All posts by Jossy Romanat

Jossy Romanat

የወልቃይት ጥያቄና የፕሮፌሰር መስፍን ክሽፈት

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ሰሞኑን ወልቃይትን በተመለከተ ኣንድ ጽሁፍ ለጥፈዋል፡፡ ጽሁፉ ኣጭር ቢሆንም እንደተለመደው ክህደትና ትእቢት የተቀላቀለበት ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ የሚጋጩ ሃሳቦችንም ያካተተ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ወትሮው የሳቸውን ሃሳብ እንደወረደ ሲያራግቡ የነበሩ ተከታዮቻቸው ሲያራግቡት ኣልታየም፡፡ ጽሁፉ “ወልቃይት የማን ነው? የሚለው ጥያቄ ትክከል ኣይደለም፣የማይረባና መጥፎ ጥያቄ ነው” ብሎ ይጀምርና ጥያቄው መጥፎ መሆኑን ለማስረዳት የቀረበው መከራከሪያ ደግሞ … Continue reading የወልቃይት ጥያቄና የፕሮፌሰር መስፍን ክሽፈት

የኢትዮጵያ መንግስትና “ኣርበኛዊ” ዲፕሎማሲ (እርምጃ)

በሳውዲ፣ የመን፣ ደቡብ ኣፍሪካና ሊብያ በኢትዮጵያውያን ላይ ችግር ባጋጠመ ጊዜ በቦታው የሌሉ ብዙ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግስት በነዛ ኣገራትና ቡድኖች ላይ እንዲወስደው የሚጠብቁት እርምጃ ኣርበኛዊ እርምጃ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ ጥሎበት (በባህሪው) ኣርበኛዊ ዲፕሎማሲ ኣያራምድም፡፡ ቢያንስ መንግስት በኣንዳንድ ወገኖች የሚነሳበትን የ”ወኔ-ቢስነት” ክስ ለመከላከልና ለዜጎቹ እንደሚቆረቆር ለማሳየት ያክል እንኳን (ባያደርገዉም) በቴሊቪዥን ብቅ ብሎ ዘራፍና ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት … Continue reading የኢትዮጵያ መንግስትና “ኣርበኛዊ” ዲፕሎማሲ (እርምጃ)

የኢህኣዴግ ፖሊሲዎች Vs የማስፈፀምና የኣቅም ችግር

ዞሮ ዞሮ ግን የማስፈፀም ስራው ብዙ ከተጓዘና ችግር ከተፈጠረ በኋላ “ግምገማ” ያካሂዱና ያ “ፀረ-ልማት” ያሉት ሰውዬ የነገራቸውን ነገር ትልቅ ችግር እንደነበረ በግምገማ ማረጋገጣቸውን ይነግሩንና ጉዞው ይቀጥላል፡፡

የሶስት ጓደኞች ኣለም – ኢትዮጵያ

(Jossy Romanat) እኔ፣ መስፍንና ካሕሳይ ጓደኛሞች ነን፡፡ ብዙ ጊዜ ኣብረን እናሳልፋለን፡፡ በብዙ የኣለም ፖለቲካና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ እንስማማለን – በቢራ ምርጫችንም እንዲሁ፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክና ፖለቲካ በተመለከተ ግን ብዙ ልዩነት ኣለን፡፡ ከማንስማማባቸው ጉዳዮች ኣንዱ ለቀድሞዎቹ ኣፄዎች ያለን ኣመለካከት ነው – ‘ኣፄኣዊ’ እይታችን የተለያየ ነው፡፡ የመስፍን እይታ – መስፍኔ የዲሞክራሲና ሰብኣዊ መብት ተከራካሪ ነው (ራሱን “ኣክቲቪስት” እያለ … Continue reading የሶስት ጓደኞች ኣለም – ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያዊነትና የኢህኣዴግ የብሄር ፖለቲካ

(ጆሲ ሮማናት) ኢህኣዴግ ስልጣን በያዘበት ሰኣት ኢትዮጵያ ውስጥ ብሄርን መሰረት ያደረገ ፖለቲካዊ መፍትሄ መስጠቱ ትክክል ነው ብቻ ሳይሆን ሌላ ኣማራጭ ኣልነበረም፡፡ የተለያዩ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለዘመናት ሲደርስባቸው የነበረው ጭቆና ብሃራቸውንና ሃይማኖታቸውን መሰረት ያደረገ ነበር፡፡ የሃይማት ጭቆናው መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ እንዲሆኑ በማድረግ ሃገሪቱ ማንኛውን ሃይማኖት በእኩል ኣይን ማስተናገድ የምትችልበት ስርኣት በመፍጠር ተፈቷል፡፡ በተመሳሳይም ብሄሮችና ብሄረሰቦች ሁሉም በእኩል … Continue reading ኢትዮጵያዊነትና የኢህኣዴግ የብሄር ፖለቲካ

ለበእውቀቱ ስዩም:-እውን የድሮው ኢትዮጵያዊነት የመዋጮ ነበርን?

(ጆሲ ሮማናት) በእውቀቱ ስዩም ኢትዮጵያ የብሄርተኝነት ሃይማኖት ክፉኛ ያሰጋታል ይለናል፡፡ ሰሞኑን ጃዋር መሃመድንና ሌሎች “ብሄርተኛ” ብሎ የፈረጃቸውን መልሶ ለመሞገት “የዘመኑ መንፈስ” ብሎ በጻፈው ጽሁፍ የዘመኑ “ታሪክ ከላሾች” እንደሚሉት ኣሁን የምናያት ኢትዮጵያ “በኣማራ ባህላዊ ስርጭት እና በኣማራ ፖለቲካ የተገነባች” ሳትሆን የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች ግንኙነት ስብጥር ነች ይከራከራል ፡፡ የኢትዮጵያ ኣገራዊ ማንነት መገለጫ የኣማራ ባህላዊ ማንነት ሳይሆን … Continue reading ለበእውቀቱ ስዩም:-እውን የድሮው ኢትዮጵያዊነት የመዋጮ ነበርን?

የዲያስፖራ “ኣርበኞች” [Amharic]

ብዙ ጊዜና ገንዘብ ኣውጥቼ ሰራሁት ያለውንና “ፌዝ-ራሊዝም” ብሎ የሰየመውን ፊልም በኢሳት ቴሌቪዥን ጋብዞን ነበር፡፡ የትግራይ ተወላጆች የሆኑና በተለያዩ የፌዴራል መንግስትና የመከላከያ ሰራዊት ያሉ ሃላፊዎችን (ተጋሩ ያልሆኑትንም እየጨመረ) ስምና ምስል ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በመቅዳት ያሳየው ይሄ “የምርምር ግኝት” ማጠቃለያው ‘ኢትዮጵያ ውስጥ ፌዴራሊዝም የለም ፌዝ-ራሊዝም ነው ምክንያቱም ስልጣኑን የያዙት “ትግሬዎች” ናቸው የሚል ነው፡፡ በርግጥ እነ ታማኝ ስለ ፌዴራሊዝም ማውራት መጀመራቸው በራሱ ትልቅ ለውጥ ቢሆንም ፅንሰ ሃሳቡ የገባው ኣልመሰለኝም፡፡

የኣቶ መለስ እረፍትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ

ኣቶ መለስ ከሞቱ ኣራት ወር ሆኗቸዋል፡፡ የኣቶ መለስን እረፍት ተከትሎ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የታየው ለውጥና የኣቶ መለስ ኣመራር ትሩፋቶች (legacies) ምን ይመስላሉ? ኣቶ መለስ በድርጅታቸው በኢህኣዴግና በመንግስት ጉዳዮች ላይ የነበራቸው ሚና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመሄዱ ካለፉት ጥቂት ኣመታት ወዲህ በህዝቡ ዘንድ ጠቅላይ ሚኒስትሩና መንግስት የኣንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው የሚል ኣመለካከት እንዲሰርፅ ኣድርጓል፡፡ ይሄ ኣመለካከት … Continue reading የኣቶ መለስ እረፍትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ

የዲሲ ፖለቲከኞች የኋልዮሽ ጉዞ ታሪክ በጨረፍታ [Amharic]

Highlight: “የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ማህበረሰብ በሰሜን ኣሜሪካ (EHSNA) የሚባል ድርጅት ኣቋቋሙ፡፡ ዝግጅቱን የሚያቀርብበት ጊዜም ከ ESFNA ጋር በተመሳሳይ ጊዜ እንዲሆን ወሰኑ፡፡ ብርቱካንም የዝግጅቱ እንግዳ እንድትሆን ኣደረጉ -ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ፡፡ እንዲህም ኣሉን – “የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ለዘመናት ስታቀርበውና ስትታገልለት የነበረውን የብርቱካን የክብር እንግዳነት ጉዳይ ይሄው እውነተኛና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ኣሳክተውታል፡፡ ደስ ብሎናል ደስ ይበላችሁ፡፡ድል ለኛ ሞት … Continue reading የዲሲ ፖለቲከኞች የኋልዮሽ ጉዞ ታሪክ በጨረፍታ [Amharic]

ቴዲ ኣፍሮ፣ እምዬ ሚኒሊክ፣ ባልቻ ኣባነፍሶ እና ኣድናቂዎቹ !!! [Amharic]

ጆሲ ሮማናት ቴዲ ኣፍሮ ታላቅ ጥበበኛ ነው፡፡ ሙዚቃዎቹ በሃሳብ ብስለትም በዜማ ጥኡምነትም ሁሌም ቢሆን ተደምጠው የማይሰለቹ ምርጦች ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ኣርቲስቱ በርካታ ኣፍቃሪዎችን ማፍራት ችሏል፡፡ ታዲያ የቴዲ ኣፍቃሪዎች ሁሉም ኣንድ ኣይነት ኣይደሉም፡፡ የፍቅራቸው ምክንያትም ይለያያል፡፡ ቢዚህም ምክንያት ደረጃ 1 እና ደረጃ 2 ኣድናቂዎች ልንላቸው እንችላለን፡፡ ደረጃ 1 ኣድናቂዎች ስለ ኑሮ፣ ስለፍቅር፣ ስለመተሳሰብ፣ ስለጥበብ ዘፍኖ ልባቸውን … Continue reading ቴዲ ኣፍሮ፣ እምዬ ሚኒሊክ፣ ባልቻ ኣባነፍሶ እና ኣድናቂዎቹ !!! [Amharic]