ኢትዮጵያና ታንዛንያ ለኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ ድርድር ስምምነት ልትፈጽም ነው።

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2018 ፤ 250 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ለታንዛንያ ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት ልትፈጽም ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የውጭ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ሽያጩን ለማደረግ የሚረዳ ድርድር በመጪው መጋቢት ወር ይከናወናል ብለዋል።

አቶ ምስክር ፥ ለሱዳን 100 ሜጋ ዋት ሃይል ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት መፈረሙንም አክለዋል።

በ2017ም ፤ 400 ሜጋ ዋት የኤሌክትክ ሃይል ለኬንያ ለመሸጥ የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ እየተገነባ ይገኛል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ ለጁቡቲ በምትሸጠው 50 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል በየወሩ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር እያገኘች መሆኑንም ተናግረዋል።

*********
ምንጭ፡- ፋና – የካቲት 15 ፣ 2006፣ ‹‹በኤሌክትሪክ ሀይል ሺያጭ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ ሊደራደሩ ነው››

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.