የኢትዮ-ሶማሌ ቴሌቪዠን የአማርኛ ቋንቋ ስርጭት ጀመረ

(አብዱረዛቅ ካፊ)

የኢትዮጲያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት ቴሌቪዠን ጣቢያ የአማርኛ ቋንቋ ስርጭት መጀመሩንና ይህም የቴሌቪዥንኑን ተመልካች ቁጥር እንደሚጨምር እንደሚጠበቅ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አክሎ አስታውቋል።

የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ኢንጅነር ኢድሪስ ኢስማኢል ጣቢያው የአማርኛ ቋንቋ ስርጭት መጀመሩ በርካታ ጉዳዮች ታሳቢ ተደርጎበት እንደሆነም ገልጿል።

በሀገሪቷ ሰፊ ተናጋሪ ያለው አማርኛ ቋንቋ በጣቢያው እንድንጀምር ባለፉት ወራት በርካታ ዝግጅቶችና የዳሰሰ ጥናት የተደረገበት ሲሆን ይህም የሀገሪቷ የስራ ቋንቋ የሆነውን አማርኛ ቋንቋ ለአማርኛ  ተናጋሪ ለሆኑት ተመልካቾች ተደራሽ ለማድረግ ሲባል ነው ብለዋል ኢንጅነር ኢድሪስ ኢስማኢል።

Logo - Ethio-Somali television
Logo – Ethio-Somali television

ኢንጅነር ኢድሪስ ኢስማኢል አክለውም የክልሉ ቴሌቪዥን በክልሉም ሆነ በአምስቱ የአለም አህጉራት ለሚኖሩ የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራ ማህበረሰብንና ነዋሪዎች ስለሀገራቸውና ስለተወለዱበት ክልላቸው መረጃ በማሰራጨትና ተደራሽ በማድረግ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ መሆኑን አስታውሰዋል።

በተጨማሪም በክልሉ መንግስትና ህዝብ እየተከናወኑ ያለው የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እንዲሁም በአጠቃላይ በክልሉ ላለው የቆዳ ስፋትና የክልሉ የተፈጥሮ እምቅ ሀብቶቻችን እንደሁም በክልሉ ላለው የቱሪዝም መስህቦችና ታሪካዊ ቅርሶችን ለክልሉ የአማረኛ ተናጋሪና ለአጠቃላይ የሀገራችን ህዝብ የክልሉን ዘርፈብዙ የልማት አውተሮችን ግንዛቤ ለማስጨበጥና የክልሉን ገጽታ ግንባታ ስራዎችን የአማርኛ ቋንቋ ስርጭቱ በከፍተኛ ደረጃ ያግዛል ብሏል ኢንጅነር ኢድሪስ።

በመጨረሻም የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ኢንጅነር ኢድሪስ ኢስማኢል ለክልሉ አማርኛ ተናጋሪ ማህበረሰብን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

*********

Guest Author

more recommended stories