የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም የባለቤትነት መብትን ያካተተ ስለመሆኑ ሶስት ህገ መንግስታዊ ምክንያቶች

(Betru Dibaba)

ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያለው ልዩ ጥቅም በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 49(5) መደንገጉ ልዩ ጥቅሙ ከባለቤትነት መብት በታች የሚመስላቸውና ከአንቀጹ ጋር የማይስማሙ አሉ። ነገር ግን፣ ልዩ ጥቅም የባለቤትነት መብትን ያካተተ ስለመሆኑ የሚከተሉት ሶስት ምክንያቶች ማሳያ ናቸው።

1/ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 49(5) [ልዩ] ‘ጥቅም’ (interest) የሚለው ቃል በBlack’s Law Dictionary [the legitemate legal dictionary] 8ኛ ዕትም፣ ገጽ 1431 ላይ እንዲህ ተተርጉመዋል፥
A legal share something, all or part of a legal or equitable claim to or right in property. Collectively, the word includes any aggregation of right, privilege, power or immunity.

ስለዚህ፣ ልዩ ጥቅም የብዙ ነገሮች ውህድ [synergy, aggregation] እንደ ሆነና የባለቤትነት መብት፣ ስልጣን፣ የማይነካ ሀይል፣ ወዘተን የሚያካትት መሆኑ ነው። በመሆኑም፣ ህገ መንግስቱ ‘ልዩ ጥቅም’ የሚለውን ሀረግ መጠቀሙ የባለቤትነት መብትንና ሌሎችንም ለማካተት ስለሆነ የሀረጉ አግባብነት የጎላ ነው።

2/ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 2፣ 47 እና 48 መሰረት 9 ክልሎች ፌደሬሽኑን እንደ መሰረቱ፣ ወሰኑም የክልሎች የወሰን ድምር እንደሆነ ይገልፃል። ህገ መንግቱ አዲስ አበባን ክልል አለማድረጉ በግድ የኦሮሚያ የግዛት ወሰን አካልና እምብርት ያደርጋታል። በህገ መንግስቱ ‘ … መሃል ስለሚገኝ…’ የሚለው ሀረግ ከዚህ በተቃራኒ ሊተረጎም አይገባም።

3/ አንቀጽ 8 እና 39፣ የብሔር፣ ብሔረሰብና ህዝብ ስያሜ፣ እውቅናና ሉዓላዊነት በሀገር ደረጃ ያለውና ለክልሎች የተሰጠ መሆኑን ተመልክተዋል። ይሁን እንጂ፣ አንቀጽ 49 (2፣4) ብሔር፣ ብሔረሰብና ህዝብ የሚለውን ስያሜ ከመጠቀም ተቆጥበው፣ ይልቁን ‘ነዋሪዎች’ (residents) የሚለውን ተጠቅመዋል።

በህገ መንግስቱ የገጠር እና የከተማ መሬት የባለቤትነት መብት፣ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን እስከ መገንጠል መብት ያለ ገደብ ለብሔር፣ ብሔረሰብና ህዝብ ከተሰጣቸው መብቶች ጥቂቶቹ ናቸው፤ አንቀጽ 39(1) እና 40(3)። ነዋሪዎች ግን የተጠቀሱትን መብቶች ሳይሆን ራሱን በራሱ የማስተዳደር (የራሱን ዕድል እንዲወስን አይደለም) መብት ተሰጥተዋቸዋል፤ አንቀጽ 49(2)።

በተሻሻለው የአዲስ አበባ ቻርተር አንቀጽ 7፣ ይህ የነዎሪዎች ራስን የማስተዳደር መብት፣

፩. ስለከተማው የሚወሰኑ ጉዳዮችን በሚመላከት መረጃ የማግኘት፣ ሃሳብና ጥያቄ የማቅረብ እና መልስ የማግኘት መብት አላቸው።

፪. የከተማው አስተዳደር የሚሰጠውን አገልግሎት በእኩልነት፣ በግልጽነትና በፍትሐዊነት መርህ መሰረት የማግኘት መብት አላቸው።

፫. ፖሊሲ፣ በጀት፣ የሥራ ዕቅድና መመሪያ ለነዋሪዎች ይፋ መሆን አለበት።

ማለት መሆኑን ትርጓሜውን ያስቀምጣል። በመሆኑም፣ የአዲስ አበባን ባለቤትነት የኦሮሚያ መሆኑን መቀበል ከክልሉ ጥቅም አንፃር ብቻ ሳይሆን የአዲስ አበባ ነዎሪዎችን ለብሔር፣ ብሔረሰብና ህዝብ ወግና መብቶች ማድረስ ነው።

************

Guest Author

more recommended stories