የቤንሻንጉል ፕ/ት: ተፈናቃዮቹ ኦሮሞዎችም ናቸው – አጣርተን እርምጃ እንወስዳለን

ባለፈው ሳምንት አዲስ አድማስ ጋዜጣ የዘገበውና (እዚህ ብሎግ ላይም የወጣ) ዜና፤ በበቤንሻንጉል ክልል የሰፈሩ ዜጐች “ሕገወጥ” ተብለው እንደተባረሩ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ዜናው እንዳለው ከሆነ፡-

 “በሚኖሩበት አካባቢ የእርሻ ቦታ በማጣታቸውና የተሻለ ሥራ ፍለጋ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ከአማራ ክልል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ ተዘዋውረው የከተሙ በርካታ ሰዎች በወረዳው ባለሥልጣናትና ፖሊሶች፤ ሰብአዊ መብታቸው ተጥሶ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን…ገለፁ፡፡

የያሶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ሻምበል ዳኛ በበኩላቸው ‹‹ከየትኛውም ክልል የሚመጡ ሰዎች ለወረዳው ካላሳወቁና ካላስፈቀዱ ሕገወጥ በመሆናቸው ወደ የመጡበት እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ደርሰናል›› ብለዋል፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደሚሉት፤ ካለፉት ስምንት ዓመታት ጀምሮ ይኖሩበት ከነበረው ክልል የመሸኛ ደብዳቤ አምጥተው በያሶ ወረዳና በየቀበሌዎቹ የነዋሪነት መታወቂያ ስለተሰጣቸው ጎጆ ቀልሰው ይኖሩ እንደነበር ይናገራሉ፡፡” (ሙሉውን ለማንበብ –  በቤንሻንጉል ክልል የሰፈሩ ዜጐች “ሕገወጥ” በሚል ተባረሩ – click here)

ተመሳሳይ ጭብጥ ያላቸው ዘገባዎች በተለያዩ ሚዲያዎች በተለያየ አቀራረብ የቀረቡ ሲሆን፤ እንደተለመደው ኢሳት ጉዳዩን አንድ ደረጃ ከፍ በማድረግ 59 የተፈናቀሉ ሰዎች በጉዞ ለላይ ሞቱ ብሏል፡፡ ይሁንና የመኢአድ (የኢንጅነር ሀይሉ ሻውል ፓርቲ) ሀላፊዎች ስለሞት መረጃ እንደሌላቸው ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

በአሜሪካ ሀገር የሚገኝ በአማርኛ የሚተላለፍ የኢትዮጲያውያን ሬዲዮ (Ethio-CivilityMap of Benishangul-Gumuz Region - Ethiopia forum) ጉዳዩን አስመልክቶ ከቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት አሕመድ ናስር ጋር ቃለ-ምልልስ ከትላንት ወዲያ አድርጓል፡፡

ወደ 30 ደቂቃ ከወሰደው ቃለ-መጠይቅ ውስጥ በርዕሰ-ጉዳዩ ላይ ከሰጡት ምላሾች የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

ከተሞችን አስመልክቶ፡-

ከከተማ የተፈናቀሉ ሰዎች ስለመኖራቸው መረጃ የላቸውም፡፡ ሊፈፀም የሚችልበት አግባብም የለም፡፡ የአካባቢው ተወላጅ በሆቴልና መሰል ንግዶች መሠማራት ባህል እንደሌለው እና ባለስልጣኖቹ ራሳቸው በመሀል ሀገር ሰዎች ንብረት በሆኑ ሆቴሎች እንደሚጠቀሙ ጠቁመዋል፡፡ ‹ችግሩ› በገጠር እንጂ በከተማ የለም ብለዋል፡፡

ገጠሩን አስመልክቶ፡-

– በክልሉ ከማጂ ዞን ባለ አንድ ወረዳ 1700 ሰዎች እንዲነሱ እንደተደረጉ መረጃ እንዳላቸው ገልፀዋል

– የሞተ ሰው የለም/መረጃ የለኝም/ ካሉ በኋላ፤ እንዲያውም ከወረዳው ባገኙት መረጃ መሠረት ተወያይተውና ሕገወጥ መሆናቸውን ተማምነው፣ ከ 20-25 ቀን ጊዜ ተሰጥቷቸው ምርታቸውን ሰብስበውና ራሳቸው መኪና ተከራይተው እንደሄዱ ነው ብለዋል

