ሱር ኮንስትራክሽን ለህዳሴ ግድብ ቃል የገባውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ገቢ አደረገ

ሱር ኮንስትራክሽን ኩባንያ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ቦንድ ለመግዛት ቃል የገባውን 25 ሚሊዮን ብር ሙሉ በሙሉ ገቢ አደረገ።

የኩባንያው ዋና ስራ አስከያጅ አቶ ታደሰ የማነ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ25 ሚሊዮን ብር ቦንድ ከተረከቡ በኋላ እንደተናገሩት ድርጅቱ  ገንዘቡን በአምስት አመታት ጊዜ ውስጥ ለመክፈል አቅዶ የነበረ ቢሆንም በኩባንያውና በሰራተኞቹ በተፈጠረው ከፍተኛ መነሳሳት ቀድሞ ሙሉ በሙሉ ገቢ አድርጓል።

ኩባንያው ከገዛው የ25 ሚሊዮን ብር ቦንድ መካከል 21 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በድርጅቱ ቀሪው ደግሞ በሰራተኞች የተሸፈነ ነው።

ኩባንያው የህዳሴው ግድብ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

የኩባንያው ሰራተኞች በበኩላቸው ከገንዘብ ድጋፍ ባሻገር በሙያቸው አገልግሎት ለመስጠትም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ባህረ ሱር ኮንስትራክሽን ኩባንያና ሰራተኞቹ ቃላቸውን በማክበር ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል።

ለግድቡ ግንባታ ቦንድ ለመግዛት ቃል የገቡ ድርጅቶችና ተቋማትም የሱር ኮንስትራክሽን ኩባንያን ፈለግ በመከተል ገንዘቡን በወቅቱ ገቢ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሱር ኮንስትራክሽን ኩባንያ ለ6 ሺ 290 ዜጎች ቋሚና ጊዚያዊ የስራ ዕድል የፈጠረ ተቋም ነው።
********
ምንጭ፡- ኢዘአ – ሚያዚያ 4/2006  ርዕስ
ሱር ኮንስትራክሽን ኩባንያ ቦንድ ለመግዛት ቃል የገባውን 25 ሚሊዮን ብር ሙሉ በሙሉ ገቢ አደረገ

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories