የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦህዴድ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ድርጅቱን የሚመሩትን መሪዎች መረጠ።
በምርጫውም አቶ ሙክታር ከድር የድርጅቱ ሊቀመንበር፣ወይዘሮ አስቴር ማሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነዋል።
አቶ ሙክታር በፌዴራል መንግሥት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር አስተባባሪነትና በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነት በማገልገል ላይ ናቸው።
ወይዘሮ አስቴር የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል።
ድርጅቱን በሊቀመንበርነት የመሩት አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ በጤና ችግር ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል።
አቶ ዓለማየሁ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድርነት መምራታቸውን ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል።
የክልሉ መንግሥት ምክር ቤት(ጨፌ ኦሮሚያ)በሚጠራው ጉባዔ የክልሉን ርዕደ መስተዳድር ይሰይማል ተብሎም ይጠበቃል።
**********
ምንጭ፡- ኢዜአ – የካቲት 20/2006