– ጉዳዩን ያስፈፀመው የወረዳው መስተዳድር መሆኑን፤ ‹ክፍተት› መኖሩን እና ሰው ልከው ማጣራታቸውንና ያም ሰው አጠናቅቆ ሐሙስ እንደተመለሰ ገልጸዋል

– በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር የአማራ ክልል <ጓዶች> መምጣታቸውን፤  አርብ መረጃ መለዋወጥና  ውይይት እንደሚጀምሩ ጠቁመዋል፡፡

– የተነሱት ሰዎች አማራ ብቻ ሳይሆኑ ኦሮሞዎችም ጭምር ናቸው (ሌሎችም ብሔሮች ሊኖሩ ይችላሉ)፤ ዞኑንም የሚዋሰነው ከኦሮሚያ ክልል ጋር ነው ብለዋል፡፡

– አላግባብ የተፈፀመ ነገር ካለም ማስተካከያ እንደሚደረግ እና በአጥፊ ሀላፊዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ገልፀዋል፡፡

– በተጨማሪም ከ4 ዓመት በላይ የኖሩ፣ መታወቂያ የተሰጣቸው ሰዎች ተፈናቅለው ከሆነ እሱን  ማስተካከል ይገባል ብለዋል፡፡

እንደአጠቃላይ የገጠሩን ሁኔታ አስመልክቶ ሲናገሩም፡-

– ከሌላ አካባቢ ሰዎች የሚመጡበት 2 ዋነኛ መንገዶች መኖራቸውን፤ እነርሱም፡- ‹‹ጉልበት ሽጦ›› ለመኖር ተቀጥረው የሚመጡ ወይም ጫካ መንጥረው በእርሻ የሚሠማሩ መሆናቸውን የተናገሩ ሲሆን፤

የመጀመሪዎቹን በተመለከተ መብታቸው መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ ‹‹ጉልበቱን ሸጦ የሚኖር ካለ፤ ዛሬም ነገም ይኖራል: ከወጣም ይገባል›› ብለዋል፡፡

ሁለተኛውን ዓይነት ማለትም ‹‹ጫካ መንጥረው በእርሻ የሚሠማሩ›› ያሏቸውን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት ሲጠቃለል፡-
‹‹ፖሊሲው›› የሚለው ሰፈራ በየክልሉ ውስጥ ብቻ እንደሚካሄድ፤ ክልሎች ለሰፈራ ያዘጋጁት መሬት ካለቀ እና ከክልል-ክልል ሰፈራ አስፈላጊ ከሆነ የሚመለከታቸው ክልሎች ተነጋግረው የሚያስፈጽሙት እንደሚሆን ከጠቀሱ በኋላ፤
እስካሁን በተለያየ መንገድ (ሕጋዊ ባልሆነም መንገድ) ገብተው የቆዩና በነዋሪነት የሚታወቁትን በተመለከተ የሚስተናገዱበት መንገድ እንደሚፈለግ፤ ለቀጣይ ግን ይህ ቋሚ አሠራር ሊሆን እንማይችልና እንዲያውም ማበረታታት እንደሚሆን፤ ይህም ለሰዎቹ ለራሳቸውም ለክልሉም ጥሩ እንዳልሆነ ሀገር ይወቅልን ብለዋል፡፡

——

ማስታወሻ፡- ይህ ጭማቂ ሙሉውን ቃለ-መጠይቅ ዳውንሎድ (Download) ማድረግ ለሚቸግራቸው አንባቢያን ለመርዳት፤ በችኮላ የተጻፈና ቁንጽል በመሆኑ፤ ሙሉውን ቢያዳምጡት ይመከራል፡፡

Download here (link) – የፕ/ት አሕመድ ናስር ጋር ቃለ-ምልልስ (size: 9.4 mb)

* For a better quality – listen here (link).

———

My comment:

What I gather from the Benishangul regional state President Ahmed Nasir’s interview about the recent evictions is that:

1/A scenario what political scientists call “local tyranny” – Wereda officials deciding matters of this scale and the President referring to their report as self-evident truth

2/Typical case of a higher official saying “I didn’t know” (Ethiopian bosses everywhere love this excuse)

3/A huge deficit of common understanding on the issues at stake

4/The absence of sufficient policy & legal framework, though we have been hearing about this kinds of issues for more than a year.

The bottom line: While the regional officials seem to be confusing federalism with separate statehood, it is the federal government who should provide sufficient legal framework to enable Ethiopians settle in any region they like – as long as they fulfill clearly stated legal requirements.

********

Daniel Berhane

more recommended stories