይሰጣል፡፡ ዛሬ ብቻም ሳይሆን በምርጫ ወቅትም፤ በበዓላት ቀንም በአስፈላጊ ወቀቶች የህብረተሰቡን ሰላም ለማረጋገጥ በሰላም ማሰከበሩ ሂደት ይሳተፋል፡፡ እነዚ ኃይሎች ለምን ተሳተፉ ብለን በምናይበት ወቅት ለምን ይህን ኃይል ሁሉ ማሰማራት አስፈለገ የሚለውን ለማወቅ እነዚን ኃይሎች ባናሳትፍ ኖሮ ምን ይመጣ እነደነበር ማየቱ የሚቻል ይመስለኛል፡፡

አንደኛ፡ እነዚ የጥፋት ኃይሎች ክልሉን ወደለየለት ህግ አልባነት በመቀየር፤ የፈለጉትን ገድለው፤ የፈለጉትን አቃጥለው እንዳሻቸው መሆን ነበር ምኞታቸው. በተግባርም ንብረት ማውደም ነበር፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን ዝርፍያም ነበር፡፡ የሰው ህይወት በብዛት ማጥፋት ነበር፡፡ በኃይል ህብረተሰቡን ከጎናቸው ማሰለፍ ነበር፡ እምቢ ያለውን ሰው ቤት ማቃጠል ነበር፡፡ አርሶ አደሩ በላቡ ዓመት ሙሉ አርሶ፤ አርሞ ያመረተውን ምርት ማቃጠል ነበር፡፡ ስለዚህም እነዚህን ነገሮች ባሉበት ለማስቆም የህብረተሰቡን የዜጎቹን ሰላም ለማረጋገጥ ነው እነዚ ኃይሎች የተሰማሩት::

