ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በትግል 10 ዓመታ ካስቆጠረ በኋላ፤ በ1977ዎቹ የፖለቲካ አመራር የሚሰጥ አደረጃጀት ማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ(ማሌሊት) በሚል ስያሜ እንደመሠረተ ይታወሳል፡፡
ያ አደረጃጀት ዓለም-አቀፋዊውን የአሰላለፍ ለውጥ ተከትሎ ከ1983 በኋላ እንዲቀር መደረጉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በአብዛኛው ሕዝብ እምብዛም አይታወቅም፡፡
ይሁን እንጂ ህወሓት ከ1970ዎቹ አጋማሽ በኋላ ላሳየው የወታደራዊ እና ድርጅታዊ እመርታ ምክንያቱ የማሌሊት ምሥረታ ያስከተለው የርዕዮተ-ዓለም ጥራት ነው ብሎ ያምናል፡፡ በአንጻሩ የቀድሞው የድርጅቱ አመራር ገብሩ አሥራት በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ፡- በወቅቱ የተገኙት ለውጦች ያለማሌሊት ሊከሰቱ የሚችሉ የአደረጃጀት ለውጥ ውጤቶች ናቸው የሚል ሀሳብ አንስተዋል፡፡
ባለፈው ሰኞ ጥር 30-2007 ቃለ-መጠይቅ ያደረግንላቸው ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሰኤ ካቀረብነው ጥያቄዎች አንዱ ማሌሊትን የተመለከተ ነበር፡፡
ከ1971 ጀምሮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት እና ማሌሊት ሲቋቋም ከመጀመሪያዎቹ 9 የፖሊት ቢሮ አባላት አንዱ የነበሩት እንዲሁም የህወሓት ሠራዊት ቺፍ ኦፍ ስታፍ የነበሩት ጻድቃን፤
* የማሌሊት ምሥረታን እና በሕወሓት መዋቅር ላይ የነበረውን ፋይዳ ያብራሩ ሲሆን አያይዘውም
* የህወሓትን ወታደራዊ ስትራቴጂ ጽንሰ-ሀሳቦች፣
* ከደርግ 603ኛ ኮር ጋር በሽረ የተደረገውን ውጊያና ተዛማጅ ታሪካዊ ሁነቶችን እንደሚከተለው አብራርተዋል፡፡
[እስከ 1993 የሀገር መከላከያ ሠራዊት ኤታማጆር ሹም የነበሩት ሌፍተናንት ጄኔራል ጻድቃን፤ የህወሓት-ሻዕቢያ ግንኙነት፣ የ1977ቱ ረሀብ፣ በኤርትራ ወረራ ወቅት የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሚና፣ የቀድሞው ሠራዊት መበተን እና ሌሎች ዐብይ ርዕሰ-ጉዳዮች እንዲሁም ስለራሳቸው ለቀረቡ ጥያቄዎች የሰጡትን ምላሾች በተከታታይ እናቀርባለን]
——
Watch Video below.
*************
Comments are closed.
Leave a Comment