(ስንታየሁ ግርማ ([email protected]))

የኢፌዴሪ ህገመንግስት ተራማጅ ህገመንግስት ሊያስብሉት የሚችሉ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ይዟል፡፡ ከሌሎች የተለየ የራሡ ገፅታዎችም አሉት፡፡ ከህገመንግስት መግቢያ ስንጀምር እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች ሰለሚል የህገመንግስት ባለቤቶች ቤሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መሆናቸውን ያሣያል፡፡ ህገመንግስቱ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሃረሰቦች፣ ህዝቦች አንቀፅ በአንቀፅ የተወያዩበት እና ያፀደቁበት ስለሆነ ባለቤቶቹ እነሱ ናቸው፡፡ በህገ መንግስቱ ላይ ከ16 ሚሊዬን በላይ ህዝብ ተወያይቶበታል፡፡

በተለይም መሬት የግል /የመንግስት/ የሚለው እና የራስን እድል በራስ መወሰን አንቀፅ በአንቀፅ ውይይት ተካሄዱበት በድምፅ ብልጫ ነው የፀደቀው፡፡ መሬት በብዙ ሀገሮች የካቤኔ ጉዳይ እንጂ ህገመንግስታዊ ትኩረት አይሰጠውም፡፡ መሬት ከኢኮኖሚያዊ ፍይዳ በተጨማሪ የብሄር/ብሄረሰቦችን መብቶች ለማስከበር ቁልፍ ሚና ያለው በመሆኑ መሬት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ሆኖ ለኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች የጋራ ተጠቃሚነት እንዲውል በህዝብም ሰም መሬት በመንግስት ስር እንዲሆን ተደንግጓል፡፡

Image - Cover page of the Constitution of Ethiopia
Image – Cover page of the Constitution of Ethiopia

የራስን እድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል በህገ መንግስቱ እውቅና በማግኘቱ የእኛ ህገመንግስት ሌላኛው መለያ ባህሪ ነው፡፡ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ከ18ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ የመጣ ሲሆን በትርጉም ሆነ በአተገባበር እስካሁን በአለም ደረጃ እያወዛገበ ነው፡፡ የራስን እድል በራስ የመወሰን ማለት ምን ማለት ነው? የእዚህ መብት ተጠቃሚዎች እነማን ናቸው? የሚሉት አሁንም እያከራከሩ ነው፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ እስካሁን ተቀባይነት ያለው አለም አቀፍ ህግ እ.ኤ.አ በ1967 በአልጀርስ ደርሶ የፀደቀው አለምአቀፍ የህዝብ መብቶች ድንጋጌ (Universal declaration of the rights of people) የሚባለው ነው፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሠረት 2 ዐይነቶች የራስራ እድል በራስ የመወሰን መብቶች አሉ፡፡ ውስጣዊ እና ውጫዊ የራስራ እድል በራስ የመወሰን መብት ናቸው፡፡ ውስጣዊ የራስን እድል በራሱ የመወሰን መብት የሚባለው አንድ ህዝብ /ብሄር/ ሀገር በሚባለው ውስጥ የራሡን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ስርአት የመዘረጋት መብት እንዳለው የሚደነግግ ነው፡፡ ውጫዊ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ደግሞ ውስጣዊ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ሣይከበር ሲቀር ተግባራዊ የሚሆን ነው፡፡

በድንጋጌው መሠረት ውጫዊ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ያላቸው የዘር ልዩነት የተደረገባቸው በወታደራዊ እና ተመሣሣይ የአገዛዝ ስርአት ስር ያሉ ህዝቦች ናቸው፡፡ ከሞላ ጐደል በዚህ ድንግጌ ውስጥ የተካተቱ መርሆዎችን ተቀብላ ኢትዮጵያ በህገመንነግስቱ ስለሰፈረች የተለየ ተብሎ መውሰድ የለበትም የሚሉ አሉ፡፡ ያምሆነ ይህ የራስን እድል በራስ መወሰን በህገ መንግስት እውቅና መሰጠት ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ብትሆንም ዋናው ነገር በተግባር መብቱን ማረጋገጥ እንጂ በህገመንግስት ስለሰፈረ ጥያቄው ሊያነሣ አይችልም የሚያስብል አይደለም፡፡ እንደውም የራስን እድል በራስ መወሰን አለማቀፍ ልማዳዊ ህግ (Customary iatenational law) ሆኗል የሚሉ አሉ፡፡

የቀድሞው ሶቬየት ህብረት ከፈራረሰች በኋላ ወደ 21 አዳዲስ ሀገራት ተፈጥረዋል፡፡ ይጐዝላቪያ ከተበታተነች በኋላ 5 አዳዲስ ሀገራት ተፈጥረዋል፡፡ በተመድሞ እውቅና አግኝተዋል፡፡ የታላቁ ብሪታኒያ አካል የሆነችው ስኮትላንድ በዴቪድ ኮሜሩን ግዜ ህዝብ ውሣኔ አካሄደው በጥቂት ድምፅ ልዩነት ከታላቁ ብሪታኒያ ጋር ለመቆየት ወሰናለች፡፡ ምንም እንኳን እንግሊዝ ያልተፃፈ ህገ-መንግስት ያላት ቢሆንም በእንግሊ ህግ የመገንጠል ጥያቂ የተፈቀደ አይደለም፡፡ ታዲያ ዴቪድ ካሜሩን ያሉት በህግ ባይፈደቀድም ዲሞክራት በመሆን የህዝብ ውሣኔውን ፈቅጃለሁ ብለዋል፡፡ ከዚህ በመነሣት የማንነት ጥያቄ የሚነሣው በህግ ስለተደነገገ ብቻ ሳይሆን በተግባር የፍትሀዊ ተጠቃሚነት (በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ) ጥያቄ ውስጥ ሲገባ ነው፡፡

ካታሎንያውያን እኛ በተፈጥሮ በጣም ሀብታም፣ ለስፔን ማዕከላዊ መንግስት ፈሰሰ የምናደረገው ገንዘብ ከፍተኛ በሌላ በኩል የኢኮኖሚ ቀውስ ሲመጣ ታታሪውን የካታሎናውያን ዜጋ የሚያጠቃ በመሆኑ የራሳችን እድል በራሳችን የመወሰን መብታችን ሊከበርልን ይገባለ እያሉ በተደጋጋሚ ቢወተወቱም እስካሁን ተቀባይነት አላገኙም፡፡ እንደውም ስፔን ብሄራዊ ቡድን ውጤት ባጣ ቁጥር የባርሴሎናና የማድሪድ ተጫዋቶች ክፍል ምክንያቱ ነው ብለው የሚያስቡ ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ ብዝሃነት ባለበት አካባቢ ትልቁ መፍትሄው የተመጣጠነ ልማት ማምጣት እና በታሪክ አጋጣሚ ለተገፋ የማህበረስብ ክፍሎች ትኩርት ሰጥቶ ልማትን በማፋጠን ፍትሀዊነት ማስፈን ነው፡፡

የማንነት እውቅና ከዘመናዊነት ጋር አብሮ እየሄድም የኋላ ቀርነት ምልክት ነው ብለው የሚያስቡ የዋህ ፖለቲካዋች ቀላል አይደሉም፡፡ አሜሪካ የበለፀገ ሀገር ነው ግን ለብዝሃት እውቅና ስለማይሰጥ በሽብርተኝነት የተጋለጠች ቁጥር አንድ ሀገር ሆናለች፡፡ ለብዝሃነት እውቅና እንደማይሰጡ ከህገ መንግስት መግቢያ ይጀምራል፡፡ የአሜሪካው ሕገ-መንግስት <<ህዝብ>> በሚል ይጀምራል፡፡ ፈረንሣይም በየጊዜው በሽብረ ጥቃተ የተወጠረች ሀገር እየሆነች ነው፡፡ የእነሱም እውቅና አለመስጠት ከህገ- መንግስቱ መግቢያ ይጀምራል፡፡ ‹‹ዜጋ›› በሚል ስለሚጀምር በፈረንሣይ የተወለደ ሁሉ ፈረንሣያዊ ነው በማለት ለብሄር ማንነት እውቅና አይሰጡም፡፡ ለብሄር ማንነት እውቅና ባለመሰጠቱ መንግስታዊ አገልግሎትን ፍትሀዊ ለማድረግና ወደዳር ተገፍተናለ ብለው የሚያስቡ የማህበረሰብ ክፍሎች በተለይም ሙስሊሞች ለማካተት የተደረገው ጥረት እጅግ አነስተኛ ስለሆነ ፈረንሣይ በሽብርተኝነት ተወጥራ ያለች ሀገር ሆናለች፡፡

እንግዲህ የማንነትን ጥያቄ ዘመናዊነት የሚያስቀር ቢሆን ኖሮ ፈረንሣይ እና አሜሪካ ማስቀረት በቻሉ ነበር፡፡ ስለዚህ በህገ መንግስታችን መግቢያ ላይ ለብዝሃነት ኢትዮጵያ እውቅና መስጠቷ ምን ያህል የተራማጅ ህገመንግስት ባለቤት ሀገር መሆናችንን ያሣያል፡፡

ታዲያ ይህንን ተራማጅ ህገ መንግስት ማክበር ማስከበር የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት መሆን አለበት፡፡ ህገመንግስት የኢህአዲግ ነው የሚሉት ተሣስተዋል፡፡ ይህንን ለማየት የህገመንግስቱን የአፀዳደቅ ሂደት ማየት ተገቢ ነው፡፡ ህገ መንነግስቱን በማረቀቅ ሂደት ምንም እንኳን ኢህአዲግ የመሪነቱን ሚና ቢጫወትም ተቀዋሚዎች ታዋቂ ግለሰቦችና ምሁራኖች ንቁ ተሣትፋ ነበሩ፡፡ እንዲውም የኢትዮጵያ ህገመንግስት አባት (Founding Father of the Ethiopian Constitution) የነበሩት አቶ ክፍሌ ወዳጅ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት የተባለ የተቃዋሚ ፖርቲ ሊቀመንበር ነበሩ፡፡

ታዲያ ይህ ህገመንግስት ኢህአዲግ ኖረ አልኖረ በጣም ተራማጅ ህገመንግስት ስለሆነ የሚኖር ነው፡፡ ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ህገመንግስት ማክበር ማስከበር የሁሉም ዜጋ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ መሆን ያለበት፡፡ ይህንን ተራማጅ ህገመንግስት እንደ ዐይናችን ብሌን መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ ህገመንግስቱ ትናንትን፣ ዛሬንም፣ የወደፊቱንም ያየ ስለሆነ ምንም አንከን ሊወጣለት ዐይችልም፡፡ ህገመንግስቱን የሚያጣጥሉት ምንም መሠረት የላቸውም፡፡ “ወፍ ብልግናዋን ለማሣየት ባህሩ ላይ ትሽናለች ባህሩ ግን አይደፈርስም፡፡”

********

Avatar

Guest Author

more recommended stories