የቀድሞው ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት አፈጻፀም ሂደት ላይ የነበራቸው አቋም በወቅቱ ከነበረው የጋራ አመለካከት ሊከሰት የሚገባው ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው እንጂ አገር ለመጉዳት በማሰብ አይደለም በማለት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ገለጹት፡፡
ጄኔራሉ ይህንን የተናገሩት፤ በጦርነቱ ወቅት መለስ ለጦር መሣሪያ ግዥ በሚወጣው ገንዘብ መጠን ላይ ተቃውሞ ነበራቸው የሚለውን ስሞታ በመጥቀስ ላቀረብንላቸው በሰጡት ምላሽ ነው፡፡
አንዳንዶቻችን ኤርትራ ልትወረን ትችላለች ብንልም ሌሎች አትወረንም የሚል አመለካከት እንደነበራቸውም ጠቅሰዋል፡፡

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ኤታማጆር ሹም የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን፡- ጦርነቱ ድንገት የመጣ ቢሆንም የመከላከያ ሀይሉን የማደራጀት ሥራ ሲሠራ የነበረ መሆኑን የገለጹት ጄኔራል ጻድቃን፤ በዚህም ረገድ በአንድ ሚሊየን ፓውንድ ክፍያ የእንግሊዝ ኤክስፐርቶችን በመቅጠር የአየር ሀይል እና የአየር መከላከያ ሲስተም ጥናት መሠራቱን፣ የመካናይዝድ፣ ፓራኮማንዶና ኮማንዶ ሀይሎች ስልጠና እና የመሳሰሉ እንዲሁም የአዲስ ምልምል ወታደር የትምህርት ደረጃ 10ኛ ክፍል እንዲሆን እና የነባሩንም ትምህርት የማሳደግ ተግባራት መካሄዳቸውን አውስተዋል፡፡
እነዚህ ይህም በጦርነቱ ወቅት የሠራዊታችንን ብዛት ከ55,000 ወደ 350,000 ሲያድግ ያንን ሊሸከም የሚችል አቅም እንዲኖር ማስቻሉን አስረድተዋል፡፡
በጦርነቱ ወቅት የሴንትራል ኮማንድ አባል የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን፡- መለስ ዜናዊ ለጦር መሣሪያ ግዥ በሚወጣው ገንዘብ መጠን ላይ ተቃውሞ እንደነበራቸውና ‹‹ሌሎች ፕሮግራሞችን ሳናፋልስ ባለው በጀት ጦርነቱን እንፈጽም›› የሚል አቋም እንዳራመዱ ያረጋገጡ ቢሆንም፤ ያ አቋም ግን ሁሉም አመራር ይጋራው ከነበረው ለኢኮኖሚ ቅድሚያ ከመስጠት አመለካከት የሚመነጭ አድርገው እንደሚረዱት እንጂ፤ ‹‹አንዱን ለመወንጀል ሌላውን [ለማመስገን] አልጠቀምባቸውም›› ብለዋል፡፡
የጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ሙሉ አስተያየት ከታች ባለው ቪዲዮ ላይ ይመልከቱ፡፡
——
Watch Video below
*************
ተዛማጅ፡-
* ማሌሊት መሠረታዊ ወታደራዊ ለውጥ አምጥቷል – ጄኔራል ጻድቃን [Video]
* [Video] ጄኔራል ጻድቃን – የዕርዳታ ገንዘብ ከሕዝብ ቀምተን ለመሣሪያ ስናውል አላውቅም
* በሽረ ጦርነት ዋዜማ ሻዕቢያ ተስፋ ቆርጦ ነበር – ጄኔራል ጻድቃን [+Video]
* ከቀድሞ ሠራዊት ‹‹ክሬም›› የሆነውን ክፍል እንዲቀጥል አድርገናል – ጄኔራል ጻድቃን [+Video]
general sel EPLF singeru betam neew yemigeremew please le hezebo liwashu yechelalu le TPLF tagayoch gen be fetsum liwashu achelum gen weshet lemdot newenna be tsoronna tornet erso yemerut tornet elkitun men neber yalut resaw ethiopawi etiopiawi yeshet neber neew yalut aye general megemeria lezia serawo hezbon yekerta yetyku le “egri mekel elkit”
á¨áá«á á¶ááá½,,,, á¨ááááµ á á«áá½áá á á¨á¶á»á áá²á«áá¨ááµááá± ,,ááá á áµááá¹ á³á á¡
General Tsadikan, he is positive thinker I have respect to him.