የሃገራዊ የምክክር መድረክ መነሻ ሰነድ (የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ (CEG – Ethiopia)

የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ (Concerned Ethiopians Group – CEG)

የሃገራዊ የምክክር መድረክ መነሻ ሰነድ ቅፅ 1.0

ዶ/ር መሓሪ ታደለ ማሩ

ጥቅምት 2005

I. አጭር መግቢያ

በቅርቡ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል ውስጥ የነበረው ተቃውሞ በቀላሉ መወሰድ እና ቸል መባል የለበትም፡፡ ጉዳዩ የተሻለ የአመራር ቅቡልነት በሚያስገኝ ሠፋ ባለ ምክክር ካልተፈታ አስፈሪ መንገድና ሊይዝ ደም መቃባትን እና ያለመረጋጋትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከተጠቀምንበት ግን በአሁኑ ሰዐት ያለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ኢትዮጵያ ወደ መበታተን መመለስ ሳይሆን ወደ ብልጽግና እና ዲሞክራሲያዊ መረጋጋት ለመውሰድ የሚያስችለንን ስራ ለመስራት እድል ሰጥቶናል፡፡

ይህ መሰረታዊ ሠነድ በCEG የተዘጋጀው ለተራማጅ ነገር ግን አዝጋሚ ቀጣይነት ላለው  የለውጥ ሂደት የሚሆን ሃገራዊ ምክክር ግልፅ የሆነ የፅንሰ ሀሳብ እና የውሣኔ ነጥቦችን ለማቅረብ ነው፡፡

ሰነዱ ለሃገራዊ ምክክር የሚሆኑ የአጠቃላይ አላማዎችን እና የአፈፃፀም ስልቶችን ማብራሪያ እንዲሁም CEG እንደ ኢትዮጵያ ቀን አቆጣጠር በ2008 /እ.ኤ.አ 2013-2014 / የሚያከናውናቸውን ተግባራት እና የአፈፃፀም ምዕራፎችንም ያቀርባል፡፡

በተጨማሪም የዚህን አፈፃፀም አፈፃፀም ለማቀላጠፍ ሰነዱ ለCEGው አባልነት መመረጫ መመዘኛዎችን እና የአሰራር መዋቅሮችን ይዟል፡፡ እንዲሁም የCEGን መስራች አባላትን፣ አሁን ያሉት አባላትን እና ለተመራጭነት የታጩ ሰዎችን ዝርዝር አካትቷል፡፡ በCEGው መቻቻልን፣ ስልጡን የሆነ ውይይትን እና የተሳለጠ ሂደትን እና እፈፃፀምን ለማስፈን የሚያስችል የስነምግባር ደንብን በተጨማሪነት ይዟል፡፡

II. ስለ CEG የምክክር መድረኩ አጠቃላይ ማብራሪያ

CEG በኢትዮጵያ ያለውን ረጅም ጊዜ የቆየ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት የፈጠሩትን እና የሚያባብሱትን ቁልፉ ሀገራዊ ጉዳዬች ላይ የተለያዩ የህብረተሰብና አመለካከት ልዩነቶችን ያቀፈ አካታች እና አሳታፊ ሃገራዊ የምክክር መድረክ ለመፍጠር በነፃ/ገለልተኛ ኢትዮጵያውያን የተወጠነ ተቋም ነው፡፡

CEG እንደ ቡድን በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከማንኛውም የፖለቲካ ቡድን ተፅእኖ ነፃ የሆነና የማይወግን ሲሆን የጋራ ሚናውም የፖለቲካ አቋም ሳይዝ የውይይትን አስፈላጊነት፣ የአመለካከት እና ሌሎች የማንነት ልዩነቶችን ተቻችሎ ማለፍን፣ የሰብአዊ መብቶችን እሳቤዎችን እና የማህበረሰብ ብዝኀነትን የሚያበረታታ አመቻች ቡድን ነው፡፡

