ኢትዮጲያ የማን ናት:- የወጣቶች ወይስ የባለስልጣናት?

ባሳለፍነው ሳምንት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተቃውሞ ሰልፍ በወጡ ዜጎች ላይ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ ከማሳሰብ አልፎ በጣም አስጨንቆኝ ነበር። እንደ ሀገርና ሕዝብ ሕልውናችን አደጋ ላይ እየወደቀ እንደሆነ ተሰምቶኛል። በአካል ሆነ በስልክ ያገኘኋቸውን ሰዎች ስጠይቅ የነበረው፤ “ሰላማዊ ሰልፍ ስለወጣን ለምን ይገድሉናል?” እና “ለምንድነው የመንግስት ባለስልጣናት የህዝቡን ጥያቄ የማይሰሙት?” የሚሉትን ነበር። ጥያቄዎቹ እንዳስጨነቁኝ አልቀሩም፣ መልስ አገኘሁላቸው። […]

ኢህአዴግን የጠለፈው “የአመራር ወጥመድ”

ከአስር ቀን በፊት አዲስ አድማስ ጋዜጣ በመንግስት አመታዊ ሪፖርቶች ዙሪያ ያቀረበውን ዘገባ ተመልክታችኋል? ነገሩ “ስህተትን መደባበቅና ማስመሰል መደበኛ የአሰራር ስልት ሆነ እንዴ?” ያስብላል። በእርግጥ ሁሉም ባለስልጣናት ያው እንደ እኔና እናንተ “ሰው” ናቸው። እንደ ማንኛውም ሰው ስህተት ሊሰሩ ይችላሉ። ችግሩ የእኛ ባለስልጣናት እንደ አምላክ ፍፁም መሆን ይቃጣቸዋል። በስህተት ላይ ስህተት እየሰሩ፤ “ተሳስታችኋል” ሲባሉ አይሰሙም፣ “ተሳስተናል” ብለው […]

ኢህአዴግ አሸነፈም ተሸነፈም ለውጥ አይመጣም

ሀገራችን ኢትዮጲያ ወደፊት ወይም ወደኋላ በሚወስድ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች። የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በኪራይ ሰብሳቢዎች ታግቷል፣ የመንግስት መዋቅር በኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስና ተተብትቧል፣ ህዝቡ በዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር እጦት ተማሯል። ችግሮቹ በዋናነት በፖለቲካ አመራሩ ብቃት-ማነስ ምክንያት የተፈጠሩና የተባባሱ ናቸው። በሌላ በኩል፣ ችግሮቹ በፖለቲካ አስተዳደር ስርዓቱ ውስጥ ግልፅነትና ተጠያቂነት በማስፈንና የአመራሩን አቅም በማጎልበት የሚፈቱ ናቸው። ስለዚህ፣ የችግሮቹ መንስዔና መፍትሄ […]

አስቴር ማሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ ተሾሙ

(ባሃሩ  ይድነቃቸው) ወ/ሮ አስቴር ማሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የመልካም አስተዳደር ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር በመሆን ተሾሙ። የወይዘሮ አስቴር ማሞን ሹመት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም  ደሳለኝ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው አስፀድቀዋል። ምክር ቤቱም  ሹመቱን በሙሉ  ድምፅ  ያፀደቀ  ሲሆን፥  ወይዘሮ አስቴር  ማሞም በምክር ቤቱ  ፊት ቃለ መሃላ  ፈፅመዋል። ወይዘሮ አስቴር የመጀመሪያ  ድግሪያቸውን […]

ሚኒስተር መላኩ ፈንታ በሙስና ተጠርጥረው ታሠሩ [የመግለጫው ሙሉ ቃል]

ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የፌዴራል የስነ ምግባር ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተሰጠ የዜና መግለጫ በዛሬው እለት የፌዴራል የስነ ምግባር ጸረ ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚገኙባቸውን 12 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉ ኮሚሽኑ በህዝብና በመንግስት ንብረት ላይ የሚፈፀምን የሙስና ወንጀል ተከታትሎ አስፈላጊውን መረጃ በማሰባሰብ ተጠርጣሪዎችን በህግ ፊት አቅርቦ በማስጠየቅ ሙስናን የመከላከልና […]

Special Edition | Post-Meles Zenawi 2012

Special edition| Post-Meles 2012 Collection of exclusive interviews, opinion pieces and news digests covering the four moths after Meles.    ************************** *PM Hailemariam’s first 100 days  ************************** "In this digest,  a summary of outstanding developments of economic interest since late August is presented…" *Post-Meles: Economic Digest (Guesh) ************************** "Meles Zenawi, the intellectual leader of Ethiopia, […]

Sendek | የጁነዲን ሳዶ ባለቤትን ጨምሮ 29 ሰዎች በሽበርተኝነት ተከሰሱ

* የጁነዲን ባለቤት በኦሮምያ ክልል አክራሪነት እንዲስፋፋ አድርገዋል – 1.5 ሚሊዮን ብር ከ27ኛ ተከሳሽ ተቀብለዋል (በዘሪሁን ሙሉጌታ) በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌድሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)(ለ)፣ 38(1) እና የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 3(1) (2) (4) (6) እና 4 ስር የተመለከተውን ተላልፈዋል ያላቸውን 29 ሰዎችና ሁለት ድርጅቶች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቷል። ዐቃቤ ሕግ ክሱን […]