ለመታገል 4 ሚሊዬን አይደለም 400 ሰው ይበቃል ~ ለማ መገርሳ

[ክፍል አራት] – የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 10/2009 በአዳማ ከተማ በተካሄደው የክልሉ የካቢኔ የዞንና የወረዳ አመራሮች የ2009 ዓመት አፈፃፀም እና የ2010 ዓመት እቅድ የግምገማና የውይይት መድረክ ላይ ያደረጉት ንግግር፡፡

(ከአፋን ኦሮሞ ወደ አማርኛ በHornAffairs የተተረጎመ)

ድርጅታችንን ጠንካራ፣ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ የሚችል፣ ብቁ እና በህዝቡ ዘንድ legitimacy ያለው ማድረግ አለብን፡፡ ስለዚህ ጠንክረን፤ ደከመን ሰለቸን ሳንል መስራት አለብን፡፡ ሞራሉ ተነሳስቶ፣ ተስፋን ሰንቆ፣ እውቅና የሰጠን፣ recognize ያደረገንን ህዝብ ልብ መስበር የለብንም፡፡

ትናንት እንደተናቅነው፣ ትናንት ህዝቡ አቆሽሾን እንደጠላን፣ ወደዚያ መመለስ የለብንም፡፡ እውነቴን የምላችሁ፤ ይሀ ህዝብ ብዙ ቀልቦናል፡፡ ብዙ ተሸክሞናል፡፡ ይሀ ህዝብ ባለፉት 25 ዓመታት ቀለበን፣ ቀለበን፣ ግን OPDO ማለት “ቢቀለብ ቢቀለብ የማያድግ ልጅ” ሆኖ ነው የቆየው፡፡ ይሀ ህዝብ ቢቀልበን ቢቀልበን ማደግ ያልቻልነው እኛ ነን፡፡ ከአሁን በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት እየተቀለበ የማያድግ ልጅ መሆን የለብንም፡፡

ድርጅታችን ህዝቡ በሚፈልገው ደረጃ ማደግ መቻል አለበት፡፡ ህዝቡ በሚፈልገው ደረጃ vigilant ሆኖ፡ bold ሆኖ ወጥቶ፣ ለዚህ ህዝብ መብት ታግሎ የህዝቡን ጥቅም ማረጋገጥ መቻል አለበት፡፡ ድርጅታችን የዚህ ህዝብ ፍላጎት እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ መቻል አለበት፡፡ መንግስታችንን ጠንካራ ማድረግ አለብን፡፡ ድርጅታችንንም ጠንካራ ማድረግ አለብን፡፡ ሊጠነክር የሚችለው ደግሞ በሁላችን ትግል ነው፡፡

ዛሬ ህዝቡ ጥሩ certificate ሰጥቶናል፡፡ ይሀን እውቅና የሰጠንን ህዝብ መዋረድ የለብንም፡፡ ዛሬ ህዝቡ የመጨረሻ እድል ሰጥቶናል፡፡ በታሪካችን ሰጥቶን የማያውቀውን እውቅና ሰጥቶናል፡፡

እኔ’ምላችሁ ነገር ቢኖር፤ በዚህ ትግል ውስጥ የምንቸገር ሰዎች ካለን፤ ገንዘብ የምንፈልግ ሰዎች ያለን እንደሆነ አስራሩ አለ፡፡ እናግዛችኋለን፣ ውጡና በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጁ፡፡ እናግዛቿለን፣ ቃል እገባላቿለሁ፡፡ ማገዝ እንችላለን፡፡ ግን እሱ ራሱ መታገዝ የሚችለው ይህ ስርዓት ሲኖር ነው፡፡ ስለዚህ ማንም ወሬ በኩንታል እያመረተ ሊረብሸን አይገባም፡፡

አላማችን አንድ እና አንድ ነው፡፡ ለዚህ ህዝብ መታገል፡፡ እያንዳንዳቹ ወደዚህ ትግል ስትገቡ ለምን ዓላማ እንደሆነ ተመልሳችሁ እራሳችሁን ጠይቁ፡፡ እኔ ወደዚህ ትግል የገባሁት ለኦሮሞ ህዝብ ለመታገል ነው፡፡ የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ነው ወደ ትግሉ የገባሁት፡፡ ለምን? ፍላጎቴ እና ጥቅሜ የሚረጋገጠው፡ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትና ተጠቃሚነት ሲረጋገጥ ስለሆነ፡፡ ይሀ ማለት ሌላውን መጥላት ማለት አይደለም፡፡ ይሀ ማለት ሌላው ላይ መዛት ማለት አይደለም፡፡ This is a logic. ይሀን መቀበል አቅቶት deny ማድረግ የሚፈልግ አለ፡፡

ከዚህ ህዝብ interest የሚበልጥብን ሌላ ግብ ሊኖረን አይችልም፡፡ ይሀን ማድረግ ካቃተን ትግሉን መልቀቅ ነው ያለብን፤ ህዝቡ ለራሱ ይታገል፡፡ አለበለዚያ bold ሆነን ህዝቡ በሚፈልገው ደረጃ በመገኘት በሀቀኝነት፣ በቅንነት፣ ቆራጥ ሆነን፣ ለቆምንለት ዓላማ ከልብ መታገል ነው ያለብን፡፡ አሁን አምኖን ከጎናችን የቆመውን ህዝብ ይዘን ጠንክረን መለወጥ መቻል አለብን፡፡

ከዚህ በፊት በህዝባችን ዘንድ እንደተናቅነው፡ ታሪካችንን ማበላሸት የለብንም፡፡ ለዚህ ትግል ዋጋ አስከከፈልን ድረስ ታሪካችንን ማበላሸት የለብንም፡፡ ጠንካራ ድርጅት መሆን ጀምረናል፡፡ ጠንካራ መንግስት መሆን ጀምረናል፡፡ ግን ፈፅሞ በቂ አይደለም፡፡ ገና ጅምር ላይ ነን፡፡

ድል ተቀዳጅተናል? አዎ! የነበረው አስከፊ ሁኔታን በመቀልበስ ድል ተቀዳጅተናል፡፡ መስራት ጀምረናል፡፡ ህዝቡ ከሚጠብቀው አንፃር ግን ገና ስራ አልጀመርንም፡፡ ስለዚህ ሁሉም ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ ሁሉም አመራር ስኬት ላይ ለመድረስ ከልብ በመናበብ፣ ከላይ እስከ ታች አንድ ቋንቋ በመናገር፣ ለጋራ ዓላማ ተሰልፎ በጋራ መታገል አለበት፡፡

ምን ይመጣል እያላችሁ ከሹመት ቦታ በመነሳት ስጋት የተለያየ illusion ውስጥ የገባችሁ አካላት፤ ሹመት ከሆነ የምትፈልጉት የሹመት ቦታ በቂ አለ፡፡ አያልቅም፡፡ እየሰራን ካለነው አኳያ ስራው ከዚህ በላይ ሃይል እየጠየቀ ነው ያለው፡፡

ግን useless የሆነ ሰው፣ ችግር መፍታት የማይችል ሰው፣ ውስጣችን ሆኖ ሊበጠብጠን አይችልም፡፡ ከስራው ይልቅ እሱ ራሱ የቤት ስራ ሆኖብን ጊዜ ልናቃጥልበት አይገባም፡፡

እንዴት ሞራላችን እንደተነካ፣ እንዴት ድርጅታችን በህዝቡ ዘንድ እንደቆሸሸ፣ እንዴት እንደተናቀ ሁላችሁም ታውቁታላችሁ፡፡ We have to change. ይሀን ታሪክ መቀየር አለብን፡፡ ይህን ታሪክ የምንቀይረው ደግሞ ወሬኛ እና ሌባን አቅፈን አይደለም፡፡ ሌብነት ነው በህዝቡ እንድንጠላ እያደረገን ያለው፡፡ ይሀን ከውስጣችን መጥረግ አለብን፡፡ ለቅመን ማስወገድ አለብን፡፡ ወዲህ ወዲያ ማየት የለብንም፡፡ ጠንከረን መስራት አለብን፡፡

እኔ ስለኦሮሞ ህዝብ ጥቅም ስለተናገርኩ የሚከፋው ሰው ካለ፤ መክፋት አይደለም ወደ ፈለገ ይገለባበጥ፡፡ ማህበር ለመጠጣት ወይም ፀበል ለመጠጣት አይደለም እኔ ወደዚህ ትግል የተቀላቀልኩት፡፡

ለዚህ ህዝብ ታግለናል እስካልን ድረስ፤ We have to protect the interest of this people. ለዚህ መስራት ነው፡፡ እኛ ይሀን ስንሰራ ስንቱ ነው ይሀ አይሆንም ያለን! ከውጭ ብቻ አይደለም እኮ! እዚህ እኛው ውስጥ ሆኖ ስንት ሴራና ደባ እኛ ላይ ለመስራት ሌተ’ቀን የሚተጋ ስንቱ አለ? ይሀን በትግላችን clear ማድረግ አለብን፡፡

ይሀ ድርጅትና መንግስት ህዝቡ አለኝታዬ ነው የሚለው መሆን አለበት፡፡ ደግመን ደጋግመን እየተናገርን ነው፡፡ ህዝቡን እንስማ፡፡ ከህዝቡ ጋራ ሆነን ህዝቡ የሚፈልገውን እንስራ፡፡ ሌላ ነገር አይደለም እንስራ እያልን ያለነው፡፡ Rocket science እንፍጠር እየተፈላሰፍን ከአቅማችን በላይ እንንጠራራ አይደለም እያለን አይደለም፡፡ ይሀ አይነት ፍላጎት የለንም፡፡ ለዚህ ህዝብ እንስራ ነው እያልን ያለነው፡፡

