ለከተማ ድሆች የተዘጋጀው ‹‹የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት›› ፕሮግራም ይዘት

ለከተማ ድሆች ማሕበራዊ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል የተባለለት ፕሮግራም የከተማ ልማት ቤቶች እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የዘርፍ መሥሪያ ቤቶች በጋራ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡

‹‹የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት›› የሚል ስያሜ የተሰጠው ፕሮግራም ግብ ‹‹በሚቀጥሉት 10 አመታት ከአጠቃላይ ድህነት ወለል በታች ያሉ90% የሚሆኑ ስራ አጦች፣ ሥራ ፈቶች እንዲሁም ለማህበራዊ ኑሮ ችግርና ጠንቅ የተጋለጡ ዜጎች ወደ ስራ እንዲሰማሩና 10% የሚሆኑት የመስራት አቅም የሌላቸው የማህበራዊ ጠንቅ ሰለባዎች የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት እንዲያገኙ›› ማድረግ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ስለፕሮግራሙ ከሚያትት በዚህ ወር ከተዘጋጀ የገለፃ ሰነድ (power point  document) የተወሰዱ ነጥቦችን ከዚህ በታች አትመናቸዋል፡፡

——–

መግቢያ

* ሀገራችን ባለፉት ስርዓቶች የምትታወቀው የጦርነትና የረሀብ ተምሳሌት ሆና ነበር፡፡

* ልማታዊ መንግስታችን ይህንን ገፅታ በመለወጥ ሰላምና ዲሞክራሲ በሀገሪቱ በማስፈን ልማትን አፋጥኖ ዋነኛጠላታችንየሆነውንድህነትለማጥፋት እየተረባረበ ይገኛል፡፡

* ሀገራችን ከድህነት ወጥታ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮችተርታለማሰለፍየሚያስችሉ ፖሊሲዎች፣ስትራቴጂዎችናፕሮግራሞችቀርፆ በመተግበር ዘርፈ ብዙ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛል፡፡Photo - Addis Ababa's slum

* ከእነዚህም መካከል የገጠር ምግብ ዋስትና ፕሮግራም፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ፣ የከተማ ልማት ፖለሲና ስትራቴጂዎች፣የኢንቨስትመንትፖሊሲ የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች የኃይል ማመንጫዎችና ሌሎች ግዙፍ የመንግስት ፕሮጀክቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

* እነዚህን ፖሊሲዎች በህዘቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲተገበሩ በማድረግ በርካታ የስራ ዕድሎች ተፈጥረዋል፣ ለኢንዱስትሪው ልማት ሽግግር መሰረት የሆኑ በርካታ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተፈጥረዋል፣ በአጠቃላይ በሁሉም ዘርፍ ዓለም ያደነቃቸው ስኬቶች እየተመዘገቡ ነው፡፡

* በየዘርፉ በርካታ ስኬቶች እየተመዘገቡ ቢሆንም ገና ያልተሻገርናቸው ችግሮች መኖራቸው ግን አልቀረም፡፡ ከእነዚህም መካከል የምግብ ዋስትና ዕጦት ተጋላጭነት አንዱ ነው፡፡

* በከተሞች የሚታዩት የማህበራዊ ኑሮ ጠንቆችና ችግሮች  ከከተሞች ህዝብ ዕድገትና ኢንዱስትሪ መስፋፋት ጋር  በመጠንና በዓይነት እየበዙ የሚሄዱ ናቸው፡፡

* በአምራችነትተሰማርተውለራሳቸውናለሀገራቸው  ሊጠቅሙ የሚችሉ በርካታ ዜጎች በስራ ላይ ባላቸው የተዛባ  አመለካከት እና በሌሎች ችግሮች ምክንያት ለስራ አጥነት፣  ለስራ ፈትነት፣ ለህገ ወጥ ስደት፣ ለጎዳና ተዳዳሪነት፣  ለለምኖ አዳሪነት፣ ለሴተኛ አዳሪነት እና ለሌሎችም  የማህበራዊ ኑሮ ጠንቆችና ችግሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ፡፡

* ይህ ሁኔታ ደግሞ በዜጎቻችን ስብዕናና በሀገራችን ገፅታ ላይ  አሉታዊ ተፅዕኖ ከማሳደሩም ባሻገር ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ  አስተዋፅኦ ሊያደርግ የሚችለውን የሰው ኃይል እያባከነ  ይገኛል፡፡

* በመሆኑም የዜጎች የምግብ ዋስትና ሳይረጋገጥ፣ የተሟላ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እውን ሳይሆን ወደ ታሰበውራዕይለመድረስአዳጋችመሆኑን በመገንዘብ መንግስት ዘላቂ የስራ ዕድል በመፍጠርና ተከታታይነትያለውየተሃድሶናየመከላከል አገልግሎትለሁሉምዜጎችለመስጠት የሚያስችለውን የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ ቀርጿል፡፡

* በፖሊሲው መነሻነትም በሁሉም ባለድርሻና ተባባሪ አካላት ተሳትፎ ተግባራዊ የሚሆን የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ስትራቴጂና ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡

– ለከተሞች የምግብ ዋስትና ችግር መባባስ እንደ  መንስኤነት የሚወሰዱት

– በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው የተዛባ የስራ ባህል፣

– ከሀብት ጋር ባልተመጣጠነ የህዝብ ዕድገት ምክንያት  የእርሻ መሬት መጠንና ምርታማነት ከጊዜ ወደ ጊዜ  መቀነስ፣

– ደካማ የግብይት ሰንሰለት፣

– ዝቀተኛና አሰተማማኝ ያልሆነ የገቢ መጠን፣

– የአካባቢ ብክለት እና የአረንጓዴ ልማት ስራ አነስተኛ  መሆን፣

– የመኖሪያ ቤት፣

– የማምረቻና የመሸጫ ቦታዎች እጥረት፣

– ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ የህዝብ ፍልሰት፣

– የመልካም አስተዳደር እጦት፣

– የተጠናከረ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት አለመኖር፣

– የተቀናጀ ድጋፍ አለመኖር፣

– ለከተማ ግብርና ልማት በቂ ትኩረት አለመስጠት፣

– የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች እንዲሁም  የቤተሰብ መፍረስ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የከተማ ልማት ፖሊሲ ከከተሞች ምግብ ዋስትና   ማረጋገጥ አንጻር

– የከተሞችን አጠቃላይ ሚና የሚጠቁም ያልተማከለና  ያልተመጣጠነ አከታተምንና የገጠርና የከተማ እንዲሁም  የከተማና የከተማ ትስስርን የሚያሳይ አቅጣጫ የያዘ  ሆኖ ተቀርጿል፡፡

– የከተሞች ፈጣን ልማትን በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በከተሞች  መልካም አስተዳደርና አቅም ግንባታ፣ የከተማ መሬት  አጠቃቀምና ማኔጅመንት፣ በመኖሪያ ቤቶች ልማት፣  በተቀናጀ መሰረተ ልማት፣ የከተሞች ውበትና ጽዳት፣  በለውጥመሳሪያዎችአተገባበር፣በኮንስትራክሽን  ኢንዱስትሪ ልማትና ሪጉላቶሪ ስራዎች በመተግበር  ኢኮኖሚያዊ ምርታማነት፣ የሁሉም ተጠቃሚነት እና  በዘላቂነት ለኑሮ ምቹ የሆኑ ከተሞች ተፈጥረው ማየት  የሚያስችል ሆኖ የተቀረፀ ነው፡፡

የማህበራዊ ደህንነት ፖሊሲ የከተሞችን ምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ አንጻር

– ማህበራዊ ደህንነት በአካል ጉዳተኞች፣ በአረጋውያን፣  ህጻናት፣ ሴቶችና ወዘተ… ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆንለእነዚህየህብረተሰብክፍሎችበሃገሪቱ  ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅሰቃሴዎች  ውስጥ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ  ነው፡፡

– ሃገሪቱ ከድህነት ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት  መደገፍ እንዲችሉ ጥበቃ ማድረግና የማህበራዊ ደህንነት  ችግሮች እንዳይከሰቱ መከላከልን ያመለክታል፡፡

– የሚዘረጉት የማህበራዊ ደህንነት ፕሮግራሞች የቤተሰብና  የህበረተሰብን ደህንነት መሰረት ያደረጉ በመደበኛነት  መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት የሚተገብሩት  እንዲሁም መደበኛ ባልሆነ መንገድም ህብረተሰቡ እርስ  በርሱ የማህበራዊ ችግር ሲገጥመው የሚደጋገፍባቸውና  የሚተጋገዝባቸው ፕሮግራሞችን ያካትታል፡፡ 

የፕሮግራሙ አስፈላጊነት

– የገጠር ምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ማስፈፀሚያ ፕሮግራም  ተቀርፆ በሥራ ላይ የዋለቢሆንም የአፈፃፀም ቅኝቱ  ገጠር ላይ ያተኮረ በመሆኑ የከተሞችን ልዩ የምግብ  ዋስትና እጦት መንስኤዎች፣ ችግሮችንና መፍትሔዎችን  የቃኘ አይደለም፡፡

– በከተሞች እየተካሄደ ያለው የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ  ስራ በአጠቃላይ ሲታይ በመንግስት፣ በሃይማኖት  ተቋማት፣መንግስታዊባልሆኑድርጅቶችእና  በህብረተሰቡ አማካይነት በፖሊሲና በተቋማዊ አደረጃጀት  ባልተደገፈ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

– እስካሁን ባለው አሰራር ተጠቃሚ መሆን የሚገባቸው  የህብረተሰብ ክፍሎችን በአግባቡ መለየት ባለመቻሉ  አላግባብተጠቃሚነትንና(inclusiveerror)  የተጠቃሚነት ማጣት (exclusive error) የሚስተዋልበት ነው፡፡

– በሌላ በኩል ደግሞ ልዩ ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደስራ  ሊገቡ የሚችሉ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የማህበራዊ  ጥበቃ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን የሚገባቸውን  የህብረተሰብ ክፍሎች ያካተተ ስትራቴጂ አልነበረም፡፡

– በመሆኑም ይህን ያልተቀናጀ፣ ወጥ በሆነ የሥራ  አመራር ሥርዓት ያልተመራውን የከተሞች ምግብ  ዋስትና ችግር በፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ፕሮግራም  እንዲሁም በተቋማዊና ሕጋዊ ማዕቀፍ በመደገፍ ችግሩን  መፍታት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው፡፡

– በአሁኑ ወቅት በከተሞች እየተከሰተ ያለው የምግብ  ዋስትና እጦት ተጋላጭነት ዓለም ዓቀፍ አጀንዳ እየሆነ  መጥቷል፡፡

– ችግሩን ለመፍታት ሀገራት እንደየሃገራቸው  ተጨባጭ ሁኔታ የመፍትሔ እርምጃዎችን እየወሰዱ  ይገኛሉ፡፡

– ለምሳሌ ያህል እ.ኤ.አ ከ2003 ጀምሮ ተግባራዊ  የሆነው የብራዚል ዜሮ ረሃብ ስትራቴጂ የሃገሪቱን  ፖሊሲዎች፣ስትራቴጂዎችናፕሮግራሞችን  አቀናጅቶና አስተሳስሮ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ  ተግባራዊ በማድረግ የተመዘገበውዓለም ዓቀፍ  ዕውቅና ያገኘው ውጤት ነው፡፡

– ይህ የሚያሳየው በከተሞች የምግብ ዋስትናን  የማረጋገጥስራበተቀናጀናበተናበበሁኔታ  ካልተመራ ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ የማይችል  መሆኑን ነው፡፡

– ስለዚህ የከተሞችን የምግብ ዋስትና ችግር ለመፍታት  ውጤት ካስመዘገቡ ሃገሮቸ ተሞክሮ በመውሰድ ባለድርሻ  አካላትን በየደረጃው አቀናጅቶና አስተሳስሮ በመምራት  አሁን ያለውን ችግር መፍታትና የወደፊቱንም የመከላከል  አቅጣጫ መከተል አስፈላጊ ነው፡፡

– ከዚህም ባሻገር ሀገሪቱ በ2017 ዓ.ም መካከለኛ ገቢ  ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ የሰነቀችውን ራዕይ  ዕውን ለማድረግ በስራ ላይ ያለውን የተዛባ አመለካከት  ለውጦ የባከነውን የሰው ሃብት ጥቅም ላይ እንዲውል  ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

– ይህንንም በማድረግ በከተሞች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ  የመጣውን የማህበራዊ ኑሮ ችግርና ጠንቅ ደረጃ በደረጃ  በመቀነስ የሀገር ገጽታ መገንባትና የዜጎችንም ስብዕና  መጠበቅ አስፈላጊና ህገ መንግስታዊም በመሆኑ የከተሞች  ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ  የዜጎችን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ አስፈልጓል፡፡

የፕሮግራሙ ማዕቀፍ

– በፕሮግራሙ ተጠቃሚ የሚሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች  ሁለት ገፅታ ያላቸው ሲሆን፡-

– የመጀመሪያው ስራ መስራት የሚያስችል አቅምና  ጉልበት እያላቸው ነገር ግን በስራ ላይ ባለው የተዛባ  አመለካት ምክንያት ስራ ፈት የሆኑ እና ስራ መስራት  ፍላጎት እያላቸው ስራ በማጣታቸው ምክንያት ስራ አጥ  ሆነው የምግብ ዋስትና እጦት ተጋላጭ የሆኑትን ዜጎች  ነው፡፡

– በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች ለምግብ  ዋስትና እጦት ተጋላጭ የሆኑትን ማለትም ለምኖ  አዳሪዎች፣ ሴተኛ አዳሪዎች፣ ጎዳና ተዳዳሪዎች፣  የመንገድ ላይ ነጋዴዎች፣ አረጋዊያንና የአካል  ጉዳተኞች እና የአዕምሮ ህመምተኞች ናቸው፡፡

– ፕሮግራሙ በሀገራችን ባሉ በሁሉም ከተሞች በአንድ  ጊዜ ተግባራዊ ማድረግ አስቸጋሪ በመሆኑ እንደ  ችግሩ ስፋትና ክብደት ከተሞችን በተለያዩ ምድቦች  በመከፋፈል ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

* በመሆኑም በዚህ ፕሮግራም የሚታቀፉ 972  ከተሞች በአምስት ምድቦች የተከፈሉ ሲሆን

– በመጀመሪያው ምድብ የህዝብ ብዛታቸው 100,000  እና በላይ የሆኑትን 19 ከተሞች፣

– በሁለተኛው ምድብ ከ50,000 እስከ 100,000  የሆኑትን 25 ከተሞች፣

– በሶስተኛዉ ምድብ የህዝብ ብዛታቸው ከ50,000  በታችና ከ20,000 በላይ የሆኑትን 91 ከተሞች፣

– በአራተኛው ምድብ የህዝብ ብዛታቸው ከ20,000  በታችና 10,000 እና በላይ የሆኑ ብዛታቸው 191  ከተሞች እና

– በአምስተኛው ምድብ የህዝብ ብዛታቸው ከ10,000  በታች የሆኑ 646 ከተሞችን የሚሸፍን ነው፡፡

የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች

* አነስተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች

– አነስተኛ ገቢ በሚያስገኝ ኢመደበኛ ( ማለትም የጎዳና  ንግድ፣ ቤት ለቤት እየሄዱ የሚሰሩ ፣ ወዘተ..) ሰራዎች  ላይየተሰማሩእንዲሁምበጥቃቅንናአነስተኛ  ኢንተርፕራይዝ ለመደራጀት የሚያስችል ሁኔታ ላይ  ያልሆኑ

– ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢያቸው የምግብ ድህነት ወለል  ከሚባለው ብር 3781 እና ከዚያ በታች ገቢ ያላቸው  የከተማ ነዋሪዎችን፣

* ጎዳና ተዳዳሪዎች

– በቤተሰብ መላላት፣ መለያየት፣ ፍቺና ሞት፣ የገቢ  ማነስ፣ በጓደኛ ግፊት፣ በተለያዩ ሱሶች በመጠመድ ወዘተ  ምክንያቶች ውሎና አዳራቸው ጎዳና ላይ ያደረጉ  የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡

* ለምኖ አዳሪዎች፣

– ልመናን እንደ አንድ የመተዳደሪያ ስራ አድርገው  የተሰማሩ

* ሴተኛ አዳሪዎች፣

– በተለያዩ ችግሮች ምክንያቶች ህይወታቸውን  በሴተኛ አዳሪነት የሚመሩ

* ስራ ፈት ዜጎች፣

– በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፕሮግራም ያልታቀፉ፣

– የቤተሰብ ጥገኛ የሆኑ፣

– ስራ ለመስራት ዝግጁነት ማነስ ያለበትና ስራ በማማረጥና ስራ ጠል የሆኑ፣

* ስራ አጦች

– ስራ ለመስራት ፈልገው ያጡ

– በጥቃቅንና አነስተኛ ለመደራጀት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች ባለማሟላታቸው ያልተደራጀ

– የቤተሰብ ጥገኛ የሆኑ

* አካል ጉዳተኞች

– የአካል ጉዳት ያለባቸው ወይም ተደራራቢ የአካል ጉዳት ያለባቸው የገቢ ምንጭ የሌላቸው

– ስራ ለመስራት የማያስችል የአካል ጉዳት ያለባቸው

* አረጋውያን

– ደጋፊ እና ጧሪ እንዲሁም መተዳደሪያ ሃብት የሌላቸው

* የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎች፣ ወጣት ጥፋተኞች፣

– በአደንዛዥ እጽ ሱስ ተጠቂ የሆኑ

– ወጣት ጥፋተኛ የሆኑ

* የአዕምሮ ህመምተኛ

– የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነ/የሆነች በቤት ውስጥ የሚገኙና በገቢ ማነስ ምክንያት ቤተሰብ ሊደግፋቸው ያልቻለ

– የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነ/የሆነች ወደ ጎዳና የወጡ

– የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነ/የሆነች በአዕምሮ ህክምና ተቋም ገብተው በሚወጡበት ጊዜ የሚቀበላቸው ቤተሰብ ወይም ዘመድ የሌላቸው

* ህጻናት

– እድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በታች የሆነና ለስራ ያልደረሰ

– ሁለቱንም ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ

– ከወላጆቻቸው ጋር የተጠፋፉና በተለያዩ ምክንያቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተለያዩ

– ወላጆቻቸው ወልደው የሚጥሏቸው

የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ማስፈፀሚያዎች /program component/

1) ሴፍቲኔት ትራንስፈር /safety net transfer/

2) የኑሮ ሁኔታን ማሻሻያ /livelihood/

3) ተቋማዊ የአቅም ግንባታና የፕሮግራም አስተዳደር /capacity building and program management/

1)ሴፍቲኔት ትራንስፈር /safetynet transfer/

* በሴፍቲኔት ትራንስፈር አሰራር ውስጥ ከሚካተቱት መካከል የጉልበት ተኮር ልማታዊ ማህበረሰብ አቀፍ ስራ በዋነኝነት የሚጠቀስ ነው፡፡

* ይህ አሰራር በተለይ የመስራት አቅም እያላቸው በተለያዩየማህበራዊችግርውስጥየሚገኙ የህብረተሰብክፍሎችአስፈላጊውየስነልቦናና የክህሎት አቅም ግንባታ እንዲያገኙ በማድረግ ወደ ስራ እንዲሰማሩ የሚደረግበት አሰራር ነው፡፡

* ይህም የሚከናወነው የጉልበት ስራን በማዋጣት በተመረጡየከተማአካባቢዎችበሚከናወኑ ማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ ነው፡፡

* በሌላ በኩል የቀጥታ ድጋፍ መስጠት ሲሆን የዚህ  አሰራር ተጠቃሚ የሚሆኑት በእድሜ መግፋት፣  በበሽታ፣ በአካል ጉዳትና በተመሳሳይ ሁኔታዎች  ምክንያት በስራ ላይ መሰማራት የማይችሉና ካሉበት  ከፍተኛ የማህበራዊ ችግር ለማውጣት ሲባል የቀጥታ  ድጋፍ ተጠቃሚ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን  የሚመለከት ነው፡፡

* በተመሳሳይ ሁኔታ የተጠቃሚዎችንና የቤተሰቦቻቸውን  የትምህርት፣ የጤና፣ የስርዓተ ምግብ ሁኔታ ወዘተ…  ለማሻሻል መሰረታዊ አገልግሎቶችን የሚያገኙበትን  መንገድ በሚያበረታታ መልኩ የሚተገበር ቀላል ቅድመ  ሁኔታ ላይ የተመሰረተ የማህበራዊ ድጋፍ አሰራርም  የሴፍቲኔት አሰራር አንዱ አካል ነው፡፡

* በሴፍቲኔት ትግበራ የጉልበት ተኮር ልማታዊ ማህበሰብ አቀፍ ስራ የሚከናወንበትን ወቅትና የጊዜ መጠን፣የክፍያ መጠን፣ የአከፋፈል ሁኔታና ተያያዥሁኔታዎችመለየትናየመወሰን ተጠቃሚዎችንከድህነትወለልለማውጣትና ከሌሎች የኑሮ ሁኔታ ማሻሻያ እርምጃዎች ጋር በሚጣጣሙበት መልኩ የሚከናወን ስራ ነው፡፡

* የሴፍቲኔት ትግበራ ትኩረት ከሚያደርግባቸው የህብረተሰብክፍሎችመካከልየጎዳናላይ ተዳዳሪዎች፣ህጻናት፣ወጣቶች፣ሴቶች፣ አረጋዊያን፣አካልጉዳተኞች፣የአእምሮጤና ህመምተኞች፣ ሴተኛ አዳሪዎች፣ በልመና ላይ የተሰማሩ ዜጎች፣ የጎዳና ላይ ነጋዴዎች እና ዝቅተኞ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ያተኮረ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል፡፡

* በከተሞች አካባቢ በማህበረሰብ አቀፍ ልማት የሚከናወኑየስራዓይነቶችየተለያዩሲሆኑ ዘርፎቹምየተለዩትበባህሪያቸውህብረተሰቡ በአካባቢው የሚገኙ የመንግስትና የሕዝብ ሀብቶችን የማልማትና የስራ ዕድል ከመፍጠርም በተጨማሪ የአካባቢ ጥበቃን፣ ጽዳትና ውበትን በማስጠበቅ ረገድና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ እንዲሚችሉ ተደርገው የሚቀረጹ ናቸው ፡፡

* በማህበረሰብ አቀፍ ልማት የሚከናወኑ የስራ ዓይነቶች በየጊዜው የሚዳብሩና በህብረተሰቡ ተሳትፎ በሚለዩ ስራዎች ላይ የሚያተኩሩ ይሆናሉ፡፡

* ትኩረት ከሚደረግባቸው የማህበረሰብ አቀፍ የስራ   ዓይነቶች መካከል የሚከተሉት ናቸው፣

– የወንዞች ዳረቻ ተፋሰስ ልማት

– አደባባዮችና የመንገድ አካፋዮችን ማስዋብ

– ፓርኮች፣ መናፈሻዎች እና ደን ማልማት

– የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ማልማት

– የኮብል ስቶን ማምረትና ማንጠፍ

– ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻን ማስወገድ

– የቆሻሻ ማስወገጃ ዲች ግንባታ

– የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች

– ለኑሮ ሁኔታ መሻሻል ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች /የማምረቻ ቦታዎች፣መጋዘኖች / ወዘተ፡፡

2) የኑሮ ሁኔታን ማሻሻያ /livelihood/

* የመስራት አቅምና ጉልበት ኖሯቸው የራሳቸውን ስራ በግልም ሆነ በማህበር ተደራጅተውም ይሁን ሳይደራጁ ለመስራት የሚሹ ወይም አስፈላጊው የቴክኒክና የተሀድሶ ስልጠና ተደርጎላቸው ወደ ስራ መሰማራት ለሚችሉ ተጠቃሚዎች የሚዘረጋ አሰራር ነው ፡፡

* በዚህ አሰራር የሚሰጠው ድጋፍም ገቢ በሚያስገኝ ስራ ላይ ለመሰማራት የሚያግዙና የኑሮ ሁኔታን ለማሻሻል የሚያስችሉ የቢዝነስ ፕላን እና የሂሳብ መዝገብ አያያዝ፣ የቁጠባ ፣ የገበያ ትስስርና የስራ ዕድል የመፍጠር ሁኔታዎችን ወዘተ…ለማበረታት የሚሰጡ የመነሻ ካፒታል ወይም ግራንት መስጠትን ጨምሮሌሎችሁለገብድጋፍመስጠትን ያካትታል፡፡

3) ተቋማዊ የአቅም ግንባታና የፕሮግራም አስተዳደር /capacity building and program management/

* በአቅም ግንባታ ረገድ ከሚተገበሩ የትኩረት አቅጣጫዎች   መካከልውጤታማየፕሮግራምማስተባበርን፣   የክትትልና የግምገማ አሰራርን በተደራጀ ሁኔታ   ለመተግበር ህብረተሰቡን ያሳተፈና ዘላቂነት ያለው   የአቅም ግንባታ ስራዎችን መስራት ያካትታል፡፡

* በፕሮግራም አስተዳደር ረገድ የከተማ ተኮር ሴፍቲኔትን   በአግባቡለማስፈጸምየሚያስችልየሰውሃይል   የመመደብናየማሰልጠን፣የትስስርናየአጋርነት   ስራዎችን ማጎልበት፣ የጥናትና ምርምር ስራዎችን   ማከናወን፣ የድጋፍ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት፣ የመረጃ   ማጠናቀሪያ ዳታ ቤዝ ልማትን ማልማት እና   ወዘተ…የሚከናወኑ ስራዎች ይሆናል፡፡

የፕሮግራሙ ዘላቂነት እና የተጠቃሚዎች  ሽግግር

* የፕሮግራሙ ዘላቂነት

– የፕሮግራሙን ዘላቂነት ለማረጋገጥ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል፡-

— የባለድርሻና ተባባሪ አካላትን አጋርነት እና ትስስር መፍጠርና ማጠናከር፣

— የዜጎችን የምግብ ዋስትና እጦት ወደ ዜሮ ረሀብ ለማድረስ በየደረጃዉ ያለዉ አመራርና ፈጻሚ በጊዜ   የለኝም መንፈስ እንዲረባረብ ማድረግ፣

— ተከታታይነት ያለዉ የልማታዊ ኮሚዩኒኬሽን ስራዎችን በመስራት ቀጣይነት ያለው የህዝብ ንቅናቄ   መፍጠር፣

* ለፕሮግራሙ ማስፈጸሚያ የሚሆን በቂ ገንዘብና ሀብት የመሰብሰብና የመጠቀም አቅምን መፍጠር፣

* ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠርና ማጠናከር፣

* አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉትን የአመለካከት፣ የክህሎት፣ የግብዓት፣ የአሰራርና የአደረጃጀት ማነቆዎችን እየለዩና እየፈቱ መሄድ፣ 

* የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት እና ተግባርን የሚጸየፍና አምርሮ የሚታገል አገልጋይና ተገልጋይን መፍጠር፣

* የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች አመራረጥ በህብረተሰቡ እና በባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ማድረግ፣

* የምክር፣ የስራ አመራርና የሙያ ስልጠናዎች እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን መስጠት፣

* የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎችን የቁጠባ ባህል በማሳደግ ከገቢያቸዉ ቁጠባ እንዲያደርጉ በማስቻል የተረጋጋ፣ ወጪ ቆጣቢና አስተማማኝ የገንዘብ ምንጭ መፍጠር፣

* ለዉጥ ያመጡትን አስፈላጊዉን ማበረታቻ በማድረግ ወደ ጥቃቅንና አነስተኛ እና ሌሎች የስራ አማራጮች እንዲሸጋገሩ ማድረግና ድክመት ያሳዩትን በመደገፍ የማብቃት ስራ መስራት፣

