አባይ ፀሐዬ – ‘ልክ እናስገባችዋለን’ የተባለች ቃል ከየት እንደተወሰደች አላቃትም’ (ጽሑፍና ቪዲዮ)

ክቡር አቶ አባይ ፀሐዬ የህ.ወ.ሓ.ት/ኢህአዴግ መስራች አባል ታጋይና በአሁኑ ግዜ በሚኒስትር ማአርግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማእከል ዋና ዳይርክተር ናቸው፡፡

ከጋዜጠኛ ዘርአይ ሀ/ማርያም በኦህዴድ ታሪክና የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳዮች ቆይታ አድርገዋል፡፡

ሙሉ ቃለ-ምልልሱ ከዚህ በታች በጽሑፍ የቀረበ ሲሆን፤ ቪዲዮውን ደግሞ ከታች መመልከት ይችላሉ፡፡

——

ዘርአይ ኃ/ማርያም:- በትጥቅ ትግሉ ዘመን ኦህዴድ የኢህአዴግ አንድ አባል ድርጅት ሆኖ መቆሙ የነበረው ፋይዳ ምን ነበር?

አቶ አባይ ፀሐዬ፡- የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ አንድ የኢህአዴግ አባል ድርጅት ሆኖ መደራጀቱ በመጋቢት 1982 ዓ.ም ፋይዳው ከዛ በፊት የኦሮሞ ህዝብ በዴሞክራሲያዊ አላማ ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝብ አስተሳስሮ የሚያታግለውና የሚመራው ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በማጣቱ የተፈጠረ ድርጅት ነው፡፡ ከዛ በፊት የነበረ የኦሮሞ ህዝብ ትግል የብሄር ጭቆናው የሌላው በደልንም ከተጀመረበት /ከተፈጠረበት ግዜ ጀምሮ ሲታገል የቆየ ህዝብ ነው፡፡ በብሄራዊ መብቱም ለአጠቃላይ የኢኮኖሚያዊና ዴሞክራሲያዊ አጠቃላይ መብትም፡፡ ግን ከዛ በፊት የነበሩ ድርጅቶች የተለያዩ በኦሮሞ ህዝብ ስም የተደራጁ ድርጅቶች ቢኖሩም አንደኛ ጠንካራ የህዝብ ድጋፍ እና ጠንካራ የህዝብ ማደራጀት ስራ አልነበረባቸውም፡፡

ወደ ህዝብ ገብተው ህዝቡን አደራጅተው ከህዝቡ ጋር ሆኖ የህዝቡን ስሜት አዳምጠው ሀይል የፈጠሩ አቅም የፈጠሩ ጠንካራ ድርጅቶች ጠንካራ የትጥቅ ትግል ሰራዊት የፈጠሩ አልነበሩም፡፡ ስለዚህ እየተደነቃቀፉ እየተኳላሹ ወደ አጎራባች ሀገሮች ወጣገባ እያሉ ነው ግዚያቸውን ያሳለፉትበአብዛኛው፡፡

ሁለተኛ መላውን የአማራ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝብ እንደጠላት የሚወስዱ ናቸው የነበሩ፡፡ ይህ ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትና ጥያቄ አልነበረም፡፡ የህዝቡ ጥያቄ የፖለቲካ ዲሞክራሲ የማንነትና የኢኮኖሚ እንዲሁም የእኩልነትና ፍትሕ ጥያቄዎች ነው የነበሩት፡፡ ስለዚህ በጊዜው የተፈጠሩ ድርጅቶች የኦሮሞ ህዝብ መሰረታዊ የዴሞክራሲና የልማት /ኢኮኖሚ ጥያቄዎች የሚያስከብሩም የሚያከብሩም አልነበሩም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ከሁሉም ህዝብ የሚያጋጩ ነው እንጂ፡፡Minister Abay Tsehaye and journo Zeray Hailemariam

