የጀርመን ሬድዮ አማርኛ አገልግሎት አምስተኛውን ዙር የፌዴራልና የክልል ምርጫ በተመለከተ ከሶስት ጋዜጠኞች ውይይት አድርጎ ነበር። የራዲዮ ጣቢያው ጋዜጠኛ ሂሩት መለሰ፡- ከየማነ ናግሽ (ሪፖርተር ጋዜጣ)፣ ከ.ይልማ ኃ/ሚካኤል (የጀርመን ሬድዮ የበርሊን ወኪል) እና ከገበያው ንጉሴ(የጀርመን ሬድዮ የብራስልስ ዘጋቢ) ጋር፤ ስለቅድመ ምርጫውና ድምፅ የተሰጠበት ሂደትና ውጤቱ እንዲሁም የወደፊት ዕጣፈንታና የውጭ ኃይሎች ሚና አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ከተነሱት መህል፡-
1/የማነ ናግሽ (ሪፖርተር ጋዜጣ):-
*የተቃዋሚ ተወካዮች እንዳይታዘቡ ተከልክለዋል። ውጤቱ ለጥርጣሬ ክፍት ያደርጓል።
*አባሎቻቸውን ገለልተኛ ታዛቢ ሆነው የቀረቡት የአገርውስጥ ማህበራት የፓለቲካ ድጋፍ እንዲሰጡ የተደራጁ እንጂ ገለልተኛ አይደሉም። *የውጭ ኃይሎች ላይ መንጠልጠል ጥገኛ አስተሳሰብ ነው። የጉዳዩ ዋና ባለቤት ህዝብ ነው። ህዝቡ ድምፄን ተሰርቋል ብሎ ካመነ እስከመቼ(ለምን) ቁጭ ብሎ ያያል?
*ተቃዋሚዎች በራሳቸው ለማሸነፍ አልገቡም። ተበታትነውና ዓቅመቢስ ሆነው ነበር የቀረቡት። አንድም ተቃዋሚ በተወዳደረባቸው ቦታዎች በሙሉ ቢያሸንፍ መንግስት ለመመስረት የሚችል አልነበረም።
* በእኛ ዓይነት ብዝኃ-ህብረሰብ ውስጥ በዚህ ደረጃ ማሸነፍ አይቻልም። አንድም ድርጅት እንዲህ ዓይነት የአስተሳሰብ አንድነት መፍጠር አይቻለውም። ውጤቱ ለኢህአዴግ አስደንጋጭ እንጂ መልካም ነገር አይደለም።ድርጅቱ ያየዘው አቋም መፈተሽ አለበት።
*ተቃዋሚዎችን በማድቀቅ ሳይሆን ሜዳውን ክፍት አድርጎ በተሻለ አስተሳሰብ ለመብለጥ መስራት አለበት።
*ነገሩ ሂዶ ሂዶ ወዴት እንደሚያደርሰን አይታወቅም። —–
2/ ይልማ ኃ/ሚካኤል (የጀርመን ሬድዮ የበርሊን ወኪል)፡-
*ማን አሸናፊ ሆኖ እንደሚወጣ ሳይታለም የተፈታ ነበር።
*የሸንጎ ምርጫ ከኳስ ጨዋታ ጋር እኩል ነው። ገለልተኛ ዳኛና ሜዳ በሌለበት አይደረግም።
*ዕርዳታ ሰጪ ምዕራባዊያን ዓይናቸውን ሳይጨፍኑ “ምንድን ነው የምናደርገው?” የሚሉበት ግዜ ደርሷል።
*መሰረታዊ ህገመንግስታዊ መብቶች የጣሰ ነው። —–
3/ ገበያው ንጉሴ(የዶቸቨሌ የብራስልስ ዘጋቢ):-
*ውጤቱ ቀድሞ የታወቀ ነበር።ለገዢው ፓርቲ ስልጣን ከማረጋገጥ ያለፈ ትርጉም የለውም። ታዛቢ ኖረም አልኖረም አንድ መራጭ ነፃ ሆኖ ድምፁ የሚሰጥበት የፓለቲካ ድባብ ከሌለ ምርጫ ተካሄደ ማለት አይቻልም።
*የኢህአዴግ የውስጥ ባህሪ ምርጫ የሚፈቅድ አይደለም።
*ለምርጫ ተብሎ ግዜና ገንዘብ ከማባከን ይልቅ የአውራ ስርዓት ዝምብሎ ቢቀጥልና የሚሆነውን ብናይ።
*ተቃዋሚዎችም ቁጭብለው ውስጣቸው ቢፈትሹ።
*ምዕራባዊያን ለእኛ ምጥን ዲሞክራሲ ነው ያላቸው። ወይም ለእኛ ደንታ የላቸውም። “የኢህአዴግ ታጋዮች የሞቱለትን ዓላማ ይህንን ዓይነቱ ምርጫ ለማድረግ ነበር ወይ!?”- የገበያው የመጨረሻ ጥያቄ ነው፡፡
——–
ሙሉውን ውይይት ከታች ባለው የድምጽ ፋይል ላይ ያድምጡ፡፡
***************
Comments are closed.
Leave a Comment