Category Archives: ሌ/ጄ ጻድቃን ገብረትንሳኤ – General Tsadkan Gebretinsae

ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ (General Tsadkan Gebretinsae) ነባር የህወሓት ታጋይ ሲሆኑ፣ ከ1971 ጀምሮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣ ማሌሊት ሲቋቋም ከመጀመሪያዎቹ 9 የፖሊት ቢሮ አባላት አንዱ የነበሩ ሲሆን እንዲሁም ከ1977 ጀምሮ እስከ1983 የህወሓት ሠራዊት ቺፍ ኦፍ ስታፍ ሆነው ታግለዋል፡፡ በ1987 ህገ-መንግስቱ ሲጸድቅ ከህወሓት አመራርነት ተሰናብተዋል፡፡

ፃድቃን ከ1983-1993 የሀገር መከላከያ ሠራዊት ኤታማጆር ሹም ሆነው የመሩ ሲሆን በ1993 በጡረታ ሲሰናበቱ በወታደራዊ ማዕረግ ሌፍተናንት ጄኔራል (ሌፍተናል ጄኔራል) ማዕረግ ደርሰው ነበር፡፡

በትምህርት ረገድ ከጆርጅ ዋሽንገተን ዩኒቨርሲቲ የዓለም ዓቀፍ ፖሊሲና ትግበራ ማስተርስ ዲግሪ፣ ከኦፕን ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አድሚኒስተሬሽን ማስተርስ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን፤ በዓለም አቀፍ ሕግ በአመስተርዳም ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሳቢያ ሳያጠናቅቁ ቀርተዋል፡፡

በተመድ አማካኝነት በደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡

[Also spelled as ሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ትንሳኤ; General Tsadkan Gebretensae, General Tsadkan Gebretinsae]

Photo-General-Tsadkan.jpg

ሌ/ጄ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ለሶሻል ሚዲያ ጥያቄዎች የሰጡት ምላሾች [Video]

ሌፍተናንት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ‹‹የሃገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦች›› በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሑፍ፤ የሀገሪቱ እና የኢሕአዴግን ያለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት ጉዞ በወፍ በረር ከቃኙ በኋላ፤ አሁን ሀገሪቱ ለገባችበት የፖለቲካ ቀውስና አደጋዎች የመፍትሔ ሀሳብ ይሆናል ያሉትን ማቅረባቸውና ፖለቲካዊ መፍትሔዎችን ለማስፈፀምም ‹‹በሀገራችን ካሉት የተለያዩ ፖለቲካዊ ፓርቲዎች ተስማምተው የሚቋቋሙት ይህንን ሂደት የሚመራ መዋቅር መፈጠር አለበት›› … Continue reading ሌ/ጄ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ለሶሻል ሚዲያ ጥያቄዎች የሰጡት ምላሾች [Video]

የሃገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦች (ሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ትንሳኤ)

(ሌተናል ጄኔራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ) መግቢያ ከሃያ አምስት ዓመት ኢህአዴግ የደርግን መንግስት በጦርነት አሸንፎ የሀገራችንን ፖለቲካዊ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ፤ ቀስ በቀስ እያደጉ የመጡ ፖለቲካዊ ችግሮች በግልፅ ጎልተው መታየት ጀምረዋል፡፡ አሁን ገዥው ፖርቲና ፖርቲው የሚመራው መንግስትም የችግሮቹን መኖር አምኖ ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ መንገር ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይህ ሁኔታ ለማንኛውም የሀገሩን ደህንነትና ሰላም፤ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ማህበራዊ ብልፅግና፤ … Continue reading የሃገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦች (ሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ትንሳኤ)

ጄኔራል ጻድቃንና ጤዛዋ ማሌሊት…በ40ኛው (በዶ/ር አረጋዊ በርኸ)

Editor’s note:በቅርቡ ከጄ/ል ጻድቃን ጋር ያደረግነውን ቃለ-መጠይቅ በተከታታይ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በቃለ-መጠይቁ ከተነሱት ርዕሰ-ጉዳዮች በተወሰኑት ላይ ዶ/ር አረጋዊ በርኸ አስተያየታቸውን ልከውልናል፡፡ዶ/ር አረጋዊ ከህወሓት መሥራቾች አንዱ ሲሆኑ እስከ1971 በሊቀመንበርነት፣ እስከ1978 ደግሞ በወታደራዊ መሪነት ያገለገሉ ሲሆን፤ የማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ(ማሌሊት) ምሥረታን ተከትሎ ከተደረገው የአመራር ሽግሽግ በኋላ ድርጅቱን ለቅቀው በአውሮፓ ነዋሪ ናቸው፡፡ ጄ/ል ጻድቃን ገ/ትንሳዔ ደግሞ ከ1971 ጀምሮ የህወሓት … Continue reading ጄኔራል ጻድቃንና ጤዛዋ ማሌሊት…በ40ኛው (በዶ/ር አረጋዊ በርኸ)

በጦርነቱ ወቅት በመሣሪያ ግዥ ላይ የመለስ ዜናዊ ተቃውሞ አገር ለመጉዳት አልነበረም – ጄ/ል ጻድቃን [+video]