ስለዚህ የደርግ አቅም በሰሜን ማለትም በትግራይና በአማራ ህዝብ ትግል እይተዳከመ ሲመጣ በሌላ አካባቢም ህዝቡ ማለትም የደቡብ ህዝቦች የሶማልያ ጋምቤላ ቤንሻንጉል አፋር ሁሉም ሲታገሉ ስለነበረ የኦሮሞ ህዝብ ያልተካተተበት፣ የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከስሜን ትግል ካልተቀናጀ ችግር ይፈጥራል ደርግ ቢወድቅም፡፡ ደርግ ለመጣልም ይህ ድርጅት ቢቀናጅ ነው የሚሻለው በሚል ነው ኦህዴድ የተፈጠረው ፡፡እና ይህን የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ የኦሮሞ ህዝብ የዴሞክራሲያዊ ድርጅት መፈጠር ጥያቄ የመለስ ለኢትዮጵያ የህዝቦች አንድነት ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ መፈጠር ምላሽ የሚሰጥ ትግሉም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተሻለ እንዲቀናጅ እና ከደርግ ውድቀት በኋላም የተሻለ የሽግግር መንግስት የተሳካ እንዲሆን ትልቅ አስተዋጽኦ የነበረው ድርጅት ነው ኦህዴድ፡፡

እንግዲህ የኦህዴድ መፈጠር የተጫወተው ሚና ምንድን ነው 1ኛ- በደርግ ውድቀት ዋዜማ እንግዲህ በግንቦት 20/83 ዓ.ም ነው ደርግ የተወገደው፡፡ መጋቢት 1983 ዓ.ም ደግሞ ኦህዴድ ተፈጥረዋል፡፡ በዚህ አንድ አመት ከምናምን ግዚያት ውስጥ የኦህዴድ አመራር አባላት ከፊሎቹ ኢህአዴግ ውስጥ የነበሩ አሁን ብአዴን የምንለው ደኢህድን ውስጥ የነበሩ ነው፡፡ ሌሎች ደግሞ በርካታ በኋላ የተቀላቀሉ ናቸው እና ይህ ሓይል መፈጠሩ የኦሮሞ ህዝብ በወለጋ፣ ሰላሌ፣ ደራ ፣ፍቼም አካባቢያለው የኦሮሞ ህዝብ በትግሉ እንዲሳተፍ እንዲሁም በደርግ መደምሰስ የመጨረሻ ርብርብ ላይ እንዲሳተፍ ሰራዊት ፈጥሮ እስከ አምስት ሺ የሚሆን (5000) የሚሆን ሰራዊት ማለት ነው ፣ ፈጥረው ሰራዊት አሰልፎ ጦርነት ውስጥ በመሳተፍ ጦርነት ላይ ከመሳተፍ በላይ ደግሞ የወለጋ ፣ ደራ ፣ ሰላሌና ፍቼ ህዝብ በማደራጀት ዓላማውን በማስረዳት የሰላምና መረጋጋት ስራ በመፈጠር ትልቅ አስተዋጽኦ ነው ያደረገው፡፡ በዛ ገና በህፃን እድሜያቸው ማለት ነው፡፡

ሁለተኛው የኢህአዴግ ተሳስሮ የኢህአደግ አባል ድርጅት ሆኖ መፈጠራቸው ጠቀማቸው፡፡ የኢህአደግ የትግል ተሞኩሮ ጠቀማቸው፡፡ እንዴት ሰራዊት ያደራጃሉ ህዝብ እንዴት ይደራጃል እንደሌሎቹ ከዛ በፊት የነበሩ የኦሮሞ ህዝብ ጥቅም እናስከብራለን የሚሉ ድርጅቶች በአንድ ጠባብ የሆነ አካባቢ ላይ ታጥሮ አልቀሩም፡፡ ኢህአደግ ሰፊ ነፃ ያወጣው መሬት አለ፡፡ ትግራይና አማራ ክልል ኢህአደግ የፈጠረው ትልቅ ሰራዊት የፖለቲካ አቋሞች የፖለቲካ አስተሳሰቦች ሰፊ ልምድ አለ ይህን ሰፊ አቅምና ልምድ ይዞ ስራ ጀመረ ጠቀማቸው ሰሜን ላይ ከዲህአዴግ ሆኖ ስለጀመሩ እንቅስቃሴያቸው በዛ አካባቢ ስራ ጀመሩ ቶሎ የጠላት ጥቃት /አደጋ እንዳይደርስባቸው ኢህአዴግ አገዘ) የተሻለ ልምድና አቅም ይህ እንደጀመሩ እገዛ ፖለቲካዊ አመለካከት ለኢትዮጵያ የህዝቦች አንድነት በሳልና ዴሞክራሲያዊ አመለካከት ይዞ እንዲጀምሩ አስቻላቸው፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ቶሎ የጠነከሩ፡፡

ከደርግ ውድቀት በኋላም የተጫወቱት ትልቅ ሚና አለ አንደኛ ያኔ የሽግግር ወቅት ሁሉም ፀረ ደርግ ሐይሎች የሚሳተፉበት የሽግግር መንግስት እንመስርት ብሎ ኢህአደግ ጥሪ ሲያደርግ ለሁሉም ኦነግ ጭምር ተሳትፈዋል፡፡ አምስቱም ሌሎች የኦሮሞ ህዝብ እንወክላለን የሚሉ ድርጅቶችም እንዲሳተፉ ነው የተደረገው፡፡ ሁሉም ነው የተቀበለው ኢህአደግ፡፡ ኦህዴድ አለ ከኔ ይበቃኛል አላለም እንዳውም የበለጠ ቦታ የተሰጠው ከኦህዴድ ይልቅ ለኦነግ ነው፡፡ በሽግግር ወቅት የምክር ቤት ቦታ የሚኒስትሮች ቦታም ትልቅ ወንበር የተሰጠው ኦነግ ነው፡፡ ለምን ቢባል የኦሮሞ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር አንድነት ሊመሰርት አዲስትዋ ኢትዮጵያ አብረን እንመስርት የሚል አቋም እንድንወስድ እነ ኦነግም ሌሎችም ሲያራምዱት የነበሩ አቋም ጠባብ አስተሳሰብ ለኦሮሞ ህዝብ እንደማይጠቅመው እንዲረዳ ነበር የኢህአደግ ጭንቀቱና ልፋቱ ፡፡በዚህ ዙሪያ ኦህዴድ ያኔ በህፃንነቱ በትንሽ እድሜውና አቅሙ ከኦነግ ተወዳድሮበ ኦሮምያ ህዝብ በራሱ በሁለቱም እግሩ ቆሞ ዴሞክራሲያዊ አንድነት በእኩልነትና ፍላጎት የተመሰረተች የህዝቦች አንድነት ያላት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ናት የምትጠቅመን እንጂ መገንጠል አይጠቅምም ብሎ ከኦነግም ከሌሎች ጠባብ ድርጅች ለመወዳደር እና ህዝቡን ለማሳመን ቻለ ፡፡

ይህ ትግል ሲያደርግ ከኦነግ ሲደርስበት የነበረ ግድያ ፣ ድብደባ ፣ እንግልት ፣ የደጋፊዎቹ መጨፍጨፍ በደል ተቋቁሞ በትእግስት ወደ ጦርነት እንዳንሄድ በኦህዴድም በኢህአዲግ አቋም ተወስዶ በትእግስት ቢፈልግ ኦነግ ይግደላቸው ይስቅላቸው አካላቸው ያጉድላቸው አባላቶቻችን ደጋፊዎቻችን እኛ በሰላምና የሰላም ኃይል መሆናችን የዲሞክራሲ ኃይል መሆናችን ለኦሮሞ ህዝብ ፍርዱን ትተን የኦሮሞ ህዝብ ራሱ ይፈርደናል፡፡ የሚጠቅመውም የማይጠቅመውም ራሱ ይለያል፡፡ የሚያዋጣውና የማያዋጣው የቱ እንደሆነ ራሱ ያውቃል በሚል በከፍተኛ ትእግስት በከፍተኛ የህዝብ ወገንተኝነት የኢህአደግ ጋር ሆኖ የኦሮሞን ህዝብ መብትና ጥቅም ራሱ የኦሮሞ ህዝብ እንዲወስንና እንዲረዳ ተረድቶም ኦነግ የሚያዋጣው ከሆነ ኦህዴድ/ኢህአደግ እንደሚያዋጣው የኢትዮጵያ አንድነት በፍላጎትና በእኩልነት ሲመሰረት እንደሚጠቅመው እንዲረዳና ይህ ተረድቶም አቋም እንዲይዝ ኦህዴድ ትልቅ ሚና የተጫወተ ከእድሜው በላይ እና ከነበረው አቅም በላይ የሆነ ትልቅና ቁልፍ ሚና ለዴሞክራሲያዊ አንድነትና ለኢትዮጵያ ህዝቦች አንድነት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገ ድርጅት ነው ኦህዴድ፡፡

ዘርአይ ኃ/ማርያም:- ኦህዴድ በኢትዮጵያ የልማትና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ የተጫወተውን ሚና/ጥረት እንዴት ይገልጹታል?

አቶ አባይ ፀሐዬ፡- ህገመንግስቱ ረቆ በህዝቦች ተሳትፎ በምርጫ ኢህአደግ የሚመራው መንግስት ሲቋቋም ደግሞ እስከአሁን ድረስ የኦሮሞን ህዝብ ይህን ያስፈልገዋል ይህን መብት ተረግጠዋል የሚሉት በሙሉ ኦነግም ሌሎችም ድርጅቶች የሚያነሱት ጥያቄ በሙሉ ኦህዴድ ሳይታክት ምላሽ እንዲያገኙ እና ከዛ ባሻገር እንዲሄዱ ነው ኦህዴድ ትልቅ ሚና የተጫወተው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ባህልና ታሪክ ተከብረዋል፡፡ ኦሮሚፋ ቋንቋ የስራ ቋንቋ እንዲሆን የት/ት ቤት ቋንቋ እንዲሆን ተደርገዋል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ የነበረው የተነጠቀው መሬቱ ምርቱ የራሱ እንዲሆንና የግብርናው የኑሮው ማሻሻያ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ኦሮምያ እየለማ ነው የኦሮሞ ገጠር በኦሮምያ ውስጥ ሰፊ ኢንቨስትመንት ሰፊ የኢንዱስትሪና የከተማ እድገት ሰፊ የመሰረተ ልማትና ሌሎች የልማት አውታሮች እንዲከናወን ኦህዴድ ከኢህአዴግ ጋር ሆኖ ትልቅ ድርሻ ተጫውተዋል፡፡ ኦህዴድ በኦሮምያ ውስጥ የኦነግና የሌሎች ጠባብ ሓይሎች ፀረ ሰላም ሓይሎች እንቅስቃሴ ከህዘብ ጋር ሆኖ በመመከት የተረጋጋ ሰላም እንዲኖር ለልማት ለዴሞክራሲያዊ አንድነት እንዲቆም የኦሮምያ ህዝብ ማድረግ ችለዋል፡፡

በዚህ መሰረት በሀገር አቀፍ ለተፈጠረው ልማት አስተማማኝ ሰላም ዴሞክራሲያዊ አንድነትም በኦሮምያ ለተበፈጠረው የኦሮምያ ህዝብም ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች የመብት የዴሞክራሲያዊ መብት ሰላም ፣ ልማት ፣ መገኘት ኦህዴድ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገ ታሪክ የስራ ሀቀኛ የኦሮሞ ሀዝብ ጥቅምና መብት ያስከበረ ለዚህም ከባድ መስዋትነት የከፈለ መራራ ትግል ያደረገ እውነተኛ የኦሮሞ ህዝብ ጥቅም አስከባሪ እና ለኢትዮጵያ ልማትና ዴሞክራሲያዊ አንድነት የቆመ ድርጅት ነው፡፡ በዚህ የጎላ አስተዋጽኦ ተጨውተዋል ብየ ነው የማምነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብም ከተግባሩ አይቶ ኦህዴድና/ኢህአዴግ ሊደግፍ የቻለው በዚህ መንግድ መምራት ስለቻለ ነው፡፡

ዘርአይ ኃ/ማርያም:- ከአዲስ አበባና አከባቢዋ ጋር ተያይዞ እርስዎ ተናገሩ “ልክ እናስገባችዋለን” በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች እየወጣ ስላለው ሁኔታ ምን ይላሉ ….የንግግርዎ ጭብጥና እውነታውስ ምን ነበር?

አቶ አባይ ፀሐዬ፡- ይህ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በአዲስ አበባ ዙርያዋ ያሉ ከተሞች ሲነደፍ ይሁን ተግባራዊ እንዲሆን ሲታሰብ በቅርቡ የተዘጋጀ ፣ የረቀቀ ማስተር ፕላን ከአዲስ አበባ ዙሪያዋ ያሉት የኦሮምያ ልዩ ዞን ጋር ተሳስሮ እንዲሰራ ነው የተስማሙ /ማስተር ፕላኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የኦሮምያ ክልላዊ መንግስት አስተዳደር ሁለቱም ተስማምቶ ነው የጀመሩት፡፡

እና እንዳልከው አሁን እኔ ያልተናገርኩት ነገር አባይ ተናግረዋል የሚል በማህበራዊ ድህረገጾች ብዙ ሲሰራጭ እንደነበረ ሰምቼአለሁ፡፡ ውሸት ነው፡፡ ህዝቡም ያውቃል ብየ ነው የተውኩት፡፡ ምንድነው “ልክ እናስገባችዋለን” ብለዋል የተባለች ቃልዋ ከየት እንደተወሰደች አላቃትም፡፡ ለብቻዋ ቃልዋ ተደጋግሞ እንደምትነገርና በኦሮሞ ህዝብ ላይ ፣ በኦሮሞ መስተዳድር ላይ የተሰነዘረ ሓይል ቃል አይነት አድርጎ ነው የሚያሰራጩት ያሉት የሰማሁት፡፡ ይህ ነገር ፍፁም ውሸት ነው፡፡

ለምንድ ነው ውሸት የሚሆነው 1ኛ የተናገርኩት ነገር የኢትዮጵያ ከተሞች አማራሮች ስልጠና ስንሰጥ ነበረ፡፡ እዚህ ላይ ስለዚህ ጉዳይ ተነስቶ ነበረ፡፡ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ከሌሎች የኦሮምያ ልዩ ዞኖች ጋር ተሳስሮ ነው የሚሰራ ያለና ከዚህ ተሳስሮ በዚህ ምክንያት የተፈጠረ ግርግር ነበር፡፡ እንዴት ነው የተፈጠረው ማለት ተጠያቂ ማን ነው? ለምንድን የተከሰተው? የሚል ጥያቄ ተጠይቆ ነበር፡፡ እዛ ላይ የሰጠሁት ማብራሪያ የንግግሬ ጭብጥ በዚህ በሚሰጥህ ኦርጅናል ሲዲ ታዩታላችሁ መጀመሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኩማ ናቸው፡፡ አቶ ኩማ የኦህዴድ ሊቀመንበርና የመጀመሪያ የኦሮሞ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ዋናው መሪና ለኦሮሞ ህዝብም ጥቅም ጠበቃ ሆኖ የተከራከረ መሪ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆኖ ሲከራከር ከኦሮምያ መስተዳደር ጋር /በጋራ ተመካከሩ ማለት አዲስ አበባ ስታድግ በዙርያዋ ያሉ የኦሮምያ ገጠሮችና ከተሞች ሊጠቀሙ ይችላሉ/፡፡ አትክልትና ጥራጥሬ በማቅረብ ውሃ በጋራ በመጠቀም ትራንስፖርት እና ሌሎች የልማት አውታሮች እና ትልቅ እድል ነው ይህን ማስተር ፕላን አዲስ አበባ የሚያክል ትልቅ ሀብት ያላት ከተማ በአከካባቢያችን መኖሩና ማስተር ፕላኑ መነደፉ በዚህ መልኩ ሌሎች ሀገራት የሚጠቀሙበት አሰራር ነው፡፡ ውሃ ከአካባቢው ከተማ በማስተር ፕላን /መለስተኛ ገጠርና ከተሞች/ በማስተሳሰር በልማት ስለሆነ በዚህ መንገድ እንስራው ተባብሎ ተስማምቶ ነው ስራው የጀመሩት፡፡ ከዚህ በኋላ ተስማምቶ የጋራ አስተባባሪ ኮሚቴ /Stream Committee/ የሚባለው ከኦሮምያ ክልል መንግስት ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርም እኩል ከሁለቱም ካብኔ አባላት የተውጣጣ ኮሚቴ ነው ያቋቋሙት፡፡

