ኒዬሊበራሊዝም ሊክደው ያልቻለ ልማት

(ስንታየሁ ግርማ)

“እ.ኤ.አ በ2016 የአፍሪካ ኢኮኖሚ 3.7% ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምስራቅ አፍሪካ ከአህጉሩ ከፍተኛው እድገት ታስመዘግባለች፡፡ በተለይም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ ባለሁለት አሀዝ እድገት እያስመዘገበች ሲሆን በ2016 ዓ.ም እድገቱ ይቀጥላል፡፡ የእድገቱ ዋንኛ መሠረት ደግሞ ሰፊ የመንግስት ኢንቨስትመንት ነው፡፡ ምዕራብ አፍሪካም በበኩሏ የኢቦላማብቃት ይረዳታል፡፡ ነዳጅ ላኪ ሀገሮች ግን እድገታቸው ይገታል፡፡ ደ/አፍሪካ በድርቅ እና በሃይል እጥረት ምክንያት የእድገቱ ማሽቆልቆል ይቀጥላል”፡፡

The Economist, Africa growthmay 28, 2016 ዘኢኮኖሚስት መፅሄት የኒዬሊበራሊዝምን ሀሳብ በማፍለቅና በማቀንቀን ቀዳሚ ነው፡፡ ዘኢኮኖሚስት መፅሄት የዋና አዘጋጁ ሪፖርተር ወዘተ ስም አያወጣም ይህ የሚያሣየው በመፅሄቱ የሚወጡ መጣጥፎች የግለሰቦች ሳይሆን የመፅሄቱ መሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡ የግለሰቦች አስተያየት ሳይሆን እውነታ ነው እኛ የምንፅፈው ለማለት ነው፡፡

ዘኢኮኖሚስት የሳይንስ አምዱ ሳየቀር በቀላል ቋንቋ የሚፃፍ በመሆኑ በአለም ላይ ተነባቢነቱ ከፍተኛ ነው፡፡ በ2014 እ.ኤ.አ 59 ሚሊዬን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን መረጃዎች ያሳያሉ በዚህ በኦንላየን የሚዲያ ዘመን ይህንን ያህል ትርፍ ማግኘት ምን ያህል ተነባቢ መፅሄት እንደሆነ ያሣያል፡፡ መፅሄቱ ተነባቢነት ያለው ዩኒዬሊበራሊዝም ርዕዬተ አለም ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ከዚህ ተቃራኒ ርዕዮተአለም የሚከተሉት ሳይቀር ናቸው፡፡ ለነገሩማ “Those who do not understand their opponents arguments cannot understand themselves አይደል የሚባለው፡፡ ዘኢኮኖሚስት በጣም የተማሩ ከፍተኛ ፖሊስ አውጭዎች እና ፈፃሚዎችን ታርጌት አድረጐ ይፅፍል፡፡ ዘኢኮኖሚስት ነፃ ንግድን ግሎባላይዜሽን ነፃ የስራተኞችን እንቅስቃሴ አንደ ሚደገፍ ከፅሑፋ መረዳት ይቻላል፡፡ ካርልማርክስ ዘኢኮኖሚስትን “The European organ of the aristocracy of finance” ይለው ነበር ለደናልድ ሬጋን እና ማርጋረት ታቸር ዘኢኮኖሚስት ከፍተኛ ድጋፍ ይሰጥ ነበር፡፡ አሜሪካ በቬትናም ለኢራቅ እና በአፍጋኒስታን ያደረገችውን ጦረነቶች ይደግፍ ነበር፡፡ ቢልጌትስ ዘኢኮኖሚስትን ሁልጊዜ ከጊዜ ገፅ እንደሚያነብ ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር፡፡

Photo - Ethiopia new rail way
Photo – Ethiopia new rail way

ዘኢኮኖሚስት ብቻ ሳይሆን ዘቴሌግራፍ ኢትዮጵያ በአፍሪካ በፍጥነት በማደግ ቁጥር 1 ሀገር እንደሆነች እና ለቱሪዝም ምቹ እንደሆነች ገልፀዋል፡፡ Where to stay in Ethiopia; The best lodges and hotels, Telegraph august 4, 2015 ዘቴሌግራፍ ጋዜጣ በእንግሊዝ የሚታተም ሲሆን ወግ አጥባቂ ፖርቲ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያለው ሲሆን በቀኝ ዘመም ደጋፊነቱ ይታወቃል፡፡ ታዋቂው ፋሪድ ዘከሪያ የምፅፈበጽ የታይም መፅሄት ፣ በየአመቱ 100 ተፅእኖ አሳዳሪ ሰዎችን እና የ20ኛው ክ/ዘመን 100 ተፅእኖ አሳዳሪዎችን በአንባቢ በማስመረጥ እና በማሳተም የሚታወቅ ነው፡፡ Forget the BRICS MEት the PINES በሚል ርዕስ ማርች 13 ቀን 2014 ባወጣው ፅሑፍ የፊሊፒንስ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ናይጅሪያ የኢትዮጵያ እድገት ከብራዚል፣ \ሲያ፣ ህንድ እና ቻይና እየበለጠ ነው በማለት ፅፏል፡፡

