ብአዴን የወልቃይት ጉዳይ የትግራይ ጉዳይ እንደሆነ በሙሉ ድምፅ ወስኗል – አለምነው መኮንን

የብአዴን ፅህፈት ቤት ሀላፊ እና የብአዴን/ኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ አቶ አለምነው መኮንን ከጋዜጠኛ ተስፋይ ሃይሉ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ ከወይን መፅሄት የካቲት 2009 እትም። ወይን፡- በትግራይ እና በአማራ ህዝቦች የነበረውና ያለው ግንኙነት እንዴት ይገልፁታል? ኣቶ አለምነው፡- አገራችን የብዙ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሃገር ነች። የትግራይና የአማራ ክልል ህዝቦች ደግሞ በኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ውስጥ የየራሳቸው ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ […]

“በጣም የከፋውና አስቀያሚው ነገር የተጀመረው ቅማንት ላይ ነው” – አዲሱ ለገሰ

የብአዴን መስራች ታጋይ አዲሱ ለገሰ ከጋዜጠኛ አባዲ ገ/ስላሴ እና ሃይላይ ተኽላይ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ ከወይን መፅሄት የካቲት 2009 እትም፡፡ ከኢህዴን ብአዴን መስራች ታጋዮች አንዱ የሆኑት አዲሱ ለገሰ፤ የትጥቅ ትግሉ ካበቃና ደርግ ከተደመሰሰም በኋላ የብአዴን ሊቀ መምበር፣ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር፣ የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር፣ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስተር፣ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር፣ የፌደራል መለስ አካዳሚ ስልጠና ማእከል ዋና […]

የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት ላይ ያነጣጠረ መሰረተ ቢስ ውንጀላ እስከ መቸ?

(ታጋይ ካሕሳይ ቃሉ) በዚሁ ወር መጀመሪያ ሳምንት በትግራይ ኦንሊይን (Tigray online) ድረ-ገፅ ላይ በአቶ እውነቱ ዘለቀ የተባሉ ፀሃፊ “ያን ያህል ወጥ መርገጥ ምን የሚሉት ድፍረት ነው”[PDF] በሚል ርእስና ቀደም ብሎ በእንግሊዝኛ ቋንቋ “Gedu Andargachew; A fifth column on the loose” በሚል ርእስ በአቶ ብርሀነ ካሕሳይ ተፅፎ ለተዘረጋው ፅሁፍ መልስ ለመስጠት ታስቦ የወጣውን ፅሁፍ ተመለከትኩ፡፡ የፅሁፉ መነሻ […]

ሕዝብ በእንጀራ ብቻ አይኖርም – በርዕዮተ ዓለም ጭምር እንጂ

አብዮታዊው ኢህአዴግ – ኢትዮጲያን በልል ፌዴራሊዝም (loose federalism) መንፈስ በተቀመረ ህገመንግስት አዲስ ስርአት የመሰረተ እና የመራ፤ ጠንካራ እና የጠራ ርዕዮተ ዓለም እና አባላት የነበረው፤ በዘረጋው ያልተማከለ የፌዴራል ስርአት የተነሳ አገር ሊበታትን እንደሆነ ይታማ የነበረ እና በብሄረተኞችና በግራ ዘመም የብዝኀነት (diversity) ኀይሎች የሚታመን ነበር፡፡ ድኅረ 97 ኢህአዴግ – በይደር ያቆያቸውን ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎችን በቅድሚያ ሳይመልስ የመናገሻ ከተማ […]

የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ ይሻል !

(ኮሎኔል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ) በቅድሚያ በኮንሶ ህዝብ ላይ እየደረሰ ሲላለዉ በደል አንዳችም ትርፍ  ነገር ሳይጨምር ሳይቀንስና ሳይደባብቅ ሃቁን ለህዝብና ለሚመለከታቸዉ የመንግስት ባለስልጣና አካላት ሁሉ እንዲደርስ ባደረገዉ በአቶ ናሁሰናይ በላይ የተሰማኝን ኩራትና አድናቆት ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ናሁሰናይ አስታዋሽ ያጣዉና ትኩረት የተነፈገዉ  የኮንሶ ህዝብ  ብቻ  ሳይሆን  ጭቆናንና በደልን የሚጸየፉ የመላዉ የሀገራችን ህዝቦች ሁሉ እንደሚያሰግኑህ ቅንጣት ጥርጥር የለኝም፡፡ ሆርን […]