ሃገራዊ የምክክር መድረኩ በCEGው የሚመራ ሲሆን ከሀገር ውስጥ እና ውጪ ካሉ የማንኛውም የፖለቲካ አመለካከት አራማጅ የፖለቲካ ሀይሎች እና ማህበራዊ ድርጅቶች ጋር በሚያገናኙ ቡድኖች ድጋፍ ይደረግለታል፡፡ ይሄም የፖለቲካ ፖርቲዎችን፣ የሲቪል ማህበረሰቡን እና ድርጅቶችን፤ ቲንክ ታንኮችን፣ እምነትን መሰረት ያደረጉ ተቋማትን፤ የትምህር ተቋማትንና መሁራንን… ወዘተ ይጨምራል፡፡

III. የCEG የመጨረሻ ግቦች

/የተረጋጋች የበለፀገች እና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ/

የዚህ የሃገራዊ  ምክክር የመጨረሻ ግብ የተረጋጋች፣ የበለፀገች እና ዲሞክራሲ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡ CEG አላማ ያደረገው ጉባኤውን በማሳለጥ ለፖሊሲ አማራጮች እና ለነባር ተቋማዊ ማእቀፎች እና ፖሊሲዎች ማሻሻያ የሚሆኑ ግብአቶችን በማቅረብ ለመጨረሻው ግብ መሳካት ሀገራዊ አስተዋፅኦ ማድረግ ነው፡፡

IV. የCEG የአፈፃፀም ስልቶች

ነባር ሃገራዊ እውነታዎችን ተቀብሎ በማፅናት እና በተመሳሳይ ጊዜ የወደፊቱን ታሳቢ ያደረጉ አዳዲስ አመለካከቶችን በመቀበል ላይ የሚመሰረተው ሃገራዊ ምክክሩ የሚከተሉትን መርሆች ከግምት ውስጥ ያስገባል፡-

1/ ውጤታማነት፣ ከፍተኛ ውጤት እና ምላሽ፡ CEG የሚከተለው ስልቶች ምርጫ ላይ ተቀዳሚ መመዘኛ የሆነው ሃገራዊ ምክክርን እና የመጨረሻውን ግብ በማሳካት ላይ ውጤታማነትን እና ስኬትን ለማግኘት ማስቻል ነው፡፡ CEG ለሃገራዊ ምክክሩ ሀገራዊ ጉዳዮችን የሚያሳዩ አጀንዳዎችን መለየት ይገባዋል፡፡ በዚህም ቁልፍ ችግሮችን ግልፅ ግልፅ ቀላል እና አጠቃላይ በሆነ ሁኔታ ማዘጋጀትና መቅረፅ አለበት፡፡ እነኚህ አጀንዳዎች መልስ ካገኙ በአሁኑ ሰዓት በሃገሪቷ ላይ የተጋረጡትን ወይም ወደ ፊት የምትጋፈጣቸውን ብዙ ችግሮች ላይ ሰፊ ትርጉም ያለው ውጤት የሚሰጡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2/ ቅደም ተከተልን የጠበቀ እና ለስለስ ያለ የአገባብ ዘዴ፡- CEGው ምላሽን ለመገምገም በሚያስችል ለስላሳ አጀማመር ላይ ያተኩራል እንጂ የስሜታዊነት ምላሾችን በመፈጠር ከጅምሩ ሊያደናቅፉት ከሚችሉ ቆስቋሽና የሚጮሁ አቀራረቦች ይቆጠባል፡፡ CEGው አስፈላጊውን የፖለቲካ ተቀባይነት፣ የሁሉንም ባለድርሻዎች የምቾች ደረጃ የጠበቀና ቅቡልነት የሚያስገኝለትን ለስለስ ያለ አቀራረብ መጠቀም አለበት፡፡

ስለዚህ በእንቅስቃሴው መጀመሪያ በሃገራዊ ምክክር አስፈላጊነት ላይ የሚያስፈልገውን ፖለቲካዊ ፈቃደኝነት ከዋና የፖለቲካ ሀይሎች ለማግኘት እና በCEG ላይ እምነት እንዲያሳድሩ ለማስቻል ከፍተኛ ጥረት መደረግ አለበት፡፡ ለስላሳው አጀማመር የሚያተኩረው በሀገራዊ ችግሮች እና በየትኛውም “ዋና” ከኢትዮጵያ ውጪ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፖለቲካዊ ድርጅቶች ውድቅ መደረግን ያስከትላሉ ተብለው የማይጠበቁ ነገሮች ላይ ነው፡፡ ምሳሌ ተመሳሳይ ውክልና የምርጫ ስርአት /የ2013 የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ምርጫ/ የቋንቋ እና የትምህርት ፖሊሲ፣ ኦሮምኛን እንደ ሁለተኛ የስራ ቋንቋ መጠቀም ወዘተ