ስራውም በሙሉ በዚህ ኮሚቴ ሲመራ ነበረ፡፡ በኋላ ወደ ማለቁ ሲሄድ እታች ያሉ የአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ አንድ አንድ ከተሞች አስተዳደሮች ምናልባት አልገባቸውም ሊሆን ይችላል ወይም አንድ አንድ ጥርጣሬ ነበሩባቸው ፣ ጥያቄ ነበሩባቸው፡፡ ከዛ በኋላም በአንድ አንድ ተቋዋሚ ሓይሎችም ወሬ ማናፈስ ጀመሩ፡፡ ይህ አዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞች ወደ አዲስ አበባ መሬት ለማካለል ነው እንጂ አዲስ አበባ ዙሪያዋ ያሉ ከተማና ገጠር ለመጥቀም አይደለም የሚል ወሬ ተናፈሰና እረ ባካቹህ ቶሎ ህዝቡን እናወያየው ይህ ጉዳይ በሚል ብዙ ውይይት ተደረገ ከአስተዳደር አካላት ውይይት ላይ በጣም መግባባት ተፈጥሮ ነበረ፡፡ ወደ ህዝብ ማውረድና ይፋ ማድረግ ነገሩ ላይ ግን ዘገየ እና ይህን ነው የገለጽኩት፡፡ አሁንም ህዝቡም የኦሮምያ ክልል መስተዳድርም ሲያስረዳ ነገሩ እኮ እንዲህ ነው የኦሮሞ ህዝብ የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳ አይደለም ሲባል ህዝቡ ደግሞ አላስረዳቹህንም ፣ ዘገያችሁ ብሎ ሳይገባው እንደተንቀሳቀሰ ነው፡፡

የዩኒቨርስቲ ተማሪው ብዙ ማብራሪያ የሰጠው እንዲህ ነው፡፡ ያኔ ንግግሬ በሙሉ ቢፈተሽ “ልክ እናስገባችዋለን” የምትል ቃል ጭራሽ የለችም፡፡ አንድ አንዴም ምን ሰምቼ ነበረ “ወደዱም ጠሉም” ተግባራዊ ይሆናል የሚል ይህ ቃልም የለም፡፡ አላልኩም፡፡ አስተዳደሮች እስኪወያዩበት ነው የዘገየው በመዘግየቱ ምክንያት ወደህዝብ አልወረደም፡፡ ህዝቡም አልተወያየበትም የህዝብ ተቋውሞም ምንም የለም ስራ ማስተርፕላኑ በነኝህ የአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ገጠሮችና ከተሞች ህዝብ አንዳችም ተቃውሞ የለምውም፡፡

ስለዚህ ችግሩ የነበረው መረጃው ያልነበረባቸው የተወሰኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ተቋዋሚዎች ያደረጉት ቅስቀሳ አንድ አንድ የአስተዳደር አካላት በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ነገሩ ሳይገባቸው ጥርጣሬ ስለነበረባቸው እና እነሱን ለማስረዳት ግዜ ስለወሰደ ብቻ ነው ግርግሩ የተከሰተው፡፡ ይህ ኦርጂናል ሲዲ (ያኔ የተናገርኩት) እንዳለ ብታሰራጩት ደስ ይለኛል፡፡ ከየት እንደተቆረጠ ይህ ቃል ልክ እናስገባችዋለን የሚል አላቅም፡፡ ለጣላቶች የተነገረ ከሆነ ለሻአብያ ፣ኦነግ ፣ኦብነግ ከሆነ አላቅም እንግዲህ፡፡ እንዲህ አይነት ቃል በፍፁም አልተናገርኩም ሐሰት ነው ይቅርና ህዝብ ላይ በግለሰብም ላይም እንዲህ አይነት ቃል የመናገር ልምድም ባህሪም የለኝም::

———

የቃለ-ምልልሱ  ቪዲዮ(ከዋልታ)

 

************

Zeray hailemariam Abebe is a scholar of International Relations and is researcher in the horn of Africa’s conflict, inter-state relations and cooperation. He blogs at HornAffairs and can be reached at [email protected]

more recommended stories