ሚኒስትር ሽፈራው:- በቅርቡ ለሚመረቀው ተንዳሆ ስኳር መዘግየት ህንዶችን ወቀሱ

በሚንስትር ማዕረግ የስኳር ኮሬፖሬሽን ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ሽፈራው ጃርሶ በግንባታ ላይ ያሉትን 10 የስኳር ፕሮጀክቶች ጎብኝተው ለተመለሱ ጋዜጠኞች ግንቦት 13 2006 በሰጡት ሰፊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከዳሰሷቸው ጉዳዮች አንዱ – ዘግይቶMinister Sheferaw Jarso እየተጠናቀቀ ያለው የተንዳሆ የስኳር ፕሮጀክት መዘግየት ላይ የሰጡት ማብራሪያ ነበር፡፡

ተንዳሆ ስኳር ፕሮጀክት ግንቦት 30 ይጠናቀቃል ያሉት አቶ ሽፈራው በፕሮጀክቱ ስለተሳተፉት የህንድ ድርጅቶችና የብድር ስርዐቱ ሲያብራሩ የተጠራቀመ ብስጭት ይነበብባቸው ነበር፡፡

ከህንዱ ኮንትራክተር ጋር የነበረውን ሁኔታ ሲያስረዱ፡- ተንዳሆን ስንጀምር በራሳችን ለመስራት ካፒታል አልነበረንም ፤ ገንዘብ ከዛ እናገኛለን ብለን በነሱ እጅ ወደቅን ፤ የድህነት ምልክት ነው ብለዋል፡፡ አቶ ሽፈራው አክለውም፡- በአንድ ወቅት መንግስት አቅም ገንብተናል በራሳችን ገንዘብ እንሄዳለን ብሎ ኮንትራቱ ለመሰረዝ አስቦ እንደነበር፤ ነገር ግን እዚህ ደረጃ ላይ ደርሶ መሰረዝ ፕሮጀክቱን ይበልጥ ማዘግየት ነው – ጠቀሜታ የለውም ብሎ እንደተወው አስረድተዋል፡፡

ሚኒስትር ሽፈራው ጃርሶ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተንዳሆ የስኳር ፕሮጀክትን አስመልክቶ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጧቸውን ማብራሪያዎች ከዚህ በታች በጽሁፍ አቅርበነዋል፡፡
*********

ጥያቄ ፡- ህንዶቹ በክፍያ ላይ ኢትዮጲያውያን ሰራተኞችን እንደሚበድሉ ሰምተናል እናንተ ውስጥ ገብታችሁ እንደምትከፍሏቸው እነሱ ግን መክፈል እንደማይፈልጉ ተረድተናል።

ሚኒስትር ሽፈራው፡

ይህ ከህንድ ጋር ያነሳኸው – አስቸጋሪዎች ናቸው ክፍያ ላይ ፡ አገራቸው….. ሰው ተርቦ ለዘመዶቻቸው….ገንዘቡን እዚው አይከፍሉም፡፡ ሰሞኑን ይህንን ሁሉ እየተቆጣጠር ነው፡፡ ቁጭ ነው የሚሉት ስራ ትተው፡፡ አወያይተን እዚው እንዲከፍሉ እያደረግን እየታገልን ነው የምንሄደው ከእነሱ ጋር፤ እና በጣም አስቸጋሪ ነው ማኔጅመንቱ፡፡ this is not our duty::የኮንትራክት ሲስተም ቢሆን ካልሰራ ማሰናበት [ግን ያንን] ማድረግ አንችልም፡፡ ወይ ከመጀመሪያ ጀምሮ ያንን አልሰራን፡፡ ገንዘብ ከዛ እናገኛለን ብለን በነሱ እጅ ወደቀን this is all problem የድህነት ምልክት ነው። እንጂ ከመጀመሪያው ጀምሮ ቢኖረን…. ራሳችን እንየወሰንን – አሁን እንደምናደርገው – በራሳችን እንሄድ ነበር፡፡ እና ይሄንንም ያለውን ችግር መረዳት ጥሩ ይመስለኛል፡፡

ጥያቄ፡- የተንዳሆ የስኳር ፕሮጀክት በጣም ዘግይቷል። ለምን ?

