Category Archives: Human Rights

ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል-1 “የፀረ-ሽብር ሽብር”

ስለማዕከላዊ (Ma’ekelawi) እስር ቤት እና ስለቀይ-ሽብር ሲነሳ እፈራለሁ። በቃ… “ቀይ-ሽብር” ሲባል የታሪክ ጠባሳ፤ “ማዕከላዊ” ደግሞ ምድራዊ ሲዖል ስለሚመስሉኝ ስለዚያ ጉዳይ ማሰብ ራሱ ያስፈራኛል። በተለይ ጋዜጠኛ ማዕዛ ብሩ እና ገጣሚና ተርጓሚ ነብይ መኮንን በሸገር ሬድዮ ያደረጉትን ብዙ ሳምንታት የፈጀ ጭውውት እንደምንም አዳምጬ ከጨረስኩ በኋላ፣ ሌላ ተጨማሪ ነገር መስማትም ሆነ ማንበብ አልሻም ነበር። ባለፈው ሳምንት ግን እንደ … Continue reading ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል-1 “የፀረ-ሽብር ሽብር”

የአብዮት እና የዴሞክራሲ ትውልድ ግጭት

የቀድሞ የኢትዮጲያ አየር ኃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት ግንቦት ሃያን አስመልክቶ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ አነበብኩት። ከቃለ-ምልልሱ ውስጥ በእሳቸው ዘመን ትውልድና በአዲሱ ትውልድ መካከል ስላለው ልዩነት የተናገሩት ነገር በጣም ትኩረት የሚስብ ነው። ከሁሉም በላይ ግን፣ “…ኢሕአዴግ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የእኛ ትውልድ የአማፂ ትውልድ ነው። የአማፂ ትውልድ የዴሞክራሲ ትውልድ መሆን አይችልም። …ስለዚህ የእኛ ትውልድ … Continue reading የአብዮት እና የዴሞክራሲ ትውልድ ግጭት

ስልጣን ነፃነት – ነፃነት ስልጣን ነው

በተለያየ ግዜና ቦታ የሚታዩ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መሰረታዊ ዓላማና ግባቸው ምንድነው? ብዙውን ግዜ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ እንደተጠያቂው ወገን ይለያያል። የሥርዓቱ ተቃዋሚዎች የትግላቸው ዓላማ “የዜጎችን ነፃነት ለማረጋገጥ” እንደሆነ ሲጠቅሱ፣ የሥርዓቱ መሪዎች ደግሞ እንቅስቃሴው “የመንግስትን ሥልጣን በኃይል ለመጨበት” እንደሆነ ሲገልፁ መስማት የተለመደ ነው። ለምሳሌ፣ አንዳንድ የምዕራቡ ዓለም ምሁራንና ፖለቲከኞች፣ ከ2010 ዓ.ም (እ.አ.አ) ጀምሮ በአረቡ ዓለም የታየውን አብዮት … Continue reading ስልጣን ነፃነት – ነፃነት ስልጣን ነው

የደሞወዝ እድገት ቀርቶብኝ የአካዳሚክ ነፃነቴን ስጡኝ

በከፍተኛ የትምህርት ተቋም ውስጥ የ10 ዓመት የማስተማር ልምድ አለኝ። ላለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ የአንድ ት/ት ክፍል ኃላፊ ሆኜ እየሰራሁ እገኛለሁ። የማስተማር ሥራውን በጣም እወደዋለሁ። ከተማሪዎቼ ጋርም ልዩ ፍቅርና ቀረቤታ እንዳለኝ አምናለሁ። በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪ አብረውኝ የተማሩ የክፍል ጓደኞቼ አብዛኞቹ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በመምህርነት በመቀጠር ነው ወደ ስራ አለም የገቡት። ሆኖም ግን፣ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ … Continue reading የደሞወዝ እድገት ቀርቶብኝ የአካዳሚክ ነፃነቴን ስጡኝ

የአማራ ክልል መንግሥት የቅማንት ብሔረሰብንና የክልሉ ሕዝብን ይቅርታ እንዲጠይቅ ተወሰነ

(ዮሐንስ አንበርብር – ሪፖርተር ጋዜጣ) በኦሮሚያ ክልል ብጥብጥ የፀጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ ኃይል ተጠቅመዋል ተባለ ከፍተኛ ኃይል የተጠቀሙ የአማራ ክልል ልዩ ፖሊስ አባላት በሕግ እንዲጠየቁ ተወሰነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያ በርካታ ቦታዎች ተፈጥሮ የነበረውን ግጭትና ሁከት በራሱ አነሳሽነት እንዲሁም በአማራ ክልል በሰሜን ጐንደር ከቅማንት የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የቀረበለትን አቤቱታ መሠረት በማድረግ ያካሄደው የሰብዓዊ መብት … Continue reading የአማራ ክልል መንግሥት የቅማንት ብሔረሰብንና የክልሉ ሕዝብን ይቅርታ እንዲጠይቅ ተወሰነ

ነፃነት “የፈጣሪ”፣ ፍርሃት “የሰይጣን” ነው!

