​የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በወጣቶች ልማት ፓኬጆች ማብራሪያ ሰጥቷል

(አብዱረዛቅ ካፊ)

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊና የክልሉ ፕሬዝዳንት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አማካሪ አቶ መሀመድ ቢሌ ሀሰን (ሚግ) የክልሉ የወጣቶች ልማታዊ ስተራቴጅዎችና አቅጣጫዎች እንድሁም በተገኘው የወጠቶች ለውጥ ሥራዎች ተጠቃሚነታቸው እንድያረጋገጡ  ለወጣቶች ልማት ፓኬጆች ጥምር ኮሚቴ አባላት ማብራሪያ ሰጥቷል።

አያይዞም ቢሮ ኃላፊው  ከቅርብ አመታት ወዲህ የክልሉ መንግስት በወጣቶች  ልማት ፓኬጆች ወጤታማነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ትኩረት  እንደተሰጠም አመልክቷል።

Photo - Mohamed Bile, Ethio-Somali press advisor

በተጨማሪም ወጣቶቹ የክልሉ ህዝብ የጀርባ አጥንት መሆናቸውና የክልሉ ልማታዊ እቅዶችን ከዳር ለማድረስ፤ደህነትና የወጣቶች ሥራ አጥነትን ለማጥፋትና አገራችን መካከለኛ ገቢ ከላቸው አገራት ተርታ ለማሰለፍም የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል በፈዴራልና በክልል ደረጃ የተነደፈው የወጣቶች ልማት ፓኬጆችን ለማሳካት በዘንድሮ አመትም የክልሉ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ላይ እንደሚገኝና  የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮም  አዲሱ የወጣቶች ለውጥ መርሃ ግብርን  በዞን፤ በወረዳ፤ በቀበሌና መንደር ደረጃም የታለሙት እቅዶችን እውን ለማድረግ የተለያዩ የወጣቶች ልማት ፓኬጆች ጥምር ኮሚቴዎች ማቋቋሙን ሃላፊው ጠቆሟል ።

በመጨረሻም በዞን፤ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ የተቋቋሙ የወጣቶች ልማት ፓኬጆች ጥምር ኮሚቴ አባላት ደህነትና ሥራ አጥነትን ለማጥፋት የታቀደው የወጣቶች ልማት ፓኬጆች ተግባራዊ እንድያደርጉና የበኩላቸው ድርሻ እንድወጡ ጥርያቸውን አቅርቧል አቶ መሀመድ ቢሌ።

*********

Guest Author

more recommended stories