ሁለተኛ፡ የፌዴራል ፖሊስም ቢሆን አብዛኛው ኦሮሞ ነው፡፡ ሌላ አካል አይደለም፡፡ የፌዴራል ፖሊስም የክልላችን ሰላም ለመጠበቅ ነው፡፡ የሀገራችንን ሰላም ለመጠበቅ ነው፡፤ አንድ ኃይል ነው፡፡ ይህን ፌዴራሊዝምም እሱ ነው የገነባው፡፡ የሀገር መከላኪያ ሰራዊትም ብንል የሀገር መከላኪያ ሰራዊት ከዬት ውስጥ ነው የወጣው! ኦሮሞ በስፋት በውስጡ የሚሳተፍበት ነው፡፡ የተለየ ነገር የለም፡፡ የአንድ ብሔር ጉዳይ ለማድረግና ለመለያየት የሚሞከር ዓላማ ካልሆነ በስተቀር እነዚ የፀጥታ ኃይሎች የህዝቡን ሰላም ለመጠበቅ ነው፡፡ ያደረገውም ይህ ነው፡፡ በተወሰኑ ቦታዎች የታዩ ግድፈቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ግድፈቶቹ ሌላው አካል እንደሚፈፅምም፤ እነዚ የፀጥታ አካላትም ከሰማይ አይደለም የወረዱት፡፡ ሁሉንም ነገር በንፁህ ይፈፅማል ማለት አይቻልም፡፡ በተወሰኑ ቦታዎች ያልተገባ ተግባር ፈፅሞ ይሆናል፡፡ ህብረተሰቡ የተናገራቸው ነገሮች፤ በተጨባጭም ሊደረሰባቸው ጥረት ላይ ያሉ ጉዳዮችም አሉ፡፡ ይህን በፍጥነት ማስተካከልና ያልተገባ ድርጊት የፈፀሙ አካላትም የሚጠየቁበት ሁኔታ አለ፡፡ በግዳጁ ላይም የሚጠየቅበት አኩኃን አለ፡፡ እነዚ ጉዳዮች በጥቅሉ ይህን ይመስላሉ፡፡ ትልቅ ማዕከል የተደረገውም የህዝቡ ሰላም ነው፡፡ ቤቶች እንዳይቃጠሉ፤ የህብረተሰቡ ንብረት እንዳይወድም፡ በግድ ህዝቡ እንዲቃወም እንዳይደረግ፤ መንገድ እንዳይቋረጥ ነው ዓላማው፡፡ በጥቅሉ መኪና እያስቆሙ መንገድ ለማሳለፍ ገንዝብ ክፍያ መቀበል ነበር፡፡ የህግ የበላይነት ከሌላ፤ የህግ የበላይነት ካልተረጋገጠ ምን አይነት ሀገር ሊኖረን እንደሚችል ማየቱ በቂ ይመስለኛል፡፡ እንደነ ሶሪያ፡ እንደነ ሶማሊያ እንዲሆን እየተሰራ የነበረው ስራ ኃይለኛ ስለነበር ይህን ለማረጋጋት ጥረት ተደርጓል፡፡ የአጋዚ ጉዳይ እንዲህም የተሰማራው ሰራዊት የአንድ ብሔር ሰራዊት ነው ተብሎ የሚራገበው ወሬ ተቀባይነት የለውም፡፡ በሀገሪቱ ህግ የተደነገገ ነው ይሄ፡፡ የፌዴራል ፖሊስም የሚመሰረተው እንዲሁም የሀገር መከላኪያ ሰራዊት የሚመሰተው በይፋ በብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተሳትፎ ነው፡፡ የሀገርን ሰላም ማስጠበቅ ነው፡፡ ከዚህ ያለፈ የለውም፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ ሊደርሰው ይችል የነበረው ጥፋት ምን እንደሆነ ማየት ይቻላል፡፡ ይህ እንዳይከሰት ለመከላከል ነው፡፤ የፀጥታ ኃይሎች ተሳትፎም ያረጋገጠው ይህንኑ ነው፡፡ መንግስትም ይህንኑ ነበር የሰራው፡፡ እንደኛ አንደኛ ከሁሉም በላይ ግን የሀገር መከላከያ ሰራዊትም አይደለም፤  ፌዴራምል ፖሊስም አይደለም፤ የኦሮሚያ ፖሊስም አይደለም፤ ሚሊሻችንም አይደለም፡፡ ትልቁን ሚና የተጫወተው ህዝቡ ነው፡፡ ጥያቄው መጠለፉን  ሲያውቅ፤ የሱ ቤት ብቻ መቃጠል ሲጀምር፤ መንገዶች ተዘግተው መንቀሳቀስ ሳይችል ሲቀር፤ እርጉዝ እናት የጫነ አምቡላንስ በመንገድ ላይ መቃጠል ሲጀምር፤ አመት ሙሉ በላቡ አርሶ ያመረተው ምርት በእሳት መቃጠል ሲጀምር ጉዳዩ የሱ እንዳልሆነ ገባው፡፡ ህዝቡ ነው የተጋፈጣቸው፡፡ ህዝቡ ባይጋፈጣቸው ኖሮ የዚህ ሀገር ሰራዊት አይደለም የመላው አፍሪካ ሰራዊት ብናመጣ የሚቆም  ነገር አልነበረም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ የጠየቀው ጥያቄ ግልፅ ነው፡፡ ለራሱ መንግስትና ለመረጠው ድርጅት ነው ያቀረበው፡፡ ግልፅነት የሌለው አካሄድ እንዲብራራለት፤ ከዕድገት የመጡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱለት በግልፅ አስቀምጧል፡፡ ከዚህ ውጭ ጥያቄ የለውም፡፡ ሌላ ብሄር የማጥፋት ጥያቄ የለውም ህዝባችን፡፡ ንብረት የማውደም ጥያቄ የለውም ህዝባችን፡፡ ሰው የማረድ፤ ሰው የማቃጠል ጥያቄ የለውም ህዝባችን፡፡ ባህሉም አይደለም፡፡ ይህ በመሆኑ በሰላም ማስከበሩ ሂደት የማይተካ ሚና የነበረው እራሱ ህዝባችን ነው፡፡ የፀጥታ ኃይሎች ሚና በሁለተኝነት የሚቀመጥ ነው፡፡ ግዴታውም ስለሆነ ማለት ነው፡፡ ይህ ነው ያለው፡፡

ሆርን አፌርስ፡ ኦህዴድ እንደ ኦሮሞ ህዝብ ፖሊቲካ ድርጅት በክልሉ ውስጥ ተከስቶ ከነበረው ተቃውሞ ምን ይገነዘባል? እነደ ፖሊቲካ የሚሰጥ መልስስ ይኖራል?

አቶ ፍቃዱ ተሰማ፡ ድርጅታችን የኦሮሞ ህዝቦች ዲሞክራሴያዊ ድርጅት ኦህዴድ የተፈጠረውም ከአርሶ-አደሩ ህዝባችን ነው፡፡ መሰዋዕት በመክፈል እዚህ ያደረሱት የድርጅቱ ታጋዮችም አርሶ-አደሮች ናቸው፡፡ ድርጅቱም የቆመው ለሰፊው የአርሶ-አደር ህዝባችን ነው፡፡ ሌላ ሰው የለም፡፡ ሰፈው አርሶ አደር ፍላጎቱ ሲሞላ፤ ህይወቱ ሲለወጥ የከተማው ነዋሪም ሌላም ህብረተሰብ ህይወት ይለወጣል ብሎ ያምናል፡፡ ለገጠሩ ህዝብና ለአርሶ-አደሩ ቆመ ሲባል ለከተማው ህብረተሰብና ለሌላው ማህበረሰብ አልቆመም ማለት አይደለም፡፡ የቆመለት ውግንና በአርሶ-አደሩና በገጠሩ ያለው ችግር ሲፈታ የሌላውም ህብረተሰብ ችግር አብሮ ይፈታል ብሎ ማሰቡ ነው፡፡

ከዚህም በመነሳት የሚገጥሙትን ችግሮች ሁሉ በራሱ ቁጭ ብሎ ከማየት ይልቅ ወደ ህዝቡ ተመልሶ ከህዝቡ ጋራ ይወያይበታል፡፡ ምን ችግር ተፈጠረ፡ ምንድነው የተከሰተው ብሎ ይወያያል፡፡ ፊትለፊት ይወያያል፡፡ በውይይቱም ህዝቡም በተደጋጋሚ የጠየቀው ትልቅ ለውጥ አምጥታቿል፤ ትልቅ ድል እንድንቀዳጅ አድርጋቿል፤ ልማት አስተምራቹናል፤ ሁሉንም መብት አግኝተናል፡፡ ነገር ግን አሁንም ልማቱ ሊቆም አይገባም፤ በበለጠ ደረጃ ልማቱ ሊመጣ ይገባል፡፡ የመልካም አስተዳደር ስራዎች የምትሉት ነገር በህይወታችን ውስጥ ትልቅ ድርሻ ስላላቸው በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል ብሎ ነው በዝርዝር ያስቀመጠው፡፡

ማስተር-ፕላኑን በተመለከተም በ2006 አምቦ ላይ ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው በደረጃ ከዚ ያነሰ ቢሆንም ችግር ተፈጥሮ ነበር፡፡ ችግሩ እንደተፈጠረ በማራጋጋት በሰፊው በውይይት ውስጥ ተገብቶ ነበር የቆመው፡፡ ወይም ተወያይተን አስፈላጊ ከሆነ እንቀጥልበታለን ተብሎ ነበር አካሄዱ የተገለፀው፡፡ እኛ ግን አረጋግተን ብቻ ነው ያቆምነው፡፡ የናንተ ስራ የእሳት ማጥፋት ስራ ሊሆን አይገባም፤ ከመሰረቱ ነው ችግር መፍታት ያለባቹ የሚሉ ሀሳቦች ነበሩ፡፡

ድርጅታችን ኦህዴድም እንደ ድርጅት ቆሞ የተፈጠረው ችግር ዬት ችግር ተፈጠረ ብሎ እራሱን የሚፈትሽ፤ መልሶ ለህዝቡ የሚነግር፤ ህዝቡም እንዲነግረው የሚያደርግ፤ በሁለቱ ድምር ጠንክሮ የሚወጣ ድርጅት በመሆኑ ትልቁ ያየው ነገር ህዝቡ የሚያነሳቸው ችግሮች በፍጥነት መልስ ከመስጠት ጋራ ተያይዞ ጉድለቶች እንዳሉበት አይቷል፡፡ ይሀ ቢሆን ኖሮ ለነዛም ክፍተት አይፈጥርም ነበር፡፡ እንደ መልካም አጋጣሚ ለመጠቀምም ክፍተት አያገኙም ነበር፡፡