ሚኒስትር ሽፈራው፡

ተንዳሆ ከተጀመረ ረጅም አመት ነው። ከኮሬፕሬሽኑ በፊት ንግድና ኢንዱስተሪ ሚኒስተር በነበረበት ጊዜ ማለት ግዜ ነው የተቋቋመው። አጋጣሚ ሆኖ በዛን ግዜ የተንዳሆ ቦርድ ሰብሳቢ ስለነበርኩ፤ ስራውም ላይ ስለተሳተፍኩ፡ ስራውን አውቀዋለሁ፡ ለመመለስ አያቅተኝም ከዛን ግዜ ጀምሮ ስለተሳተፍኩ።

የተንዳሆ አጀማመራችን ችግር ያለው ነው። ተንዳሆን ስንጀምር እንደሀገር ካፒታል የለንም ፤ በራሳችን ለመስራት [አቅም] አልነበረንም። እንደዚህ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን እንጀምራለን ብለን ገና አላሰብንም፤ ስለዚህ ፋይናንስ ማፈላለግ ነበረብን። [በዚህ ግዜ ነው] ከህንድ ፋይናንስ እንሰጣለን የሚል ሃሳብ የተፈጠረው፡፡

ሲፈጠር ለህንድ ኩባንያዎች… ግዜ ለመሻማት ተብሎ ambitions ስለነበርን… ጨረታ አወጣን ፡፡ የህንድ ካምፓኒዎች አሸነፉ፡፡ የፊንጫ ተጨማሪ እና አዲሱን የወንጂ ፋብሪካ – ወንጂም አዲስ ፋብሪካ ነው የድሮው dismantled ሆኖ [እንዳዲስ ነው የተሠራው]፡፡ ጨረታዎችን ከጨረስን በኃላ የህንድ መንግስት ገንዘቡን ይፈቅዳል ፡፡

የህንድ መንግስት ገንዘቡን ሲፈቅድ የተደረገው ሁኔታ E.P.C. (Engineering Procurement Contract) ካልመጣ ገንዘቡን አንለቅም ተባለ። ስለዚህ ኢ.ፒ.ሲ ኮንትራት የሚያደርግ፡ አንድ ላይ የሚሰራ ካልመጣ ተባለ። ገንዘብ ማግኘት ስላለብን እሱን ፍለጋ ተደረገ። ስለህንድ ሲስተም – ኦፊሻል በሆነ መንገድ ብዙ የማይነገር ነገር አለ፡፡ (ሳቅ)-

ያ ካምፓኒ ተመረጠ by any means፡፡ ያው የእነሱ መንግስት ኢ.ፒ.ሲ ይሠራል የሚለው ያ ካምፓኒ ተገኘ። ከዛ በኃላ እሱ ወደ ማስተባበር ሲገባ፤ እኛ ከመረጥናቸው [ኩባንያዎች] አንዳንዶቹን ወደ መተው እና የራሱን ወደመምረጥ ሄደ። ሁለተኛ፤ በግል እስከማውቀው ድረስ ኩባንያዎቹ ፍርድ ቤት ሁሉ ተካሰዋል፤ እስካሁን ፍርድ ቤት ላይ ነው ያሉት፡፡ የሆነ ማበረታቻ አለ በውጪ ሀገር ሲሰራ። ትልቁ ችግራቸው፡ ኤክስፖርት እንሴንቲቭ አለው አንድ ፋብሪካ ሲሰጠው። እዛች ብር ላይ፡ ያችን ብር ‹‹ኢ.ፒ.ሲ እኔ ልውሰድ፡ ፋብሪካው የሚያመርተው ላይ እኔ ልውሰድ ነው›› ትልቁ ጠብ፡፡ የራሳቸው የውስጥ ጠብ ነው፤ እኛ ኢ.ፒ.ሲ መስጠት ነው። እሱ በጣም ፕሮጀክቱን አዘግይቶታል፡፡ በኛ ስህተት አንድ አመት ተኩል፡ ጎርፍ ተጥለቅልቆ ቆሟል፡ መጀመሪያ ላይ በዛ ምክንያት መዘግየት ተፈጥሯል፡፡

ከዛ በኃላ በሲስተሙ ይሄ ኮንትራቱን የወሰደው ኩባንያ ከማስተባበር ውጪ የራሱ ፋብሪካዎች የሉትም፡፡ ለሌሎች ሥራውን በመስጠት ከsub vender ጋር ነው የሚሰራው ፡፡ ከነሱ ጋር ፋይናንስ የመልቀቅ የመለቃቀቅ completely አስቸጋሪ የሆነ አካሄድ ነው። እቃውን አምርቶ በግዜ እያመጣለትም፡ ወዘተ… የቅንጅት ችግር ነው ፡፡ ይህንን ስል እኛም የማኔጅመንት እጥረት የለብንም አልልም ገና በቂ አቅም አልፈጠርንም፡፡ እና…. ችግሩ እዛ ላይ ነው፡፡