በየትኛውም ደረጃና በየትኛውም ቦታ ለዚህ ህዝብ ፍላጎትና ተጠቃሚነት እንቁም ነው እያልን ያለነው፡፡ ጠንክረን እንስራ ነው እያልን ያለነው፡፡ 25 ሙሉ ያልተሰራበትን የፊንፊኔ ልዩ ጥቅም ለማረጋገጥ ስንሰራ ማነው አይሆንም ያለን? የኦሮሞ ህዝብ ተጠቃሚነት ”አይ አይሆንም” ያለን ማነው? የተፋለመን ማነው? ይሀን ነው እያልን ያለነው፡፡ ጠንክረን መስራት አለብን፡፡ ሌላ አማራጭ የለንም፡፡

የሞተ ኦህዴድ ለኢህአዴግም አይጠቅምም፡፡ የተኮላሸ ኦህዴድ ለሀገሪቷም አይጠቅምም፡፡ ለሀገሪቷም ቢሆን ጠንካራ ኦህዴድ ነው የሚጠቅመው፡፡ ይህ ድርጅት ጠንክሯል እያለ ስጋት የሚሰማው ሰው ካለ ተሳስቷል፡፡ ይሀ ድርጅት ከጠነከረ ነው፣ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከጠነከረ ነው፣ ሀገሪቷም ሀገር የምትሆነውና የምትጠቀመውም፡፡ ሀገሪቷም የምትጠነክረው ያኔ ነው፡፡ ሌላውም ይሀን ማወቅ አለበት፡፡

ለዚህ ህዝብ ተጠቃሚነት ስለሰራን ብቻ በመጥፎ አይን መታየት የለብንም፡፡ ግን ደግሞ የፈለገ ሰው አይኑ መቅላት አይደለም ደሙ ይደፍርስ እንጂ፤ እኛ ነን በቀዳሚነት ለዚህ ህዝብ ጥቅም መታገል ያለብን፤ የዚህን ህዝብ ጥቅም ማሰጠበቅ ያለብን፡፡ ስለዚህ እንደ አመራር በአንድነት ጠንክረን በመስራት፣ ዳግም እድል ለሰጠን ህዝብ ውጤት ማሳየት አለብን፡፡ ከሰራን ደግሞ እንችላለን፡፡ ህዝቡ ይሰማናል፡፡ ትንሽዬ ሰርተን ላሳየነውም ይመሰክራል፡፡

ሌላው መታወቅ ያለበት ደግሞ፤ ይሀ ድርጅት ወድቆ አይወድቅም፡፡ የፈለገ እየዞረ ወሬ ይሸጣታል እንጂ፤ የፈለገ የሚያኖረው መስሎት በህዝብ እየነገደ ይኖራታል እንጂ፤ ይሀ ድርጅት ጠንካራ ህዝባዊ መሰረት አለው፡፡ ለመታገል 4 ሚሊዬን አይደለም 400 ሰው ይበቃል፡፡ የፈለገ ወደፈለገበት ቦታ መሄድ ይችላል፡፡ በትግል ሂደቱ ዋጋ ከፍለንበታል፡፡ ለዚህ ህዝብ ጥቅም ብለን ታመንበት፣ ተሰቃይተንበት፣ ህይወት አጥተንበታል፡፡ ስለፈለገ ማንም ሊያደናቅፈን አይችልም፡፡

ወዲያ ወዲህ ማለት ትተን ይህን ህዝብ፣ ይሀን ድርጅት፣ ይሀን መንግስት፣ በአግባቡ መምራት አለብን፡፡ በአግባቡ ለመምራት ደግሞ ሌቦችን፣ ወረኞችን፣ ውሸታሞችን፣ የሌብነት ሱስ ያለባቸው ሌቦችን፣ ፍርፋሪ ለቃቃሚዎችን፣ ከውስጣችን መጥረግ አለብን፡፡ አለበለዚያ የቆሸሸውን አቅፈን ህዝቡ እኛን ሊሆን አይችልም፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ በምሬት እንታገላለን፡፡ እኛ የምንፈልገው የህዝባችን ከኛ ጎን መሰለፍ ነው፡፡ የፈለገ ወደ ፈለገው ይሂድ፡፡ ህዝባችን ከኛ ጋራ ከሆነ መስራት እንችላለን፡፡

***********

* የፕ/ት ለማ መገርሳ ንግግር ክፍል አንድ – “አምና በዚች ወቅት ምን ውስጥ ነበርን? ዛሬስ የት ነን?”
* የፕ/ት ለማ መገርሳ ንግግር ክፍል ሁለት – ከኛ ጎን ለመሰለፍ ማንም ከማንም የማንነት ሰርተፍኬት እውቅና ሰጪ አያስፈልገውም
* የፕ/ት ለማ መገርሳ ንግግር ክፍል ሶስት – ከ4000 የሚበልጡ አመራሮችን አራግፈናል

Daniel Berhane

more recommended stories