የስኳር ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ሽፈራው ጃርሶ ጋዜጣዊ መግለጫ (+Audio)

በእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ የሀገሪቷን ግዙፍ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም እና ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ የስኳር ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ጄኔራል ሚኒስተር ሽፈራው ጃርሶ ለጋዜጠኞች የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ (ኦዲዮ)፡፡

ለአድማጭ ያጥር እና ይመች ዘንድ የጥያቄዎቹን ዝርዝርና የአቶ ሽፈራው ጃርሶ መልስ የሚገኝበትን ደቂቃ ዘርዝረን አስፍረናል፡፡

[የመጀመሪያው 15 ደቂቃ የአቶ ሽፈራው ጃርሶ መክፈቻ ገለጻ ነው]

ጥያቄዎች እና ምላሹ የሚገኝበት ደቂቃ

• በጣና በለስ ጉብኝቴ ላይ እንዳየሁት በተለይ ፋብሪካው በ2007 ታህሳስ ይደርሳል የሚለውን ለማመን ይከብዳል። እውነት ለታህሳስ/ጥር 2007 ይደርሳል? (16:00ኛ ደቂቃ ላይ)

• ለወልቃይት ስኳር ፕሮጀክት የፋይናንስ ምንጭ ተገኝቷል ፡፡ ስራው አሁን በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? (17:04ኛ ደቂቃ ላይ)

• የራስን አቅም የመገንባት እና በሀገሪቱ የሰው ሀይል የመስራት ብቃት አሁን በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? (32፡40ኛ ደቂቃ ላይ)

• ከስኳር ምርት ጋር ተያያዥ ምርቶችን ጥቅም ላይ የማዋል ሁኔታ እንዴት ነው፡፡ (37፡42ኛ ደቂቃ ላይ)

• እንደተባለው የእቅዱ 70% ከተሳካ አቅርቦት ከፍላጎት በላይ ይሆናል፡፡ ለዚህ ትርፍ ምርት ገበያ ለማፈላለግ እና ተወዳዳሪ ለመሆን ምን እየተሰራ ነው? (41፡59ኛ ደቂቃ ላይ)

• አብዛኛዎቹ ፋብሪካዎች አሁን ካሉበት ደረጃ አንፃር ለትራንስፎርሜሽን እቅዱ መጠናቀቅ በቀረው አንድ አመት ውስጥ ስራ መጀመር ይቻላቸዋል?

• ከመሰረተ ልማት መሟላት ጋር በተያያዘ በበለስ የስኳር ፕሮጀክት ጉድለቶች ተመልክተናል፡፡ (48፡19ኛ ደቂቃ ላይ)

• የወልቃይት ስኳር ፕሮጀክት ላይ ኮንትራክተሩ የተሰጠውን 10 ኪ.ሜ አጠናቆ ቀሪው 65 ኪ.ሜ የካናል ስራ እሰኪሰጠው እየጠበቀ ነው፡፡ ለምን እንዲያቆም ተደረገ? (52፡47ኛ ደቂቃ ላይ)

• የተንዳሆ የስኳር ፕሮጀክት በጣም ዘግይተዋል፡፡ ለምን? 55፡45ኛ ደቂቃ ላይ)

• የስኳር ፕሮጀክቶቹ በተጎዳኝ የኤሌትሪክ ሃይል አንደሚያመነጩና ወደ ዋናው ግሪድ እንደሚያስገቡ ይገልፃል፡፡ ከ 10ሩ ፋብሪካዎች ምን ያህል መጠን የኤሌትሪክ ሀይል ይጠበቃል? (01፡05፡27ኛ ደቂቃ ላይ)

• በተንዳሆ የአካባቢው outgrowth አርሶ አደሮች በክፍያ ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ይናገራሉ፡፡ (01፡11፡46ኛ ደቂቃ ላይ)

• በሰራተኞች ዘንድ የአካል ደህንነት መጠበቂያ አልባሳት አለመኖር ታዝቤያለሁ፡፡ (01:14:14ኛ ደቂቃ ላይ)

• ለምርት ገበያ የማፈላለግ እና የጥራት ሁኔታ ምን ላይ ነው? (01፡17፡22ኛ ደቂቃ ላይ)

• የሀገርን አቅም መገንባት ተገቢ ቢሆንም በቀሰም የ METEC የግድብ ስራ አፈፃፀም የሀገር ሀብት ከማባከን አይተናነስም፡ (01፡19፡42ኛ ደቂቃ ላይ)

• ህንዶቹ በክፍያ ላይ ኢትዮጲያውያን ሰራተኞችን እንደሚበድሉ ሰምተናል ፡ እናንተ ውስጥ ገብታችሁ እንደምትከፍሏቸው እነሱ ግን መክፈል እንደማይፈልጉ ተረድተናል። (01፡24፡55ኛ ደቂቃ ላይ)

• የስኳር ተረፈ ምርት ኢታኖል በ 13 ብር ወጪ ተመርቶ የሚሸጠው ግን በ9ብር ነው ፡፡ይህ ኪሳራ አይሆንም? (01፡25፡52ኛ ደቂቃ ላይ)

• በወንጂ ሁለት የስኮር ፋብሪካዎች (ወንጂና ሸዋ) እና አንድ የከረሜላ ፋብሪካ እንዲፈርስ ተደርጓል፡፡ አድሶ መጠቀም አይቻልም ነበር? (01፡29፡03ኛ ደቂቃ ላይ)

• በአሚባራ የስኳር ፕሮጀክቱ ለጥጥ የተዘጋጀ መሬትን ተጠቅሞል፡፡ ይህ በትራንስፎርሜሽን እቅዱ ለጨርቃ ጨርቅ የተቀመጠውን እቅድ አያደናቅፍም? (01፡30፡53ኛ ደቂቃ ላይ)

• የኦሞ ኩራዝ ፕሮጀክት የአገደ ተከላ ተጠናቋል ፡ ፋብሪካው ግን ብዙ እንደሚቀረው አይቻለሁ ፡፡ በዚህ ሁኔታ በነሃሴ 2006 የሙከራ ምርት ይጀምራል መባሉን ቢያብራሩልኝ፡፡

• በኦሞ አርብቶ አደሮች ዘንድ ወደ አርሶ አደርነት የመቀየር ፍላጎት እንዳለ ተገንዝበናል፡፡ ይህን ለማገዝ ምን ታስቧል? (01፡34፡00ኛ ደቂቃ ላይ)

• የፊንጫ ፕሮጀክት በካይዘን ትግበራ 30 ሚሊየን ብር አትርፏል፡፡ ይህንን ሌሎች ፕሮጀክቶች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ታስቧል? (01፡37፡13ኛ ደቂቃ ላይ)

**************

**************

Fetsum Berhane is an Ethiopian resident, economist researcher and a blogger on HornAffairs.

more recommended stories