
Category: ሌ/ጄ ጻድቃን ገብረትንሳኤ – General Tsadkan Gebretinsae
ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ (General Tsadkan Gebretinsae) ነባር የህወሓት ታጋይ ሲሆኑ፣ ከ1971 ጀምሮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣ ማሌሊት ሲቋቋም ከመጀመሪያዎቹ 9 የፖሊት ቢሮ አባላት አንዱ የነበሩ ሲሆን እንዲሁም ከ1977 ጀምሮ እስከ1983 የህወሓት ሠራዊት ቺፍ ኦፍ ስታፍ ሆነው ታግለዋል፡፡ በ1987 ህገ-መንግስቱ ሲጸድቅ ከህወሓት አመራርነት ተሰናብተዋል፡፡
ፃድቃን ከ1983-1993 የሀገር መከላከያ ሠራዊት ኤታማጆር ሹም ሆነው የመሩ ሲሆን በ1993 በጡረታ ሲሰናበቱ በወታደራዊ ማዕረግ ሌፍተናንት ጄኔራል (ሌፍተናል ጄኔራል) ማዕረግ ደርሰው ነበር፡፡
በትምህርት ረገድ ከጆርጅ ዋሽንገተን ዩኒቨርሲቲ የዓለም ዓቀፍ ፖሊሲና ትግበራ ማስተርስ ዲግሪ፣ ከኦፕን ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አድሚኒስተሬሽን ማስተርስ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን፤ በዓለም አቀፍ ሕግ በአመስተርዳም ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሳቢያ ሳያጠናቅቁ ቀርተዋል፡፡
በተመድ አማካኝነት በደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡
[Also spelled as ሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ትንሳኤ; General Tsadkan Gebretensae, General Tsadkan Gebretinsae]
[caption id="attachment_16432" align="alignnone" width="640"]

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በትግል 10 ዓመታ ካስቆጠረ በኋላ፤ በ1977ዎቹ የፖለቲካ አመራር የሚሰጥ አደረጃጀት.