የትግራይ ህዝብ የለውጡ አጋር እንጂ ተጠቂ ሊሆን ኣይገባም

(መርስዔ ኪዳን) ([email protected] – ሜኔሶታ፤ ሃገረ ኣሜሪካ) ሰሞኑን በሃገራችን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ አመፅ ምክኒያት ብዙ የሰው ህይወት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት እየደረሰ ነው። ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር ያበቁ ብዙ ምክኒያቶች ቢኖሩትም አንዱና ዋነኛው ምክኒያት በሃገሪቱ ውስጥ ፍትሃዊ የሆነ የፖለቲካ ስርዓት አለመኖሩ ነው። ኢትዮጵያ ብዙ ብሄሮች ብቻ ሳይሆን ብዙ ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አመለካከት ያለው ህዝብ የሚኖርባት አገር […]

የኮንሶ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ

የኮንሶ ጥናታዊ ጉዞየን እንድሰርዝ ያስገደድኝኝ ግጭት ምንነት ለማወቅ ያካባቢው ሰዎችን አነጋግሬ ያገኘሁት መረጃ ለማካፈልና አሳሳቢነቱን ስለማሳወቅ ስል ይህንን ፅፍያለሁ።ሁኔታው ካሁኑ ካልተገታ ወደ እማያባራ ግጭትና መተራረድ ሊያመራ ስለሚችል የክስተቱ አጣዳፊነት ለማስገንዘብ ስል ጭምርም ነው ይህንን የፃፍኩት። የኮንሶ ህዝብ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልላዊ መንግስት ተደራጅቶ ያለ ብሔረሰብ ሲሆን ከ2004 መጋቢት ወር በፊት በልዩ ወረዳ መዋቅር ራሱን በራሱ […]

ም/ጠ/ሚ ደብረጺዮን – የብሔር የበላይነት ስለሚባለውና በጎንደር ስለተከሰተው መፈናቀል [Video]

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚና ፋይናንስ ክላስተር አስተባባሪ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ባለፈው አርብ ነሐሴ 27/2008 ለኦንላይን ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በጋዜጣዊ መግለጫው ከዳሰሷቸው በርካታ ጉዳዮች መሀል፡- * በጎንደር መተማ-ዮሐንስ አካባቢ ስለተከሰተው መፈናቀል እና ስለአካባቢው ፀጥታ * ‹‹የአንድ ብሔር የበላይነት›› የሚባለውን አስመልከቶ የሰጡትን ማብራሪያዎች ቪዲዮ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡ (ለድምጽ ጥራት ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡) —— Watch the video *************

ተራማጅ ህገ-መንግስት

(ስንታየሁ ግርማ ([email protected])) የኢፌዴሪ ህገመንግስት ተራማጅ ህገመንግስት ሊያስብሉት የሚችሉ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ይዟል፡፡ ከሌሎች የተለየ የራሡ ገፅታዎችም አሉት፡፡ ከህገመንግስት መግቢያ ስንጀምር እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች ሰለሚል የህገመንግስት ባለቤቶች ቤሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መሆናቸውን ያሣያል፡፡ ህገመንግስቱ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሃረሰቦች፣ ህዝቦች አንቀፅ በአንቀፅ የተወያዩበት እና ያፀደቁበት ስለሆነ ባለቤቶቹ እነሱ […]

ወልቃይት እንኳን ህዝቡ መሬቱም ትግራዋይ ነው – ከታሪክ መዛግብት

(አስፋው ገዳሙ ([email protected])) 1/ መግቢያ የኢትዮጵያ ክልሎች አወቃቀር ሁሉንም ኢትዮጵያውያን አብረውና ተከባብረው እንዲኖሩ የሚያስችል ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር፡፡ በተለያዩ ወቅቶች ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ ገዢዎች ለህዝቡ ምቾት ሳይሆን ለራሳቸው በሚመች መልኩ ሃገሪቱን ሲስተዳድሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የአሁን መንግስትም ለራሱ በሚመቸው መልኩ እያስተዳደራት ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ብዙ ሰዎች፣ በተለይም የጎንደር ተወላጆች በደርግና በአጼ ሃይለስላሴ ወደ ነበረው አከላለል ካልተመለስን እያሉ […]