3/ ቀስ በቀስ እየተሻሻለ በምዕራፍ የሚሄድ አሠራር እና ግትር ያልሆነ አቋም፡ ተጨማሪ ፖለቲካዊ አለመግባባትን ሊፈጥር የሚችል ችኮላን ለማስወገድ ብሔራዊ ምክክሩ ተራማጅና እየጨመረ በሚሄድ የሚከወን ይሆናል፡፡ የአፈፃፀም ምዕራፎች ለCEG እና ለብሄራዊ ምክክሩ ቁልፍ ተሳታፊዎች ተጨባጭም ተራማጅም መሆን እንዲችሉ ይረዳቸዋል፡፡ የአፈፃፀም ምዕራፎች በተጨማሪም CEG እና የፖለቲካ ሀይሎችን የድርጊት መርሃ-ግብራቸውን ያለፉትን ምዕራፎች አተገባበር እንዲገመገሙ እና ቀጣይ መርሃ-ግብራቸውን ከልሰው እንዲቀርቡ ያስችላቸዋል፡፡ ይሄ አካሄድ ሂደቱን ለመቆጣጠር አወንታዊ ጎኖቹን ከፍ ለማድረግና እና የታዩ ድክመቶችን እና አደጋዎችን ለማረም የሚረዳን ነው፡፡ ለዚህም የተሳታፊ የትኩረት ነጥቦች፣ አገናኞች እና ፖለቲካዊ ሀይሎችን ብዛት የሚጨምሩ ተከታታይ ዙር ውይይቶች ይኖራሉ፡፡

የስብሰባው ድግግሞሽ እና የእምነት ደረጃ ሲጨምር የምክክር ሂደቱ ቀላል ካሉ ችግሮች ወደ ከባድ የብሔራዊ ምክክር ጉባኤ አጀንዳዎች ያድጋል፡፡ ይሄ ከላይ በተጠቀሰው መርህ 1 እና 2 መሰረት ይመራል፡፡

ከዚህ በመነሣት በምዕራፍ 1 CEGው የአባላት ምርጫን በኦፊሴል በመከወን እንዲሁም በዚህ ፅሁፍ እና ሌሎች አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ራሱን ያጠናክራል፡፡ ለብሔራዊ ምክክሩ ውስጥ የሚቀርቡ ሀገራዊ ጥያቄዎች ማዘጋጀት የሚጀመር ሲሆን በመጀመሪያ ዙር ውይይቶች ላይ የሚጋበዙት ግለሰቦች ቁጥር (ከዋና ዋና የፖለቲካ ሃይሎች የተውጣጣ አነስተኛ ቡድን ማእከላዊ አገናኝ ነጥብ እያገለገለ) በሂደት እየጨመረ ይሄዳል፡፡

ከዚያም ውይይቱና ብሔራዊ ምክክሩን ለመጀመር ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፍቃድ ይጠየቃል፡፡ ከዋና የፖለቲካ ሃይሎች ግለሰቦችን የመለየት እና ሃገራዊ ምክክሩን እና CEGን እንዲደግፉ የማሳመን ስራ ወድያውኑ ይጀመራል፡፡

ከሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ተወካዮች እንዲሁም ሁኔታዎች ሲፈቀዱ ደጋፊዎቻቸውን/ተከታዮቻቸውን ሊያስረዱ ፈቃደኛ የሆኑ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ይመረጣሉ፡፡ እነኝህ አገናኞች ተጋብዘው ከCEG ጋር ወይም CEG በሚያዘጋጃቸው መድረኮች የአንድ-ለአንድ ውይይቶችን ያደርጋሉ፡፡ በዚህ መልኩ ውይይት የሚደረግባቸው ጥያቄዎች እና ችግሮች በምዕራፍ 2 እና 3 ላይ ይበልጥ እየሰፉና እየተብራሩ ይሄዳሉ፡፡

