ስልጣን ነፃነት – ነፃነት ስልጣን ነው

በተለያየ ግዜና ቦታ የሚታዩ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መሰረታዊ ዓላማና ግባቸው ምንድነው? ብዙውን ግዜ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ እንደተጠያቂው ወገን ይለያያል። የሥርዓቱ ተቃዋሚዎች የትግላቸው ዓላማ “የዜጎችን ነፃነት ለማረጋገጥ” እንደሆነ ሲጠቅሱ፣ የሥርዓቱ መሪዎች ደግሞ እንቅስቃሴው “የመንግስትን ሥልጣን በኃይል ለመጨበት” እንደሆነ ሲገልፁ መስማት የተለመደ ነው። ለምሳሌ፣ አንዳንድ የምዕራቡ ዓለም ምሁራንና ፖለቲከኞች፣ ከ2010 ዓ.ም (እ.አ.አ) ጀምሮ በአረቡ ዓለም የታየውን አብዮት መነሻ ምክኒያት አስመልክቶ የአንድ ሶሪያዊን አባባል ደጋግመው ይጠቅሳሉ። እሱም፡-“We want what you have – Freedom” የሚለው ነው። ነገር ግን፣ በቱኒዚያ፣ በግብፅ፣ በሊቢያና በየመን የሆነውን በእውን ለተመለከተው ፕ/ት በሽር ዓል-አሳድና ደጋፊዎቹ የተቃዋሚዎች ዓላማ “ነፃነት ነው” ቢሏቸው መስሚያ የላቸውም።

በሀገራችን ያለውም ነባራዊ እውነታም ከዚህ ብዙም የተለየ አይደለም። በተለያየ ግዜ በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች፤ “የዜጎች ነፃነት ይከበር!” ከማለት በዘለለ፣ በግልፅ “ዓላማችን ስልጣን መያዝ ነው!” የሚሉ ተቃዋሚዎች ብዙም አይስተዋሉም። በሌላ በኩል፣ በስልጣን ላይ ያለው መንግስትም ተቃዋሚዎችን “ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድና ስልጣንን ለመያዝ” ዓላማ እንዳላቸው ከመግለፅ ግን አይቦዝንም። ነገር ግን፣ ይህ “ነፃነት – ስልጣን” ጉዳይን በጥልቀት በጥልቀት ከተመለከትን ነገሩ ሁሉ፤ “ስልቻ ቀልቀሎ፣…ቀልቀሎ ስልቻ” የሚሉት ነው። ምክንያቱም፣ ስልጣን ነፃነት ነው!፤ ነፃነት ደግም ስልጣን ነው!። ለዚህ ደግሞ የቶማስ ሆብስ (Thomas Hobbes) “Leviathan”የተሰኘው መፅሃፉ በዋቢነት የሚጠቀስ ነው። ከዚህ መፅሃፍ የተወሰደውን የሚከተለውን ዓ.ነገር በማንበብ እንጀምር፤

“A PERSON is he whose words or actions are considered, either as his own, or as representing the words or actions of another man, or of any other thing to whom they are attributed, whether truly or by fiction. …

The word person is Latin, instead whereof the Greeks have prosopon, which signifies the face, as persona in Latin signifies the disguise, or outward appearance of a man, counterfeited on the stage… So that a person is the same that an actor is, both on the stage and in common conversation; and to personate is to act or represent himself or another; and he that acteth another is said to bear his person, or act in his name and is called as a representer, or representative, an attorney, an actor, and the like.

Of persons artificial, some have their words and actions owned by those whom they represent. And then the person is the actor, and he that owneth his words and actions is the author, in which case the actor acteth by authority. So that by authority is always understood a right of doing any act; and done by authority, done by commission or license from him whose right it is.” (Leviathan – Thomas Hobbes, Page 84)

እንደ ቶማስ ሆብስ አገላለፅ “ሰው” ማለት በቃላት (ሃሳብ) ወይም ድርጊት ራሱን ወይም ሌሎችን መወከል የሚችል ነው። እንዲሁም፣ “ሰውነት” የሚገኘው በሁለት መንገድ፤ በተፈጥሮ እና በህግ አግባብ ነው። በዚህ መሰረት፣ “በተፈጥሮ የተገኘ ሰውነት” (natural person) ሲባል በቃላት ወይም በድርጊት ራሱን በራሱ መወከል፤ በራሱ “ፀኃፊና ተዋናይ” (author and actor) መሆኑን እንገነዘባለን። “የህግ ሰውነት” (artificial person) ደግሞ በቃላት ወይም በድርጊት ሌሎችን በመወከል የሚገኝ ነው። በህግ አግባብ በሚገኝ ሰውነት ፀኃፊ (author) እና ተወናይ (actor) የተለያዩ ሰዎች እንደሆኑ መገንዘብ ይቻላል። ፅንሰ-ሃሳቡን በዝርዝር ለመረዳት እንዲያመቸን የተወሰኑ ቃላትን ትርጉምና ፍቺ እንመልከት።

በመጀመሪያ ደረጃ በእንግሊዘኛ “author” የሚለው ቃል “auctorem” ከሚለው የላቲን ቃል የመጣ ሲሆን “መስራች፣ የበላይ ኃላፊ፣ መሪ” (founder, master, leader) የሚል ትርጉም አለው። “authority” የሚለው ቃል ደግሞ “auctor”ከሚለው የላቲን ቃል የመጣ ሲሆን “የበላይ ኃላፊ፣ መሪ፣ ፀኃፊ” (master, leader, author)ማለት ነው። በዚህ መሰረት፣ “authority” የሚለው ሥርዖ-ቃሉ “author” የሚለው እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። በሌላ በኩል፣ “ስልጣን” (authority) የሚለውን ቃል የኣማርኛ ፍቺ ስንመለከት “አንድን ነገር ለማድረግ፣ ለመስራት፣ ወይም ለማሰራት የሚያስችል መብት” መሆኑን ይጠቅሳል። ባለስልጣን” ማለት ደግሞ፤ “አንድን ነገር ለማድረግ፥ ለመስራት፥ ወይም ለማሰራት ኣመራርን ለመስጠት፥ ለመወሰን የሚያስችል መብት ያለው ግለሰብ ወይም ድርጅት” ማለት ነው። ስለዚህ፣ “ስልጣን” ማለት በተፈጥሮ ወይም በውክልና የተሰጠና አንድን ነገር ለማድረግ፣ ለመስራት፣ ወይም ለማሰራት የሚያስችል “መብት” (right) ነው።

በመቀጠል በተለይ ለመንግስት በውክልና የሚሰጥው ስልጣን የዜጎች “ነፃነት” ስለመሆኑ በዝርዝር እንመለከታለን። ለዚህ ደግሞ በቅድሚያ “ነፃነት”* የሚለውን ቃል ፍቺ እንመልከት። የአማርኛ መዝገበ ቃላት “ነፃነት” የሚለውን ቃል፤ “1ኛ፡- ሌላውን ሳይነኩ የፈለጉትን ነገር የመስራት፥ የመናገር፥ የመፃፍ፣ … መብት። 2ኛ፡- በባዕድ መንግስት ወይም በሌላ ሰው ቁጥጥር ስር አለመሆን። 3ኛ፡- ራስን በራስ የማስተዳደር፥ የመምራት ስልጣን፥ መብት” እንደሆነ ይጠቅሳል። የአንድ ሉኣላዊ መንግስት ስልጣን ከእያንዳንዱ ግለሰብ፥ ዜጋ ነፃነት ላይ ተቆርሶ የተሰጠ መብት መሆኑን ለማሳየት የቶማስ ሆብስ በድጋሜ ዋቢ እናድርግ፤