ሁለተኛ፡ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ህዝቡን እያሰለቹት፡ ህዝበችንን እያስከፉት ስለሆነ ጊዜ ሳይሰጠው መፍታት እንዳለብን ተገንዝበናል፡፡ ሦስተኛ፡ ወጣቱን የማህበረሰብ ክፍል በሰፊው አስተምረናል፡፡ መማሩ ጥቅማችን ነው፡፡ አሁንም ከዚ በሰፋ መልኩ እናስተምራለን፡፡ ተምሮ በሚወጣው ህዝብ ልክ የስራ ዕድል እየፈጠርን ነው ወይ! በየገጠሩ የስራ እድል እየፈጠርን ነው ወይ! በየከተማው የስራ እድል እየፈጠርን ነው ወይ! በስራ ፈጠራ ላይ እየተሞከረ ያሉ ጥረቶች አሉ፡፡ ከችግሩ ስፋት አኳያ ስታይ ግን የሚመጣጠን አይደለም፡፡ በጥፋት ውስጥ ተስፋ የሌለው ሰው ለዬትኛም ወገን ቢሰለፍ የሚያስገርም ነገር አይደለም፡፡ እዚህ አከባቢም የምናያቸው ነገሮች ይኖራሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በተለይ በአዲሱ ትውልድ ላይ መስራት አስፈላጊ መሆኑ፤ ድርጅታችን በትናንቱ ወጣት የተገነባ ቢሆንም አሁንም አባል እና አስፈፃሚዎቹ በስፋ ወጣት ቢሆኑም በሁሉም የኦሮሞ ወጣት ልብ ውስጥ በአግባቡ ለመስረፅ በሚያስችል መልኩ የበሳል  ፖሊቲካ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ድርጅታችን እንደ ችግር ለይቷል፡፡ ወደፊት ይህን ሰርቶ ከግብ እንዲደርስ እምነቴ ነው፡፡

ሆርን አፌርስ፡ የኦሮሞ ህዝቦች ዲሞክራሴያዊ ድርጅት ኦህዴድ እነደ ኢህአዴግ አካል፤ እንደ ገዥው ፓርቲ የሚጫወተው ሚና ትንሽ ነው ይባላል፡፡ ስልጣን የለውም ተብሎም ይታማል፡፡ እዚሀ ላይ ምን ይላሉ?

አቶ ፍቃዱ ተሰማ፡ ይህ ድርጅት (ኦህዴድ) ከተመሰረተበት ዕለት አንስቶ የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ አንግቦ ያካሄደው መራራ ትግልና የከፈላቸውን መሰዋዕትነቶች በተጓዳኝ፤ ኦነግ በኦሮሞ ህዝብ ስም በቅድሚያ ተደራጅቶ እንደ አንድ ድርጅት የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን እመልሳለሁ ብሎ በመነሳቱ የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ለዚህ ጉዳይ አዎንታዊ ዕይታ አለው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ስለሆነ፡፡

ግን የኦሮሞ ህዝብ ትግል በዚህ ቆይታ ውስጥ ከብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ትግል ጋራ መተሳሰር ባለመቻሉ የኦሮሞ ህዝብ ትግል መሬት ላይ እየተጓተተ፤ እየቀጨጨ፤ ብዙ መሰዋዕትነት እየተከፈለበት የመጣ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ኦህዴድ የኦሮሞ ህዝብ ትግልን ከሌሎች ተጨቋኝ ብሔር በሔረሰቦች ትግል ጋራ በማስተሳሰር የተለየ አማራጭ ይዞ የወጣ ድርጅት ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ባህልን ፣ማዕከል አድርጎ የወጣ ድርጅት ነው፡፡ ከህዝቦች ጋራ መኖርን መሰረት አድርጎ የወጣ ድርጅት ነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ሁሉም ችግሮች ይፈታሉ ብሎ የወጣ ድርጅት ነው፡፡

ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችን ሁሉ እንደ ጠላት የሚያይ ሳይሆን፤ ጠላቱን እንደ ጠላት፤ የትኛውንም ነፍጠኛ እነደ ነፍጠኛ ለዬትኛውም ብሔር ጠላት ነው ብሎ፤ ሌሎች ቤሔር ብሐየረሰቦች ግን ዘመድ ናቸው ብሎ የጠራ መስመር በመያዝ የወጣ ነው፡፡ ይሀ ላይ ልዩነት አለን፡፡ ይሀ ድርጅት (ኦህዴድ) ከተመሰረተበት ዕለት አንስቶ እስከ ዛሬም ድረስ ከትምክህተኞም ሆነ ከጠባቡ ኃይል ህዝቡ በድርጅታችን ላይ ጥርጣሬ እንዲያሳድር እየዘመቱ ይገኛሉ፡፡ ለወደፊትም በድርጅታችን ላይ መዘመታቸውን ያቆማሉ ብዬ አላስብም፡፡ ይሀ ደግሞ እናን ያጠናክረናል እንጂ አያንበረክከንም፡፡ የትግላችን መልስም ይሀው ነው፡፡

