Category Archives: Grand Ethiopian Renaissance Dam

የህዳሴ ግድብ ተቃዋሚ አሜሪካዊ ድርጅት ሆርን አፌይርስን አስጠነቀቀ

የኢትዮጲያን ግድቦች በመቃወም የሚታወቀው ‹‹ኢንተርናሽናል ሪቨርስ›› የተባለው ድርጅት የታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ ሥራ ቆሞ ከግብጽ ጋር ድርድር መካሄድ አለበት በማለት በመጋቢት 22/2006 ላወጣው መግለጫ፤ በሆርን አፌይርስ-የእንግሊዝኛው ገጽ(HornAffairs-English) ላይ በሚያዝያ 6/2006 የተሰጠውን ምላሽ አወገዘ፡፡ በዳንኤል ብርሃነ የተፃፈው ምላሽ፤ የድርጅቱን መግለጫ አንድ በአንድ እየነቀሰ ድርጅቱ የህዳሴ ግድብ ዓለም-አቀፍ የባለሙያዎች ፓነል ሪፖርትን አጣምሞ ማቅረቡን ያመላከተ ቢሆንም፤ የድርጅቱ ኤግዘኩይቲቭ … Continue reading የህዳሴ ግድብ ተቃዋሚ አሜሪካዊ ድርጅት ሆርን አፌይርስን አስጠነቀቀ

የግብፅ ‘ክስ’ – ቂም ነው ትርፉ!

ግብፅ <ከኢትዮጵያ ጋር ያለኝን አለመግባባት ወደ አለም አቀፍ ገላጋዮች እወስደዋለሁ> ስትል እንደፎከረችው አሁን ተግባራዊ ለማድረግ ጫፍ ላይ የደረሰች ትመስላለች፡፡ በሙባረክ ዘመነ ስልጣን የህግና ፓርላማ ጉዳዮች ሚኒስትር የነበሩትና የአረብ ሊግን ዋና ፀሃፊነት ስልጣን ከአሚር ሙሳ እንዲረከቡ በሙባረክ እጩ ሆነው ተመርጠው የነበሩት ሙፊድ ሼሃብ <<የህዳሴውን ግድብ ጉዳይ ለአለም አቀፍ አካል ለማቅረብ የሚያስችለኝን ሁሉን አቀፍ ጥናት አጠናቅቄ ለፕሬዝዳንቱ … Continue reading የግብፅ ‘ክስ’ – ቂም ነው ትርፉ!

የቻይና ባንክ ለህዳሴ ግድብ የኃይል ማከፋፈያ-ማሰራጫ መስመር ብድር ለመልቀቅ ተስማማ

(ውድነህ ዘነበ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ለሁለት ከተከፋፈለ በኋላ የውጭ አገር የፋይናንስ ተቋማት ቀደም ሲል የፈቀዱትን ብድር በማቋረጣቸው፣ የተቋረጠውን ብድር ለማስለቀቅ የኮርፖሬሽኑን ኃላፊነት የተረከበው አዲሱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሯል፡፡ ከዚህ ቀደም ኮርፖሬሽኑ ፈጽመዋቸው የነበሩ ስምምነቶችን ኢንተርፕራይዙ በማደስ ላይ እንደሚገኝ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ … Continue reading የቻይና ባንክ ለህዳሴ ግድብ የኃይል ማከፋፈያ-ማሰራጫ መስመር ብድር ለመልቀቅ ተስማማ

የህዳሴ ግድብ ውሀ ለሚተኛበት ስፍራ ደን የማንሳት ሥራ ተጀመረ

ውሃው የሚተኛበትን ሥፍራ የማዘጋጀቱ ሂደት ከአጠቃላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መርሃግብር ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጐ የሚቆጠር ነው፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ የግድቡ ውሃው በሚተኛበት ስፍራ የሚገኘውን የተፈጥሮ ደን የማንሳት ሥራ መጀመሩን የግድቡ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ገለጹ፡፡ የተፈጥሮ ደኑ ውሃው ከሚተኛበት ቦታ መነሳቱ የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ሊከሰት የሚችለውን … Continue reading የህዳሴ ግድብ ውሀ ለሚተኛበት ስፍራ ደን የማንሳት ሥራ ተጀመረ

የህዳሴው ግድብ ድርድር ማርሽ መቀየሪያ ሰዓቱ አሁን ነው!

የግብፆቹ የክርክር ድርቅና ትንሽ ወረደብኝ። መልስ ባገኘና ሃገር ባወቀው ሃቅ ለመነታረክ ጊዜ መስጠት ልክ በአንድ ማርሽ የተለያየ ተዳፋትን በአንድ ፍጥነት ለማለፍ እንደመታገል አይነት ሹፍርና ይመሰልብኛል። ሞተር ማበላሸት ነው። ሃገራችንን ያስንቃል፤ የእነርሱንም የዲፕሎማሲ ድንቁርና እንደመውረስ ይቆጠራል። ግድቡ ትልቅ ስለሆነ ጸንቶ አይቆምም፤ የመሬት መናወጥ ክልል ውስጥ ስለሆነ መሰራት የለበትም፤ … ሲሉ ላምናቸው ተቃርቤ የአለማቀፍ ባለሙያዎችን ቡድን ምስክርነትና … Continue reading የህዳሴው ግድብ ድርድር ማርሽ መቀየሪያ ሰዓቱ አሁን ነው!

