ከኛ ጎን ለመሰለፍ ማንም ከማንም የማንነት ሰርተፍኬት እውቅና ሰጪ አያስፈልገውም ~ ለማ መገርሳ

[ክፍል ሁለት] የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ለማ መገርሳ በአዳማ ያደረጉት ንግግር፡፡

(ከአፋን ኦሮሞ ወደ አማርኛ በHornAffairs የተተረጎመ)

እዚሁ እኛ መሀል ሆኖ፡ ያመጣነውን ለውጥ ለማብጠለጠል “እስቲ ይሀ አዲሱ አመራር የሚያመጣውን ለውጥ እናያለን!” እየለ፤ እራሱን Harvard ተምሮ መጥቶ እሱ ወንበር ላይ ቁጭ ካላለ በስተቀር ኦሮሚያ መኖር እንደማትችል፤ እሱ ከወንበር ሲነሳ ኦሮሚያ እንደምትጠፋ እያስበ illusion ውስጥ የሚኖር ሰው ብዙ ነው፡፡

ይቺ ሀገር እኮ የሁላችንም ናት፡፡ ኦሮሚያ የኦሮሞም፣ ኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ናት እኮ፡፡ በዚህ የትግል ሂደት ውስጥ ከኛ ጎን ለመሰለፍ እና ለመታገል ማንም ከማንም የማንነት ሰርተፍኬት እውቅና ሰጪ አያስፈልገውም፡፡ እኔ ለኦሮሞ ህዝብ ለመታገል እኔ ከወሰንኩ በቂ ነው፡፡ የማንም ሰርተፍኬት እውቅና ሰጪ አያስፈልግም፡፡

ምሁራኖችን አመጣን፡፡ ምሁራኖችን ወደ አመራርነት ማምጣት ለምን እንደ ጥፋት ይታያል? ለምን ምሁራኖችን አመጣን? ለምን ከነበሩ አመራሮች ይልቅ የተሻለ አቅምና ጥሩ አመለካከት ያለው እንዲሁም commitment ያለው ለማምጣት ለምን ወሰን? ለምሁራን የተለየ ፍቅር ስላለን ነው? አይደለም፡፡

ሁላችሁም እዚ ያላችሁ አመራሮች በክልል፣ በከተማ፣ በወረዳ እና በተለያዩ ተቋማት መዋቅር ላይ ያላችሁ በመሆናችሁ በየመዋቅሮቹ ውስጥ ያለውን እውነታ ታውቃላችሁ፡፡ የዛሬ 10 እና 20 ዓመታት እየሰራን በነበረው ሁኔታ ዛሬ መስራት አንችልም፡፡ ብዙ እጅግ ብዙ completely ተቀይሯል፡፡ በዛ ብቃት በዛ አዕምሮ እና በዛ እውቀት የአሁኑን ስራ መስራት አንችልም፡፡

ከዬትኛውም ጊዜ በበለጠ በአሁኑ ወቅት ስራ እውቀት ይጠይቃል፡፡ ልምድ ይጠይቃል፡፡ ቆራጥነትም ይጠይቃል፡፡

እውቀት ያለው አለ፡፡ ልምድ ያለው አለ፡፡ የተሻለ ሀሳብ ያለው አለ፡፡ ይሀን አንዱ ለአንዱ ጉልበት በሚሆን መልኩ mix በማድረግ በማቀናጀት ማዋቀር ካልቻልን አንድ እርምጃ ወደፊት መጓዝ አንችልም፡፡

ትናንት እኮ ህዝቡ እኮ እኛ ላይ ፊቱን ያዞረው፡ ህዝቡን መምራት ስላቃተን ነው፡፡ ለምን ህዝቡን መምራት አቃተን? ህዝቡን ለመምራት የሚያስችል አቅም ስላልነበረን፡፡ አመለካከት ምናምን እንበል እንጂ ተጨምቆ cumulative ውጤቱ ሲታይ This is it.

ህዝቡን የመምራት አቅም አልነበረንም፡፡ አቅማችን ከዚህ በላይ አልነበረም፡፡ በድርጅታችን በመንግስታችን ውስጥ ለህዝብ እና ለሀገር የሚጠቅም ሀሳብ የማመንጨት ድርቅ መቶን ከጊዜ ጋራ መራመድ አቅቶን ነበር እኮ! የዛሬ 10 እና 20 ዓመታት እንሰራበት በነበረው formula ዛሬ መስራት አንችልም፡፡ ያ formula ዛሬ phase Out አድርጓል፡፡

ዛሬ ላይ ቆመን አቅማችን የት ላይ ነው ያለነው ብለን እራሳችን ማየት አለብን፡፡ “አቅማችን፣ ብቃታችን፣ እውቀታችን፣ ኪሎአችን የት ነው ያለው? ምን ይጨመር?” ብለን እራሳችንን ማየት አለብን፡፡