ኢህአዴግ በሚለው ጉዳይ ላይ በተጫባጭ መሬት ላይ ባለው ነገር ወሳኙ አካል ኦህዴድ ነው፡፡ ከአህዴድ ውጭ ኢህአዴግን ማሰብ የሚቻል ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ኢህአዴግ መሰረቱን ገጠርን ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀሰው፡፡ ወገንተኝነቱ ለአርሶ አደሩ ነው፡፡ የአርሶ አደሩ ህዝባዊ መሰረት ኢህአዴግ ነው፡፡ የኢህአዴግ መሰረት አርሶ አደሩ ከሆነ ሰፊው የአርሶ አደር ማህበረሰብ የሚገኘው በኦሮሚያ ነው፡፡ በኦሮሚያ ክልል ደግሞ የሚያስተዳድረው ኦህዴድ ነው፡፡ ኢህአዴግ ከወደ 6 ሚሊዮን በላይ አከባቢ ካለው አባል ከግማሽ በላይ ያለው የኦህዴድ አባላት ናቸው፡፡ ሰፊ አባል ያለው ኦህዴድ ነው፡፡ ለዚህ ፌዴራሊዝም ማዕከሉ ኦህዴድ እና ኦሮሞ ህዝብ ናቸው፡፡ ተወደደም ተጠላም፡፡

ድርጅታችን ኢህአዴግ በጋራ ደንብ የሚተዳደር ነው፡፡ ሁሉም አካላት በመንገድ ላይ የተገናኙ ሳይሆን በዓላማ ላይ ግንባር የፈጠሩ ናቸው፡፡ ሁሉም በራሱ ክልል ያስተዳድራል፡፡ በኢህአዴግ ውስጥ ሁሉም ድርጅት አባላት የመቃወም፤ የመደገፍ መብት አላቸው፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ ሚና እንደሌለን አድርጎ የሚያነሱ አከላት ይሀ ፌዴራሊዝም እንዲፈርስ ምኞት ያላቸው ናቸው፡፡ በዚ ፌዴራሊዝም ላይ የኦሮሞ ህዝብ ጥርጣሬ እንዲያሳድር ሚና የለውም በማለት ህዝቡ በጥርጣሬ ውስጥ እንዲገባ ነው ፍላጎታቸው፡፡ እስካሁን የመጣው ልማት የኦህዴድ አመራር ፍሬ ነው፡፡ ኢህአዴግ የሚኮራበት፡፡ የህዳሴ ግድቡን እንኳን ብንወስድ ትልቁ ተሳትፎ የኦሮሚያ ክልል ነው፡፡ በዚህ መንገድ ማየት ያስፈልጋል፡፡

በሌላ መንገድ ደግሞ እየገነባን ያለነው የፌዴራሊዝም ስርዓት ነው፡፡ በዚሁ ፌዴራላዊ ስርዓት ውስጥ ትልቅና ትንሽ ብሔርም እኩል መብት አላቸው፡፡ ትንሽ ብሔር ነው ብለህ መብቱን ልትወስድበት አትችልም፡፡ ትልቅ ብሄር ነው ብለህ ሌላውን ማስበለጥም የለም፡፡ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በቁጥራቸው ልክ ይወከላል፡፡ የፌዴሬሽን ም/ቤትም እንዲሁ፡፡በቁጥር አኃዝ ትልቁ ኦሮሞ ነው ማለት ነው፡፡ ኦህዴድ ነው ማለት ነው፡፡ መወከል ባለበት ቦታ በቁጥሩ ልክ ይወከላል፡፡ በቁጥር ብቻም ሳይሆን የራሱን የበጀት ድርሻም ይወስዳል፡፡ በቁጥሩ ልክ ይጠቀምበታል ማለት ነው፡፡ ከዚህም ባለፈ በአስፈፃሚም ደረጃ በቁጥሩ ይወከላል፡፡ የዚህ ሀገር ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሊወከሉ ይገባል ማለት ነው፡፡ ፌዴራሊዝሙ የኛ ነው ብሎ እንዲያምኑበት ሊሳተፉበት ሊወከሉበት ይገባል ማለት ነው፡፡ ይህንንም ስናይ በአስፈፃሚ ደረጃ ከ9ሚኒስትሮች ባላይ ነው ያለን፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ማዕከል አድርገን ብናይ ጥሩ ይመስለኛል፡፡

**************

Abdulbasit Abdusemed

more recommended stories