“This is more than consent, or concord; it is a real unity of them all in one and the same person, made by covenant of every man with every man, in such manner as if every man should say to every man: I authorize and give up my right of governing myself to this assembly of men, on this condition; that [you] give up, [your] right to [them], and authorize all [their] actions in like manner. This done, the multitude so united in one person is called a COMMONWEALTH… And he that carries this person is called sovereign, and said to have sovereign power;….” (Leviathan – Thomas Hobbes, Page 87)

ከላይ እንደተጠቀሰው የቶማስ ሆብስ አገላለፅ፣ “መንግስት” ማለት የዜጎችን የጋራ ሰላምና ደህንነት እንዲያስጠብቅ የተፈጠረ አስተዳደራዊ መዋቅር ነው። ማለትም፣ መንግስት፤ “1ኛ፡- የሌላውን መብት ሳይነካ የፈለገውን ነገር እየሰራ፣ እየተናገረና እየፃፈ በሰላም በሀገሩ እንዲኖር (to peace at home)፣ እና 2ኛ፡- በባዕድ ሀገር መንግስት ወይም በሌላ ሰው በኃይል ተገዢ እንዳይሆን (mutual aid against their enemies abroad)ጥበቃና ከለላ እንዲያደርግለት”፤ ከላይ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ከተዘረዘሩት የነፃነት ዓይነቶች ውስጥ 3ኛ ላይ የተጠቀሰውን፡- “ራስን በራስ የማስተዳደር፥ የመምራት ስልጣን፥ መብት”ን በውክልና ለተወሰኑ ሰዎች በመስጠት የተቋቋመ ነው። ስለዚህ፣ “የመንግስት ስልጣን” ማለት የዜጎችን ነፃነት እንዲያስከብር ከእያንዳንዱ ግለሰብ ነፃነት ላይ ተቆርሶ የተሰጠ ነፃነት ነው።

በአጠቃላይ፣ የመንግስት ስልጣን ስሪቱም ሆነ ውጤቱ፤ አጠቃላይ መነሻና መድረሻው፣ ነፃነት ነው። በመሆኑም፣ የህዝብ ተቃውሞ እንቅስቃሴ ዓላማው “የዜጎችን ነፃነት ማረጋገጥ?” ወይስ “የመንግስት ስልጣን መጨበጥ ነው?” በሚል ማለቂያ ወደሌለው ንትርክ መግባት አያስፈልግም። ምክንያቱም፣ ስልጣን ነፃነት፣ ነፃነት ስልጣን ነውና!

ማስታወሻ
በመዝገበ ቃላቱ ውስጥ 1ኛ ተራ ቁጥር ላይ፤ “ነፃነት ስ 1. ኣርነት፣ የምንም ነገር ጥገኛ አለመሆን” የሚል ፍቺ ያለው ቢሆንም፣ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ፍልስፍናዊ ትንታኔ የሰጡ እንደ ቶማስ ሆብስና ኢማኑኤል ካንት ያሉ ፈላስፋዎች ፍቺው ስህተት እንደሆነ ይገልፃሉ። ይህ “ከምንም ነገር ነፃ” በሚል እሳቤ ላይ የተመሰረተ የነፃነት ፅንሰ-ሃሳብ ከሰዉ ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ጋር አብሮ አይሄድም። ምክንያቱም፣ በተፈጥሮ ሰው ማህበራዊ እንሰሳ እንደመሆኑ የምንም ነገር ጥገኛ ሳይሆን መኖር እንደማይችል ይገልፃሉ።

—–

የማጣቀሻ መጽሓፍት

– የኣማርኛ መዝገበ ቃላት፣ የኢትዮጲያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ ኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ፥ የካቲት 1993 ዓ.ም

– End of Civil Government – John Locke

– Leviathan – Thomas Hobbes

*****************

Seyoum Teshome is a Lecturer at Ambo University Woliso Campus and head of Management Department. He was born in Arsi, Assela, in 1979 and studied Management at Harameya University and MBA at Mekelle University. He also blogs at http://ethiothinkthank.com

more recommended stories