የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከ1500 በላይ እስረኞችን ለቀቀ

(አብዱረዛቅ ካፊ/ESMMA)

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት አብዲ መሀሙድ ኡመር ከ1500 በላይ ታራሚዎች በይቅርታ ለቋቸዋል።

ታራሚዎቹ በፀረ-ሰላምና በሌሎች ወንጀሎችም የተፈረደባቸው የነበሩ ሲሆኑ የክልሉ ምህረት ኮሚቴ የታራሚዎቹን ወንጀል በማጣራትና በመለየት በአሁኑ ወቅት እንዲለቀቁ ለክልሉ ፕሬዝዳንት ካቀረቡ በኋላ፤ ፕሬዝዳንቱ ደግሞ የኮሚቴውን ውሳኔ በመቀበል ከ1500 በላይ ታራሚዎች በይቅርታ እንድለቀቁ አደርገዋል።

በሌላ በኩል በክልሉ በሚገኙ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ያሉት ታራሚዎች ሁለት አይነት መሆናቸውም ተገልጿል። እነሱም:-

1. በክልሉ ፍርድ ቤቶች የተፈረደባቸውና ለፈዴራል ማረሚያ ቤት በአደራ መልክ የተሰጡ ሲሆኑ የመለቀቅ ጉዳያቸውም በክልሉ ይቅርታ ኮሚቴ የሚወሰን፤

2. በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተፈደረባቸውና የመለቀቅ ጉዳያቸውም በፈዴራል መንግስት የሚወሰን ናቸው።

በክልሉ መንግስት በፈዴራል ማረሚያ ቤቶች የነበሩ የሌሎች ብሔረሰቦች እስረኞች ስለተፈቱ፤ በፈዴራል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ የኢትዮጵያ ሶማሌ ታራሚዎችም በምህረት እንዲለቀቁ ዘንድ የክልሉ የይቅርታ ኮሚቴ በአክብሮት ጠይቋል።

በተጨማሪም እስረኞችን በምህረት መለቀቅ የመጀመሪያ ወይም የመጨረሻ ጊዜ ሳይሆን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የተለመደና የጥንቱ ባህል እንደሆነም አይዘነጋም።

********

Guest Author

more recommended stories