የሺሻ ማስጨሻና የጫት ማስቃሚያ ቤቶችን ሕገ-ወጥ የሚያደርግ ህግ እየተዘጋጀ ነው

በሺሻ ማስጨሻና ጫት ማስቃሚያ ቤቶች ላይ ህጋዊ እርምጃን መውሰድ የሚያስችል ህግ እየረቀቀ ነው ተባለ።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ሀላፊ የሆኑት ምክትል ኮማንደር አበራ ጉሊና ፤ የህጉ መዘጋጀት እስካሁን ይወሰድ የነበረውን የማሸግ ብቻ እርምጃ ከፍ በማድረግ ድርጊቱን ለማሰቆም ያግዛል ብለዋል።

እስካሁን በድርጊቱ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ማስቀጣት የሚያስችል ህግ ባለመኖሩ ፥ የሺሻ እቃዎችን ከማቃጠልና ቤቶቹን ለጊዜው ከማሸግ ያለፈ እርምጃ አይወሰድም ነበር ነው ያሉት።

አዲስ የሚረቀው ህግ ግን ድርጊቱን በዘላቂነት ለመከላከል እንደሚያስችል ተናግረዋል።

ፍትህ ሚኒስቴርም የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ለጉዳዩ የህግ ማእቀፍ የማዘጋጀት ስራ እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።

የህግ ማዕቀፉ እስኪጠናቀቅ ድረስም ፖሊስ የጀመረውን ሰራ የሚቀጥል ሲሆን ፥ ህብረተሰቡም ትብብሩን ሊያጠናክር እንደሚገባ ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

*********
ምንጭ፡- ፋና፣ መጋቢት 10-2006፣ ርዕስ ‹‹በሺሻ ማስጨሻና ጫት ማስቃሚያ ቤቶች ላይ ህጋዊ እርምጃን መውሰድ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው››፣ በብርሀኑ ወልደሰማያት

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories