Category Archives: ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ ተከታታይ ጽሑፍ

“ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ” በሚል አብይ ርዕስ በቀረበ ተከታታይ ጽሑፍ፡-

ክፍል-1 “የፀረ-ሽብር ሽብር” – ሽብርተኝነትን በፀረ-ሽብር ዘመቻና ጦርነት/ዘመቻ መግታት እንደማይቻል፤

ክፍል-2 “ፍርሃትን በፍርሃት” – በፍርሃት የሚወሰዱ አብዛኞቹ የፖለቲካና ወታደራዊ እርምጃዎች ስህተት እንደሆኑ፤

ክፍል-3 “የአሸባሪዎች ሕግ” – የሽብር ጥቃት በደረሰ ማግስት የሚወጡ አዋጆችና መመሪያዎች የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሊገድቡ እንደሚችሉ፤

 በክፍል-4 “እውነትን በጉልበት” – ደግሞ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በታሰሩ እስረኞች ላይ ስለሚካሄደው የስቃይ ምርመራና ከዚያ ጋር ተያይዞ ያለው የተሳሳተ እሳቤና ተፅዕኖ እንመለከታለን።

መልካም ንባብ፡፡

—— 

ምስል – ማዕከላዊ እስር ቤት (Maekelawi or Federal Police Crime Investigation Sector)

Map - Maekelawi or Federal Police Crime Investigation Sector

ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 4 – “እውነትን በጉልበት”

“ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ” በሚለው ተከታታይ ፅሁፍ፤ በክፍል-1 “የፀረ-ሽብር ሽብር” – ሽብርተኝነትን በፀረ-ሽብር ዘመቻና ጦርነት/ዘመቻ መግታት እንደማይቻል፤ በክፍል-2 “ፍርሃትን በፍርሃት” – በፍርሃት የሚወሰዱ አብዛኞቹ የፖለቲካና ወታደራዊ እርምጃዎች ስህተት እንደሆኑ፤ እንዲሁም በክፍል-3 “የአሸባሪዎች ሕግ” – የሽብር ጥቃት በደረሰ ማግስት የሚወጡ አዋጆችና መመሪያዎች የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሊገድቡ እንደሚችሉ ተመልክተናል። በመጨረሻው ክፍል-4 ደግሞ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በታሰሩ እስረኞች … Continue reading ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 4 – “እውነትን በጉልበት”

ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 3 – “የአሸባሪዎች ሕግ”

በዚህ “ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ” በሚለው ተከታታይ ፅሁፍ፤ በክፍል-1 “የፀረ-ሽብር ሽብር” – የሽብር ጥቃትን በፀረ-ሸብር ጦርነት/ዘመቻ መፍትሄ ለመስጠት መሞክር በተሳሳተ እሳቤ ላይ የተመሰረተ ስለመሆኑ ተመልክተናል። በክፍል-2 ደግሞ “ፍርሃትን በፍርሃት” በሚል ርዕስ የአሸባሪዎችን ጥቃት በፈጠረው ፍርሃትና ስጋት ውስጥ ሆኖ የሚወሰድ የፖለቲካና ወታደራዊ እርምጃ ውጤቱ ሌላ ተጨማሪ ፍርሃትና ስጋት እንደሆነ አይተናል። የዚህ ክፍል ዋና ትኩረት ደግሞ “የሕዝብን ሰላምና … Continue reading ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 3 – “የአሸባሪዎች ሕግ”

ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 2 – “ፍርሃትን በፍርሃት”

“ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ” በሚለው ተከታታይ ፅሁፍ በክፍል-1 “የፀረ-ሽብር ሽብር” በሚል ርዕስ በዓለም-አቀፉ የፀረ-ሽብር ጦርነት እና በደርግ የቀይ-ሽብር ዘመቻ መካከል ያለውን ተመሣሣይነት እና የተሳሳቱ እሳቤዎች ተመልክተናል። በአሸባሪዎች ለተፈፀመ “ወንጀል” ጦርነት ማወጅና ሽብርን በሌላ ሽብር ለመመከት መሞከር ፍፁም ስህተት ነው። ምክንያቱም፣ መንግስት “በፀረ-ሽብር” ስም የሚፈጥረው ሽብር የትኛውም የአሸባሪ ቡድን ሊያደርስ ከሚችለው በላይ የከፋ ነው። በእርግጥ አሜሪካኖች አንድ ግዜ … Continue reading ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 2 – “ፍርሃትን በፍርሃት”

ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል-1 “የፀረ-ሽብር ሽብር”

ስለማዕከላዊ (Ma’ekelawi) እስር ቤት እና ስለቀይ-ሽብር ሲነሳ እፈራለሁ። በቃ… “ቀይ-ሽብር” ሲባል የታሪክ ጠባሳ፤ “ማዕከላዊ” ደግሞ ምድራዊ ሲዖል ስለሚመስሉኝ ስለዚያ ጉዳይ ማሰብ ራሱ ያስፈራኛል። በተለይ ጋዜጠኛ ማዕዛ ብሩ እና ገጣሚና ተርጓሚ ነብይ መኮንን በሸገር ሬድዮ ያደረጉትን ብዙ ሳምንታት የፈጀ ጭውውት እንደምንም አዳምጬ ከጨረስኩ በኋላ፣ ሌላ ተጨማሪ ነገር መስማትም ሆነ ማንበብ አልሻም ነበር። ባለፈው ሳምንት ግን እንደ … Continue reading ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል-1 “የፀረ-ሽብር ሽብር”