ያለውንም እያበቃን፡፡ ይሀ ትግል እዚህ እንዲደርስም ለዚህ ትግል ዋጋ ለከፈለውም፣ ጭነት እንደተሸከመች አህያ እያራገፍን ሳይሆን፣ ለከፈለው ዋጋ እውቅና ከመስጠት ባለፈም እያበቃነው፣ እያገዝነው፣ ከአዲሱ ሃይልም ጋራ እያቀናጀነው፣ አንዱ ለአንዱ ጉልበት በሚሆን መልኩ ካልገነባነው አንድ እርምጃ ወደፊት መጓዝ አንችልም፡፡ ጠንካራ ተቋማት እና ጠንካራ ድርጅትም መገንባት አንችልም፡፡

በዓለማችን ውስጥም ያለ እውቀት ያደገ የተለወጠ ሀገር የለም፡፡ አቅም የሌለው ሰው እንኳን አንድ ተቋም መምራት መለወጥ አንድ ቤተሰብ መምራት አይችልም፡፡ This is a fact.

ሁሌ እውቀት መጠማት አለብን፡፡ እውቀት ስንጠማ ደግሞ ፈልገን ፈላልገን ካለው ቦታ መጠጣት አለብን፡፡ በመጥፎ አይን ማየት የለብንም፡፡ የመጡት ምሁራኖችም ሆነ ነባሮቻችን ተቀናጅተው ቢሰሩና መንግስታችን፡ ሀገራችን እና ድርጅታችን ቢጠነክሩ ማነው የሚጠቀመው? ይሀ ህዝብ ነው የሚጠቀመው፡፡ እኛም ነው የምንጠቀመው፡፡

ይሀ ወንበር ደግሞ ለኛ ለተወሰኑ ሰዎች የተሰጠ እርስት አይደለም፡፡ የሁላችንም እርስት ናት፡፡ ወንበሯ የምትጠይቀውን ስራ መስራት የሚችለው ሰው ሁሉ ናት፡፡ ይሀ በድርጅታችን የትግል ሂደት የመጣ ውጤት ሲሆን፤

አንደኛ፡ ድርጅታችንም ሆነ መንግስታችን እንዲጠነክር የህዝቡን ጥያቄ በሚፈለገው ደረጃ መመለስ እንዲችል፡ ምሁራኖችን ሳናቅፍና ሳናሳትፍ በድርጅታችን እና በመንግስታችን መዋቅር ብቻ መስራት እንደማንችል ስላመንበትም ጭምር ነው፡፡

ሁለተኛ፡ በትግላችን ሂደት ውስጥ እንደ አንድ ማህረሰብ ክፍል እኛን trust አለማድረግ ብቻ ሳይሆን reject ያደረገን ምሁሩ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ ድርጅታችን፡ ይሀ ድርጅታችን ባለፈበት መንገድ እንኳ መሻገር የማይሻ የህበረተሰብ ክፍል ዋናው ይሄው የምሁሩ class ነበር፡፡ እንደዚህ ወደፊት መሄድ አንችልም፡፡ እንደዚ መስራት አንችልም፡፡ እንደዚ መቀጠል አንችልም፡፡ ምሁራኖችን ማቀፍ አለብን፡፡ ሚና አላቸው፡፡ ድርሻ አላቸው፡፡ ምሁራኖቹ የሚጫወቱት ሚና በማንም የሚተካ አይደለም፡፡

ይሀን በማድረጋችን የቀሩ ሌሎች ምሁራንም ፊታቸውን ወደ ድርጅታቸን ወደ መንግስታችን አዙረው “ምን እናግዛችሁ? እኛም ለህዝባችን፡ ለክልላችን፡ ለሀገራችን ያለንን እናበርክት? ድርሻችንን እንወጣ? ከጎናችሁ መሰለፍ እንፈልጋለን፡፡” ማለት ጀምረዋል፡፡

ይሀ ለድርጅታን፡ ለመንግስታችን፡ ለሀገራችን ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም፡፡ ምሁራኖችን ማሳተፍ እንደ ስጋት መታየት የለበትም፡፡ ተባብረን እየተጋገዝን፡ አንዳችን ለአንዳችን ጉልበት በሚሆን አኳሃን ስንሰራ ሁላችንም ነው የምንጠቀመው፡፡ ሀገራችን ነው የምትጠቀመው!!!

******** 

* የፕ/ት ለማ መገርሳ ንግግር ክፍል አንድ – “አምና በዚች ወቅት ምን ውስጥ ነበርን? ዛሬስ የት ነን?”
* የፕ/ት ለማ መገርሳ ንግግር ክፍል ሶስት – ከ4000 የሚበልጡ አመራሮችን አራግፈናል

Daniel Berhane

more recommended stories