የቀድሞው ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት አፈጻፀም ሂደት ላይ የነበራቸው አቋም በወቅቱ ከነበረው የጋራ አመለካከት ሊከሰት የሚገባው ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው እንጂ አገር ለመጉዳት በማሰብ አይደለም በማለት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ገለጹት፡፡ ጄኔራሉ ይህንን የተናገሩት፤ በጦርነቱ ወቅት መለስ ለጦር መሣሪያ ግዥ በሚወጣው ገንዘብ መጠን ላይ ተቃውሞ ነበራቸው የሚለውን ስሞታ በመጥቀስ ላቀረብንላቸው በሰጡት ምላሽ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን ኤርትራ … Continue reading በጦርነቱ ወቅት በመሣሪያ ግዥ ላይ የመለስ ዜናዊ ተቃውሞ አገር ለመጉዳት አልነበረም – ጄ/ል ጻድቃን [+video]

ከቀድሞ ሠራዊት ‹‹ክሬም›› የሆነውን ክፍል እንዲቀጥል አድርገናል – ጄኔራል ጻድቃን [+Video]

የደርግ ሥርዐት መገርሰስን ተከትሎ የቀድሞው ሠራዊት እንዲበተን ቢደረግም 9,000 ገደማ ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የአዲሱ መከላከያ ሠራዊት አካል ሆነው እንዲቀጥሉ መደረጉን ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ አወሱ፡፡ ሰሞኑን ከሆርን አፌይርስ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ የቀድሞውን ሠራዊት የመበተን ውሳኔ ድህረ-ምክንያት (rationale)፤ ከአብዮታዊ ለውጥ ርዕዮተ-ዓለማዊ አመለካከት እና ከሠራዊቱ የደርግን ወንጀሎች ፈጻሚ የነበረ ከመሆኑ የመነጨ መሆኑን ጄኔራሉ አብራርተዋል፡፡ የቀድሞ ሠራዊት በመሰናበቱ የተጎዳ … Continue reading ከቀድሞ ሠራዊት ‹‹ክሬም›› የሆነውን ክፍል እንዲቀጥል አድርገናል – ጄኔራል ጻድቃን [+Video]

በሽረ ጦርነት ዋዜማ ሻዕቢያ ተስፋ ቆርጦ ነበር – ጄኔራል ጻድቃን [+Video]

* የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ለሻዕቢያ አሉታዊ የሆነ አቋም ያለማቋረጥ ይይዙና ይወተውቱ ነበር * የህወሓት/ኢህአዴግ ሠራዊት አዲስ አበባ ሲገባ አብሮ የመጣው የሻዕቢያ ተዋጊ ብዛት 300 ገደማ ነበር በሕወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) የትግል ታሪክ እንደ ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጎ የሚወሰደው የ1981ዱ የሽረ ጦርነት ከመካሄዱ ጥቂት ወራት በፊት ሻዕቢያ በትጥቅ ትግሉ ስኬት ላይ ተስፋ አጥቶ እንደነበር ጄኔራል … Continue reading በሽረ ጦርነት ዋዜማ ሻዕቢያ ተስፋ ቆርጦ ነበር – ጄኔራል ጻድቃን [+Video]

[Video] ጄኔራል ጻድቃን – የዕርዳታ ገንዘብ ከሕዝብ ቀምተን ለመሣሪያ ስናውል አላውቅም

ከ1971 ጀምሮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት የህወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ‹‹እኔ የማውቀው ከደርግ ከሚገኘው ንብረት አብዛኛውን ከሕዝብ ስንካፈል እንጂ ከውጭ ለእርዳታ የመጣውን ገንዘብ ከሕዝብ ቀምተን ለጦር መሣሪያ ስናውል አይደለም›› አሉ፡፡ ጄኔራሉ ይህን ያሉት ባለፈው ሰኞ ጥር 30-2007 ባደረግንላቸው ቃለ-መጠይቅ ላይ፡- ለ1977ቱ ረሀብ የመጣው ዕርዳታ ለድርጅት ሥራ እንዲውል ተደርጓል ስለሚለው የዶ/ር አረጋዊ … Continue reading [Video] ጄኔራል ጻድቃን – የዕርዳታ ገንዘብ ከሕዝብ ቀምተን ለመሣሪያ ስናውል አላውቅም

ማሌሊት መሠረታዊ ወታደራዊ ለውጥ አምጥቷል – ጄኔራል ጻድቃን [Video]

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በትግል 10 ዓመታ ካስቆጠረ በኋላ፤ በ1977ዎቹ የፖለቲካ አመራር የሚሰጥ አደረጃጀት ማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ(ማሌሊት) በሚል ስያሜ እንደመሠረተ ይታወሳል፡፡ ያ አደረጃጀት ዓለም-አቀፋዊውን የአሰላለፍ ለውጥ ተከትሎ ከ1983 በኋላ እንዲቀር መደረጉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በአብዛኛው ሕዝብ እምብዛም አይታወቅም፡፡ ይሁን እንጂ ህወሓት ከ1970ዎቹ አጋማሽ በኋላ ላሳየው የወታደራዊ እና ድርጅታዊ እመርታ ምክንያቱ የማሌሊት ምሥረታ ያስከተለው የርዕዮተ-ዓለም … Continue reading ማሌሊት መሠረታዊ ወታደራዊ ለውጥ አምጥቷል – ጄኔራል ጻድቃን [Video]