ከቀድሞ ሠራዊት ‹‹ክሬም›› የሆነውን ክፍል እንዲቀጥል አድርገናል – ጄኔራል ጻድቃን [+Video]

የደርግ ሥርዐት መገርሰስን ተከትሎ የቀድሞው ሠራዊት እንዲበተን ቢደረግም 9,000 ገደማ ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የአዲሱ መከላከያ ሠራዊት አካል ሆነው እንዲቀጥሉ መደረጉን ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ አወሱ፡፡Photo - General Tsadkan interview

ሰሞኑን ከሆርን አፌይርስ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ የቀድሞውን ሠራዊት የመበተን ውሳኔ ድህረ-ምክንያት (rationale)፤ ከአብዮታዊ ለውጥ ርዕዮተ-ዓለማዊ አመለካከት እና ከሠራዊቱ የደርግን ወንጀሎች ፈጻሚ የነበረ ከመሆኑ የመነጨ መሆኑን ጄኔራሉ አብራርተዋል፡፡

የቀድሞ ሠራዊት በመሰናበቱ የተጎዳ ቤተሰብ እንዳለ እንዲሁም የአፈጻጸም ሂደቱን በተመለከተም የሚቀርብ ትችት ሊኖር እንደሚችል እንደሚረዱ ከጠቀሱ በኋላ ውሳኔው በመሠረቱ ግን ትክክል ነበር ብለዋል፡፡

አሁንም መለስ ብለው ሲያስቡትም፤ የቀድሞው ሠራዊት ከአዲሱ የታጋይ ሠራዊት ጋር ተቀላቅሎ ይቀጥል ቢባል ሀገር ሊከላከል የሚችል፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ዋዜማ ላይ የነበረውን ሠራዊት ያህል ብቃት ያለው ሠራዊት አይሆንም ነበር፡፡ ይልቁንም የተለያዬ የፖለቲካ ሀይሎች የሚጎትቱት ሀይል ይሆን ነበር ብለዋል፡፡ በሌላ ሀገር ሄደው ያጋጠማቸውም ተሞክሮ ያንን አመለካከት እንዳጠናከረላቸው ነው የጠቆሙት፡፡

ይሁን እንጂ ከቀድሞ ሠራዊት ‹‹ክሬም›› የሆነውን ክፍል ወደአዲሱ ሠራዊት እንዲመለስ መደረጉን ጠቅሰው፤ ይህ ተቺዎች የሚዘሉት ሀቅ ነው ብለዋል ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ፡፡

የሽግግር መንግስቱ ሠራዊት ቺፍ ኦፍ ስታፍ የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን፤ ከቀድሞ ሠራዊት አባላት መሀል ከደህንነት እና ከኢሠፓ መዋቅር ግንኙነት ያልነበራቸው፣ ራሺያ ሄደው የሰለጠኑ፣ 9,000 ወታደራዊ ኤክስፐርቶች – 7,000 ከእግረኛ እና 2,000 ከአየር ሀይል – በአዲሱ ሠራዊት እንዲቀጥሉ ተደርጓል ብለዋል፡፡

በ1983 የህወሓት ታጋዮች ብዛት 85 ሺህ ገደማ የነበረ ሲሆን አዲሱ ሀገራዊ ሠራዊት ሲደራጅ ከ32-35ሺህ የሚሆኑት እንደተሰናበቱም አስታውሰዋል፡፡

የስልጠና፣ የጥናት እና ምርምር እና የሎጂስቲክ ሥራዎችን ሲመሩልን እና መልክ ሲያስይዙልን የነበሩት ከቀድሞ ሠራዊት የተመለሱት ወታደራዊ ኤክስፐርቶች ናቸው ብለዋል፡፡ ይህም በሠራዊት ግንባታ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሥራ ነው ብለዋል፡፡ በተለይም እስከ 1989 ድረስ በተከናወነው የ7 ሜካናይዝድ ብርጌድ ስልጠናና ማደራጀትም ትልቅ አስተዋጽኦ የነበራቸው የቀድሞ ሠራዊት አባላት የነበሩ ኮሎኔሎች እንደነበሩ አውስተዋል፡፡ እንዲያውም ለነሱ በተሰጠው ሚና ሳቢያም አንዳንድ ነባር ታጋዮች እኛ እየተገፋን ነው የሚል ቅሬታ አቅርበው እንደነበርም እና ያንን ለማጥራት ኮንፍረንስ መካሄዱን አስታውሰዋል፡፡

የጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ሙሉ አስተያየት ከታች ባለው ቪዲዮ ላይ ይመልከቱ፡፡

——

Watch Video below.

*************

ተዛማጅ፡-
*
ማሌሊት መሠረታዊ ወታደራዊ ለውጥ አምጥቷል – ጄኔራል ጻድቃን [Video]

* [Video] ጄኔራል ጻድቃን – የዕርዳታ ገንዘብ ከሕዝብ ቀምተን ለመሣሪያ ስናውል አላውቅም

* በሽረ ጦርነት ዋዜማ ሻዕቢያ ተስፋ ቆርጦ ነበር – ጄኔራል ጻድቃን [+Video]

Daniel Berhane

more recommended stories