ነፃነት ለሰው ልጅ የተሰጠ ተፈጥሯዊ ፀጋ እንደመሆኑ፤ በነፃነት ማሰብ፣ መናገርና መፃፍ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው። ነፃነት ሰብዓዊ መብት ሳይሆን የሰብዓዊነት ተግባራዊ መገለጫ ነው። በመሆኑም፣ ነፃነት ከሌለው ሰው ሰብዓዊ ክብሩን ያጣል። ይህን ተፈጥሯዊ ባህሪ የመስጠትና የመግፈፍ ስልጣን ያለው ፈጣሪ ብቻ ነው። ምክንያቱም፣ በሕይወት የተሰጠኝ ነፃነት በሞት ይወሰዳል። ሞትን የደገሰልኝ ፈጣሪ ሕይወትን ጠንስሶልኛልና እሱ ብቻ የሰጠውን … Continue reading ነፃነት “የፈጣሪ”፣ ፍርሃት “የሰይጣን” ነው!

ደርግነት እያቆጠቆጠ – ዴሞክራሲው እየጨላለመ ነው – ህዝቦች ጠንቀቅ በሉ! (ሜ/ጄ አበበ ተክለሃይማኖት)

አበበ ተክለሃይማኖት(“ጆቤ”) (ሜጀር ጄኔራል፣ PhD Candidate) መግቢያ የሃገራችን መንግስትና የገዢው ፓርቲ አጠቃላይ ችግር ዉስጥ በመግባታቸው ምክንያት እዚህና እዝያ እሚታዩ ችግሮች እየተስተዋሉ ነው። ሰሞኑን እንዃ ብናይ ከኦሮሞ ህዝባዉ ዓመፅ፣ ሜቴክና ስዃር ፋብሪካ፣ ከጋምቤላ ጠለፋና ግድያ፣ በኤርትራ በኩል የሚመጣ ተከታታይነት ያለው ዜጎቻችንን የማበሳበስ ሁኔታ እያስተዋልን ነው። የድርቁና በየክልሉ የሚታዩ የህዝቦች መነሳሳት ተጠቓሽ ናቸው። እነዚህ የሚፈጠሩ ነገሮች ካጠቃላይ … Continue reading ደርግነት እያቆጠቆጠ – ዴሞክራሲው እየጨላለመ ነው – ህዝቦች ጠንቀቅ በሉ! (ሜ/ጄ አበበ ተክለሃይማኖት)

መንግስት ግዴታ እንጂ መብት የለውም!

ነፃነት የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ስለሆነ እንቅስቃሴው በሙሉ ከዚያ ጋር የተቆራጀ ነው። መብትና ግዴታ፣ ሕገ-መንግስትና የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ፣ ሀገርና መንግስት፣… የሁሉም መሰረታዊ ዓላማ የሰው ልጅን ነፃነት ማክበርና ማስከበር ነው። ከሰው በስተቀር የሚከበር መብት ያለው ሌላ አካል የለም። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን በሀገራችን እየወጡ ያሉ ሕጎችና አዋጆች መንግስትንና ባለስልጣናት “መብት እንዳላቸው” ታሳቤ ያደረጉ ናቸው። ነገር ግን፣ … Continue reading መንግስት ግዴታ እንጂ መብት የለውም!

ልማታዊ መንግስትና የ3ኛው ምዕራፍ መንታ መንገድ

ወደ ምስራቅ እርቆ የተጓዘ ሰው መድረሻው ምዕራብ ይሆናል። በተመሣሣይ፣ የልማትና እድገት መነሻቸው እና መድረሻቸው ነፃነትና ዴሞክራሲ ናቸው። ከአዳም ስሚዝ ካፒታሊዝም፣ ወይም ከፓርክ ቹንግ ሂ (Park Chung Hee) – ልማታዊ መንግስት እስከ መለስ ዜናዊ – ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት፣ የልማትና እድገትን ፅንሰ-ሃሳብ በጥልቀት የመረመረ፤ ልማት ማለት ነፃነት፣ እድገትና ዴሞክራሲ መሆኑን ይረዳል። አንዱ የሌላኛው ማረጋገጫ እንጂ አማራጭ እንዳልሆነ … Continue reading ልማታዊ መንግስትና የ3ኛው ምዕራፍ መንታ መንገድ

ዝግመትና መንግስት፡ ነፃነትና ፍጥነት

በእርግጥ አነሳሴ፣ በሀገራችን ያለውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተደራሽነትና ሰሞኑን ኢትዮ-ቴሌኮም እየወሰዳቸው ባሉት እርምጃዎች ዙሪያ የዳሰሳ ፅሁፍ ለማቅረብ ነበር። የዓለም የቴሌኮምዩኒኬሽን ማህበር (ITU) በ2015 የፈረንጆች አመት ያወጣውን ሪፖርት በወፍ-በረር እያነበብኩ ነበር። የአለም ሀገራት በዘርፉ ያላቸውን የልማት ደረጃ ከሚያሳው ሰንጠረዥ ውስጥ ኢትዮጲያን ከላይ ወደ ታች እየወረድኩ ብፈልጋት አጣኋት። ፍለጋዬን ከታች ወደ ላይ አድረኩ። 167ኛ፡ ቻድ፣ 166ኛ፡ ኤርትራ፣ 165ኛ፡- … Continue reading ዝግመትና መንግስት፡ ነፃነትና ፍጥነት