ዘወል እስትሬት ጋዜጣ ስያሜው የወሰደው ከፋይናንስ ገበያ ማዕከሉ ነው፡፡ በአሜሪካ በስርጭት የመጀመሪያው ነው፡፡ ኒዬሊበራሊዝም ለገነነበት ለጌጋን ዘመን ዘወልስትሬት የ Supply side economics ማለትም ከአቅርቦት ገበያን ያረጋጋል የሚል ሀሣብ በብዛት ሲሰብክ ነበር፡፡ \በርት መድ\ክ ከገዙት በኋላ የወግ አጥባቂዎችን ሀሳብ በአብዛኛው ያቀነቅናል፡፡ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ሳይንሳዊ ትንታኔ ላይ ጥርጣሪ እንዳለው በተለያየ ጊዜ አንፀባርቋል፡፡ በአጠቃላይ በኒዬሊበራል ሀሳብ አቀንቃኝነቱን የታወቀ ጋዜጣ ነው፡፡ እሱም “WhY made in Ethiopia could be the next made in china may 15, 2014 በሚል ባወጣው ፅሑፍ በአለም ታዋቂ የሆነው ሑጃን የተባለ በቻይና ኩባንያ በሚቀጥሉት አመታት 2 ቢሊዮን የላር በኢትዮጵያ የጫማ ፋብሪካ ኢንቨስት በማድረግ ወደ አውሮፖ እና አሜሪካ ለመላክ ዋንኛ አማራጭ ለማድረግ ኢትዮጵያ አንዴት ምቹ እንደሆነች መስክሯል፡፡

የአለም ባንክ በማደግ ላይ ላሉ ሀገሮች ለካፒታል ኘሬግራም የገንዘብ ድጋፋ ለመስጠት በሚል አላማ የተቋቋመ ድረጅት ነው፡፡ ይሁንና የቀድሞው የባንኩን ኢኮኖሚስት ጁሴፍ ስትግሊዝ ጨምሮ በውሳኔ አሰጣጡ የአሜሪካ ከፍተኛ ተፅእኖ ያለበት መሆኑ ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ባልተገነባበት ሁኔታ የባንኩ መዋቅራዊ ማሻሻያዎች ተግባራዊ የሚሆኑ ከሆኑ ከፍተኛ ጉዳቶች ያደርሳሉበሚል ዬተቹታል፡፡ ባንኩ ውስጥ የአሜሪካ ተፅእኖ ከሌሎች ምዕራባውያን ሳይቀር እየተተች ነው፡፡ የዋሽግተን መግባባትም የሚሉት አሉ፡፡ ባንኩ የምዕራባውያን በተለይም የአሜሪካ መንግስትን ጥቅም በሌሎች በመጫን ይከሰሳል፡፡ ይሁንና የባንኩ የቀድሞው የባንኩ ዳይሬክተር ኤነረስ \ዳ ስብተር በተለምዶ የኢኮኖሚ እድገት የሚለካበትን መንገድ በመሞገት አዲስ 49 መለኪያዎችን በመጠቀም 149 ሀገሮችን ሁኔታ ዳሰዋል፡፡ ስብተር እንደሚሉት የኢኮኖሚ እድገት መለከታ ያለበት ለሰዎች ሁለንተናዊ እድገት ባደረገው ልክ መሆን አለበት፡፡ እድገቱ ለህዝቡ ምን ጥቅም አስገኝቷል፡ የሚለው መታየት አለበት ይላሉ በእሳቸው መለኪያዎች መሠረት አስገራሚ ውጤቶች ቢኖ\ም የሰዎች ሁለንተናዊ ለውጦችን በማስመዝገብ ኢትዮጵያ ቀዳሚ ናት ይላሉ፡፡

ኒዮርክታየምስ በአሜሪካ ከዋልስትሬት ጆርናል ቀጥሎ በስርጭት 2ኛ ነው ግን የተለያዩ ሽልማቶችን በማግኘት የመጀመሪያ ነው፡፡ ባለሪከርዱ ጋዜጣ በመባል ያንቀላኘሱታል፡፡ ጋዜጣው “Is the era of great famine over? May 8. 2016 ባወጣው ፅሑፍ ኢትዮጵያ ድርቅ ወደ ረሃብ እንዳይቀየር የረዳት ሰላም ከፍተኛ ግልፀኝነት፣ በጥንቃቄ የታቀዱ እቅድ ናቸው ይላል፡፡