* ሁሉንም ከተሞች ሊያገናኝ የሚችል ዘመናዊ የዳታቤዝ ማኔጅመንት ስርአት በመዘርጋት የመረጃ ቅብብሎሹ ወቅታዊና ተአማኒነት እንዲኖረዉ ማድረግ፣

* ቀጣይነት ያለዉ የርዕስ በርዕስ መማማር ስርዓትን በማጠናከር በክትትልና ድጋፍ የተደገፈ ግብረ መልስ በመስጠት እንዲሁም የፋይዳ ግምገማ በማድረግ ክፍተቶች እንዲስተካከሉ እና መልካም ተሞክሮች ተቀምረው የማስፋት ስራ መስራት፡፡

የፕሮግራሙ ራዕይ፣ ዓላማ እና ግቦች

ራዕይ፡

“ኢኮኖሚያዊ ምርታማነት፣ የሁሉም ተጠቃሚነት እና በዘላቂነት ለኑሮ ምቹ አካባቢ ያረጋገጡ ከተሞች በ2017 ተፈጥረው ማየት!”

ዓላማ፡

በከተሞች ከድህነት ወለል በታች እየኖረ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በማቀፍ ስራ እንዲፈጥሩ ማስቻልናከሌሎች የልማት አካላት ጋር በማስተሳሰር በአጭር ጊዜ ከምግብ ዋስትና ተጋላጭነት ማላቀቅና በረዥም ጊዜ ከድህነት እንዲወጡ ማድረግ ነው፡፡

ዝርዝር ዓላማዎች

– በስራ እና በመደጋገፍ ባህላችን ላይ ያለውን የተዛባ   አመለካከት በመለወጥና የዜጎችን ገቢ በማሳደግ የምግብ   ዋስትናቸው እንዲረጋገጥ ማድረግ፣

– የተቀናጀና የተደራጀ የአሰራር ስርዓት እንዲፈጠር   ማድረግ፡፡

– ለከተሞች ምግብ ዋስትና መረጋገጥ አቅም የሚሆን   ጥናትና ምርምር ማካሄድ፣ መረጃና ሀብት እንዲሰባሰብ   ማድረግ፣

– ለተለያዩ የማህበራዊ ኑሮ ጠንቆች ሰለባ ለመሆን   በማኮብኮብ ላይ ያሉ ዜጎች ባሉበት አምራች ሆነው   ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ፣

– ለማህበራዊ ኑሮ ጠንቅ ሰለባ የሆኑትን ማቋቋም፣

– የመስራት አቅም የሌላቸውና ለማህበራዊ ኑሮ ችግርና   ጠንቅ የተጋለጡ ዜጎች የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት   እንዲያገኙ ማድረግ፣

ጥቅል ግብ፡-

* በሚቀጥሉት 10 አመታት ከአጠቃላይ ድህነት ወለል በታች ያሉ90% የሚሆኑ ስራ አጦች፣ ሥራ ፈቶች እንዲሁም ለማህበራዊ ኑሮ ችግርና ጠንቅ የተጋለጡ ዜጎች ወደ ስራ እንዲሰማሩና 10% የሚሆኑት የመስራት አቅም የሌላቸው የማህበራዊ ጠንቅ ሰለባዎች የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

ፕሮጀክቶች

1) የትስስርና አጋርነት ፕሮጀክት

2) የአመለካከት ለውጥና የአቅም ግንባታ ፕሮጀክት

3) የሥራ ዕድል ፈጠራና የቤተሰብ ጥሪት ግንባታ ፕሮጀክት

4) የተቋምና የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ፕሮጀክት

5) የዳታ ቤዝ ልማት ፕሮጀክት

6) የድጋፍ ማዕቀፎች አቅርቦት ፕሮጀክት

7) የተጠቃሚዎች ዕድገትና ሽግግር ፕሮጀክት

8) የጥናት፣ምርምርና ስርፀት ፕሮጀክት

9) የሀብት ማፈላለግ ፕሮጀክት

9) የሀብት ማፈላለግ ፕሮጀክት

**********

Daniel Berhane

more recommended stories