‘ኢትዮጵያ  የአባይ ወንዝን መጠቀሟን አጠናክራ ትቀጥላለች’ አቶ መለስ ዓለም

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር – ፕሬስ መግለጫ)

ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን ፍትሐዊ  እና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ፣  ዓለም ዓቀፍ ህግን አክብራ የአባይ/ናይል ወንዝን የህዝቧን የአሁን እና የወደፊት ትውልድ ፍላጎት ለማሳከት መጠቀሟን አጠናክራ እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ገለጹ።

ቃል አቀባዩ ዛሬ በሰጡት ጋዜጠዊ መግለጫ እንደገለፁት ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብት ለመጠቀም የማንንም ፈቀድ አትጠይቅም።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ረሀብን ለማጥፋት የምታከናውነው ፕሮጄክት መሆኑን ጠቅሰው ይህ ፕሮጀክት የኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ በመሆኑ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው።

የግድቡ መገንባት ጥቅሙ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ግብፅና ሱዳንን ጨምሮ ለሌሎች ጎረቤቶቻችን ጭምር መሆኑንም አቶ መለስ ገልፀዋል፡፡

ይህም ግድቡን አፍሪካን ከማስተሳሰር አንፃር አፍሪካዊ ፕሮጀክት ያደርገዋል፡፡ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ከሱዳን እና ግብጽ ጋር ተባብራ መስራቷን ትቀጥላለች።

በዚሁም ኢትዮጵያ የመርሆዎች መግለጫ ስምምነቱ (DoP) በሁሉም ሀገራት እንዲከበር በአጽንኦት ታሳስባለች ብለዋል አቶ መለስ፡፡

Photo - Meles Alem, Spokesperson of Ethiopian Ministry of Foreign Affairs
Photo – Meles Alem, Spokesperson of Ethiopian Ministry of Foreign Affairs

Photo - Press briefing by Meles Alem, Spokesperson of Ethiopian Ministry of Foreign Affairs

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከአሜሪካው አቻቸው ሬክ ቴሌርሰን፣ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ዶናልድ ያማማቶና ሌሎች የኋይ ትሀውስ ባለስልጣናት ጋር በአካባቢያዊና በአለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡
በውይይቱም ሁለቱ አገራት ስትራቴጅክ አጋር መሆናቸውን እና በአፍሪካ ቀንድ ሠላም እና የጸረ ሽብር ትግሉ ላይ በጋራ እንደሚሠሩ ቃል አቀባዩ ገልፀዋል። ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን የሠላም ሂደት  እና በሶማሊያ እያደረገችው ያለችው አዎንታዊ አስተዋፅኦንም አድንቀዋል።

በኤርትራ መንግስት ላይ በተበበሩት መንግስታት የተጣለው ማዕቀብ መቀጠሉ ለአካቢቢው አገራት ሠላም በጎ አስተዋጵዖ እንደሚኖረው ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ቃል አቀባይ ጽ/ቤት 

ህዳር 14 ቀን 2010 ዓ.ም.

********

Guest Author

more recommended stories