ኢቴቪ የአልጀዚራን ግብፃዊ ፕሮፓጋንዳ ሲያስተጋባ

በኳታር መንግስት ሃብት የተቋቋመውና ስነ አፈጣጠሩ ሲጠናም የምዕራቡን አለምና የእስራኤል ሚዲያን የአረብ ሀገራት ጉዳይ አዘጋገብ ለመገዳደር የተፈጠረው የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ስትራግል ኦቨር ናይል በሚል ርዕስ አንድ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅቶ ነበር። ጣቢያው ይህን ፊልም በቴሌቪዥኑ ያስተላለፈው ሲሆን በድረ ገፁ ላይ ስለጫነውም በርካቶች ተመልክተውታል። የዘጋቢ ፊልሙ ይዘት በናይል ወንዝ የተነሳ በላይኛውና በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት መካከል ስለነገሰ ውጥረት … Continue reading ኢቴቪ የአልጀዚራን ግብፃዊ ፕሮፓጋንዳ ሲያስተጋባ

የታሪካዊ የውኃ ዋስትና ወይስ የታሪካዊ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት መብት አጀንዳ?

አሁን የአረቦቹ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥገኞች ነን። በእውቀትና በሥራ ሳይሆን ከነዳጅ የተገኘ ሃብታቸውን ለመቀላወጥ ያልሆንላቸው ነገር የለም። ድንግል የእርሻ መሬታችንንና የተፈጥሮ የምግብ ምርታችንን የገበያ ዋጋ ለመወሰን አቅማችን በወረደ የገበያ መድረክ ይነጥቁናል። በአለማቀፍ መድረክም ድህነታችን ባመጣብን ጣጣ የእነርሱን ፍላጎት በትክክለኛ ሚዛን ላይ አስቀምጠን እንዳንደራደር አድርገውናል፡፡ ለውኃ  ልማታችን ብድር እንዳናገኝ የዘጉብንን በር ማስታወሱ በቂ ነው። መሪዎቻችንን ገና ከናስር … Continue reading የታሪካዊ የውኃ ዋስትና ወይስ የታሪካዊ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት መብት አጀንዳ?

[መነበብ-ያለበት] ፕ/ር ሃይሰም ማሃዎዲ እና ዶ/ር ናስር ኣላም ከናይል ቲቪ ጋር ያካሄዱት ውይይት፡፡

(በሙሉነህ ቶለሳ) የግብጽ የአሌክሳንደሪያ ዩኒቨርሲቲ የሲቪል ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰር ሃይሰም ማሃዎዲ እና የግብፅ የቀድሞ ውሃ ሀብት ሚኒስትር ዶክተር ናስር ኣላም ከናይል ቲቪ “ላይቭ ዊንዶስ” የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ላይ (ከጋዜጠኛ ዲና ሁሴን) ጋር ያካሄዱት ውይይት፡፡ ጋዜጠኛ ዲና ሁሴን፡- እንደሚታወቀው ከኢትዮጵያው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ችግሮች እየተጋረጡብን ነው፤ የኃይል እጥረት ሊያጋጥመን ነው፣ የግብፅ የናይል ውሃ ድርሻም ከ55 … Continue reading [መነበብ-ያለበት] ፕ/ር ሃይሰም ማሃዎዲ እና ዶ/ር ናስር ኣላም ከናይል ቲቪ ጋር ያካሄዱት ውይይት፡፡

ግቤ ሶስት 82 በመቶ – ገናሌ ዳዋ ሶስት 48 በመቶ – ህዳሴ ግድብ 32 በመቶ ተጠናቅቀዋል

(የማነ ገብረስላሴ) የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታወቀ ። የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል የውጭ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ የፕሮጀክቶቹን አፈጻጸም በማስመልከት ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የግቤ ሶስት፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ የገናሌ ዳዋ የሃይል ማመንጫ ግድቦችና የአዳማ ሁለት የንፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታዎች በፍጥነት እየተከናወኑ ናቸው። … Continue reading ግቤ ሶስት 82 በመቶ – ገናሌ ዳዋ ሶስት 48 በመቶ – ህዳሴ ግድብ 32 በመቶ ተጠናቅቀዋል

Dr. Merera|ግድቡ አይሳካም፣ተቃዋሚዎች ከግብጽ ሊተባበሩ ይችላሉ

(አርአያ ጌታቸው) በአባይ ወንዝ ዙሪያ በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል በተነሳው አለመግባባት ዙሪያ ብዙዎች ብዙ ሲሉ አድምጠናል፡፡ በተለይ ደግሞ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች መንደር የተደመጠው ምላሽ ዛሬም ድረስ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የሀገሪቷ የፖለቲካም ይሁን የሌሎች ዘርፍ ምሁራን በጉዳዩ ዙሪያ ምንም ሲሉ አልተደመጡም፡፡ ይሄንን ነገር ሳብላላ አንድ ሰው በአምሮዬ ብቅ አሉ፡፡ አልተሳሳቱም በፎቶው ላይ የሚመለከቷቸው ዶክተር መረራ ጉዲና፡፡ … Continue reading Dr. Merera|ግድቡ አይሳካም፣ተቃዋሚዎች ከግብጽ ሊተባበሩ ይችላሉ