ያልተደረገ ጥረት የለም፡፡ በኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሥር ሁኖም ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመ በኃላም ከፍተኛ ጥረት ነው የተደረገው። አቶ አባይ ፀሐዬ እያሉም ከፍተኛ ጥረት ነው የተደረገው፤ እኔም ከመጣሁ በኃላም እንደዚሁ ነው እያደረግን ያለነው፡፡

[በመሠረቱ]ኢ.ፒ.ሲ ኮንትራት ማለት እንጂነሪንጉንም ይሰራል፣ ኮንስትራክሽኑንም ይሰራል፣ ያስረክባል፤ ውስጥ አትገባም አንተ።

አሁን ከዛ ውጪ አልፈን ነው፤ እያንዳንዱ vender ላይ ያልተሰጠውን ገንዘብ ምንድን ነው እያልን ፈትሸን ነው እያሰራን ያለነው። በስምምነቱ መሰረት ኮንትራቱን መሰረዝ ትችላለህ፡ ፡፡ ግን እዚህ ደረጃ ላይ ደርሶ ኮንትራቱን መሰረዝ አደጋ ነው ራሱ። ፋይናንሱም ከነሱ ነው፣ ሌላው ውስብስብ ተዳምሮ…. የባሰ ፕሮጀክቱን ማዘግየት ነው እንጂ ጠቀሜታ የለውም፤ እንደ ሀገር ጠቀሜታ የለውም፡፡

በአንድ ወቅት እንዲሰረዝ መንግስትም አስቦ ነበር። ይሰረዝና፡ አቅም ገንብተናል በራሳችን ገንዘብ እንሄዳለን እስከማለት ድረስ ተደርሶ ነበር፡፡ ግን ከህንድ ጋር ካለን ግንኙነትም አንፃር ብንቀጥልበት የሚል ውሳኔ ነው ተወስኖበት የተኬደው። ዋናው ትልቁ እሱ ጋር ነው ፤ ሁለተኛው ራሳችንም ያንን ራሱ ማኔጅ አድርጎ ያለመምራት ችግሩ ነበረብን፡፡ የእነሱ complication ብቻ አይደለም የእኛም [ድክመት] ቀላል አይደለም የሚል እምነት አለኝ፡፡ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመ ጀምሮ እንደተደረገውም ማድረግ ይቻል ነበር።

ግን አስቸጋሪዎች ናቸው በጣም፤ የገጠመኝ ፡፡ አጠቃላይ የህንድ ካምፓኒዎች አስቸጋሪዎች ናቸው ማለት አይቻልም። ከያዝነው ኢ.ፒ.ሲ ጋር ግን ከፍተኛ ችግር ነው የገጠመን እና ለማንኛውም አሁን መጨረሻ ላይ ደርሰናል ፤ እና ለጥያቄህ መልሱ ፡ አዎን በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ያልቃል ነው። …. አብዛኛው አልቋል dry-test ተደርጓል እኔ ራሱ ሳምንት እዛ ነበርኩ፡፡

ቢዘገይ አሁን ያልነውን ቴስት ሲያደርጉ ተጨማሪ ሁለት ሶስት ቀን ፡ እስከ ግንቦት 30 ድረስ በእርግጠኝነት ያልቃል የሚል ግምት ነው ያለን እና ከበፊቱ የበለጠ፤ በፊት ምኑንም አናውቀውም ነበር፡፡ እቃ መጣ ይባላል ከዛ እቃቸውን እዚህ አምጥተው ይደብቁብናል፡ ከራሳቸው ችግር ስላለ።

ስለተንዳሆ ብዙ የዘረዘርኩት ብዙ ስለሚጠየቅ ነው ፡፡ በዛ ደረጃ ነው ፡ I hope ያልቃል የሚል ግምት ነው ያለን። ምን እንሚመጣ ደግሞ አብረን እናያለን ፤ ቃሉ ካልሰራም ያው በዛው አብሮ ማየት ነው የሚሻለው፡፡

*******
* ሽፈራው ጃርሶ ስለተንዳሆ የስኳር ፕሮጀክት የሰጧቸውን ማብራሪያዎች ከታች ያዳምጡ፡፡

***********

Fetsum Berhane is an Ethiopian resident, economist researcher and a blogger on HornAffairs.

more recommended stories