ጋዜጣው አክሎሞ ድረቅ ወደ ረሃብነት የሚቀየረው በህዝብ ብዛት እና በተፈጥሮ ሳይሆን በፖለቲካ መሆኑን ኢትዮጵያ አሳይታለች ይላል፡፡ “Famine is Nat caused by over population, and as Ethiopia experience shows, it is not a necessary consequence of drought, politics creates famines, and politics can stop it.

ሲጠቃለል የኢትዮጵያ እድገት እና ልማተ የበረካታ የሀገር ኢንቨስተሮች መሪዎች እና እሁንን ትኩረት እየሳበ ነው፡፡ የተለያየ ርዕዮተ አለም ያላቸው ሀገሮች መሪዎች ከኢትዮጵያ ጋር በመጐዳኘት ከባለሀብቶች ጋር በመሆን ሀገራችንን በመጐብኘት እያሳዩ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ተሰሚነቱንም /Soft Power/ እያሳደገ ነው፡፡ በተለመድ የፀጥታው ም/ቤት ተለዋጭ አባል ሆኖ ተመረጣለች፡፡ እስራኤል በአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ለመሆን ኢትዮጵያን ማሣመን ተገቢ ነው በማለት ጠ/ሚ/ር ኔታናንያሁ ኢትዮጵያ ጐብኝተዋል፡፡ ህንድ እና ብራዚል የተወደ የፀጥታው ም/ቤት አባል ለመሆን ለአፍሪካ ህብረትም 1 ድምፅ በመስጠት ይገባል ይላሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያን ማሣዬን የአፍሪካ ህብረት ማሳመን ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ እድገት soft power / የማሣመን አቅም/ እያሣደገለት ነው፡፡

የዚህ እድገት እና ልማተ መሠረቱ ኢህአዲግ በተለይም በታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ መሪነት የነደፋቸውን እና ተግባራዊ ያደረጋቸው ሀገር በቀል ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች ናቸው፡፡ በ1983 ዓ.ም. ኢህአዲግ ሀገሪቱ ሲቆጣጠር በአለም ላይ ኒዬሊበራሊዝም በትወራም በተግባርም የበላይነት ያገኘበት ሁኔታ ቢሆንም ኢህአዲግ በወቅቱ ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የሚመጡ መዋቅራዊ ሽግግር ቅድመ ሁኔታዎች ያልተቀበላቸው ነበ\፡፡ ከእነዚህ መካከል የፋይናንስ ሴክተ\ን ለውጭ ለህዝብ ካለው ውግንና የተነሳ አልተቀበላቸውም ነበር፡፡ ጂሴፍ ስትግሊዝ በሚከተለው መልኩ ገልፀውታል፡፡

“Ethiopia resisted the IMF’s demand that i.e. “open” its banking system, for good reason. It had been what happened when one of its east African neighbors gave into IMF demands. The IMF has insisted on financial market liberalization, be living that competition among banks would lead to lower interest tastes, the results were disastrous; the move was followed by very rapid growth of international and local banks at a time when banking supervision were in adequate with predictable results 14 banking failures in 1993 and 1994 alone.

“In the end interest rates in created, not decreased. Understandably, the government of Ethiopia was wary, committed to improve the living standards of its citizens in the total sector, It feared that liberalization will have a divesting effect on its economy. Those farmers have managed to get credit, would find themselves unable to buy seed or fertilizer b/s they would be unable to obtain cheep credit or would be forced higher interest rates which they could ill afford. That is a country racked by droughts which result in massive starvation; its leaders didn’t want to make matters worse. The Ethiopians worried that the IMF’s advice would cause farmers in comes to fall, exasperating an already dismal situation.”

ስለዚህ የዛሬው ልማት የባለ ራዕዩ መሪ ውጤት ነው እና ማስቀጠል ይገባል፡፡ ለዚህደግሞ ሰላም ወሳኝ ነዉ::

“Peace is not merely a distant goal we seek, but a means by which we arrive at that goal” – Martin Luther King Jr

“It isn’t enough to talk about peace. One must believe in it. And it isn’t enough to believe in it. One must work at it” – Eleanor Roosevelt

**********

* ፀሐፊው ስንታየሁ ግርማ በኢፌዲሪ ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ሀላፊ ሲሆኑ በ[email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

Guest Author

more recommended stories