4/ ሚስጢራዊነትና መተማመን መፍጠር፡

CEGው በምዕራፍ 1 እና 2 የሚያደርጋቸው ውይይቶች ከጥቂት ግለሰቦች ጋር ብቻ እና  ያለ ምንም የሚዲያ ሽፋን የሚደረግ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የተመረጡት ተወካዮችና አገናኞች የውይይት ነጥቦቹን እስከ ምዕራፍ 2 ምናልባትም እስከ ምዕራፍ 3 ድረስ ለሚወከሉት አካል/ህብረተሰብ ሳያጋሩ እንዲቆዩ ይጠየቁ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ይሄ ሚስጠረኝነት የፖለቲካ ሀይሎች ተመካክረውበት ወይም CEG ወስኖበት ይፋ እንዲሆን በመግባባት ላይ ከተደረሰ ሊቀየር ይችላል፡፡

5/ በተሻለ መልኩ ነጥረው መውጣት ከቻሉ ጋር መስራትና ጎታች ችግሮችን መፍታት፡- ለዚህ እንቅስቃሴ ደጋፊ ወይም እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ – ማለትም በከፍተኛ ወይም በዝቅተኛ ተነሳሽነት የሚደግፉ እና እንቀስቃሴውን ሊያግዱ ወይም ሊያዘገዩ አካላትን/ግለሰቦችን መለየትና ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ቀጥሎም CEG ደጋፊዎቹን ለተሻለ ድጋፍ ማበረታታት የማይደግፉትን ደግሞ ቀርቦ በማነጋገርና ከተቻለም በማሳመን የእንቅስቃሴው እንቅፋቶች እንዲወገዱ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

ለዚህ አንድ መንገድ ሊሆን የሚችለው ሊያደናቅፉት ከሚችሉት ጋር (ለምሳሌ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የፖለቲካ ፖርቲዎች መሪዎች፣ እና ቁልፍ የሚዲያ ሰዎች ወዘተ) ቅድመ ምክክር በማድረግ እንቅፋቶቹን ለማስቀረት መጣር ነው፡፡

7/ በፍላጎትና ብቃት ላይ የተመሰረተ አቀራረብ – ብዙ በመንግስት ውስጥ ያሉ ግለሰቦች፣ የተቃዋሚ ፖርቲዎች እና የሲቪል ማህበረሰቦች ሀገራዊ ምክክሩን ለመርዳት ፍላጐት ሊኖራቸው ነገር ግን ፍላጐታቸውን ወደ ድርጊት የመቀየር ሀይል ላይኖራቸው ይችላል፡፡ በCEGው ቀጣይ ሂደት ላይ አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ ቢሆንም የምንቀርባቸውን የትኩረት ነጥቦችን ለብሄራዊ ምክክሩ ያላቸውን ድጋፍ ብቻ ሳይሆን በተጨማሪም በሀገሪቷን ፖለቲካዊ ምህዳር በተለይም በሚወክሉት የህብረተሠብ ክፍል ዘንድ ያላቸውን ቦታ ከግምት ማስገባት ጠቃሚ ነው፡፡

8/ ከፍተኛ ታማኝነት /ሀቀኝነት/፡- በዳያስፖራም ሆነ በሃገር ውስጥ ጡዘት በሚታይበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደ CEG አይነት እንቅስቃሴ ከፍተኛ የመንግስትን፣ የህዝብን እና የሚዲያን ትኩረት ያገኛል፡፡ ይህ ምናልባት ጥሩ ወይም መጥፎ ሊሆን ይችላል፡፡ CEG ለከፍተኛ ለህዝባዊ ትኩረት እና የሚዲያ ትችት የመጋለጥ እድሉ ሰፊ ነው፡፡ በዚህ መሰረት CEGው ለመሠል ትእይንቶች እና ተለዋዋጭ ግጭቶች መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡

ከእነዚህ ሁኔታዎች አንዱ በCEGው አባላት በማንነታቸው በብሄራቸው ወይም በፖለቲካ አቋማቸው እንዲሁም/ወይም በCEGው አላማዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ነው፡፡ ይህን መሠል ትችቶች ምናልባት በጠርዝ ካሉ የገዢው ፖርቲ አካላት፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ወይም ከሚዲያ አካላት ሊመጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ CEGው በተቻለ መጠን ለመሰረተ ቢስ ትችቶች ጭምር ከፍተኛ ትእግስት እና ሃቀኝነትን በቃላት እና በድርጊት ማሣየት አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም CEGው ለስብሰባዎች እና ለአሰራሮች እና ለስነምግባር ደንቦች አፈፃፀም ከፍተኛ ስነስርአት ያስፈልገዋል፡፡

9/ የእርስ በእርስ መተማመንን መገንባት ፡- በተለያዩ የፖለቲካ ፖርቲዎች መሃከል መተማመንን ለመገንባት CEG የመንግስት፤ የገዢ ፖርቲ፣ የተቃዋሚ ፖርቲዎችን፣ የዳያስፖራ ተቃዋሚዎች…ጥያቄዎችንና ስጋቶችን ለማወቅና መልስ እንዲያገኙ ለማድረግ ይጥራል፡፡

10/ ተሣታፊዎች የደህንነት ዋስትና እና የተመቻቸ መድረክ፡ አስተማማኝና ምቹ ቦታን ማዘጋጀት፡- CEG ነፃ የሆኑ እና ምቹና አስተማማኝ ተብለው የሚታሰቡ እና ሁሉም ቁልፍ የፖለቲካ ሀይሎች እንዲሳተፋ የሚያደርግ ምቹ ቦታን /በተለይ በምዕራፍ 3/ ያዘጋጃል፡፡ ይህ የሚሆነው ምናልባት አዲስ አበባ ወይም በሀገሪቱ ውስጥ እና ወደ ኋላም በጥናት ሌሎች ሀገራትን በሚጨምር መልኩ ነው፡፡

11/ ሀገራዊ ባለቤትነት፡- የምክክር መድረኩ በኢትዮጵያውያን ባለቤትነት የተያዘ እንዲሆን፣ የምክክሩ ውጤቶች በኢትዮጵያውያንና ለኢትዮጵያዊያን መሆኑ እና የውጭ እርዳታ ሰጪ ተሳትፊዎች ከእኛ ችግሮች ጋር ሊጣጣም የማይችሉ አጀንዳዎችን ይዘው ቢንቀሳቀሱ እንኳን አግባብ ያልሆነ ተፅእኖ ሊያርጉብን እንደማይችሉ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም የኢትዮጲያውያንን ሙሉ ተሳትፎ ለምክክሩ ጥልቀት በመስጠት፣ በመታመን፣ በሂደት እና ውሳኔዎች ላይ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

V. ቁልፍ አገራዊ አጀንዳዎች/ብሔራዊ ጥያቄዎች

በCEG በሲጂኢና እና ሌሎች ቁልፍ ተሳታፊዎች ወደ ኋላ ላይ ከሚካተቱ ሌሎች ችግሮች/አጀንዳዎች በተጨማሪ ሃገራዊ ምክክሩ በሚከተሉት ቁልፍ አጀንዳዎች እና ሀገራዊ ጥያቄዎች ላይ ያተኩራል

1/ አቃፊ ዲሞክራሲ እና ህገመንግስታዊነት

ሀ. የምርጫ ስርአት፡- የምርጫ ህጐች /የተመጣጠነ ውክልና ወይስ የአብላጫ ድምፅ/፣ የምርጫው አስፈፃሚ አካላት ሃቀኝነት እና ነፃነት

ለ. ከሽብር፣ ከሚድያ፣ ከፖለቲካ ፖርቲዎች እና ሲቪል ማህበረሰቡ ጋር የተገናኙ ህጎችንና አሰራሮችን ማሻሻል

ሐ. ዲሞክራሲያዊ እና ህገ መንግስታዊ ተቋማትን ማሻሻል ፡- የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋፋት ለታጋሽ እና ለብዝሀ ማህበረሰቦች ነፃነት የሚሰጥ ምህዳር ለመፍጠር ሁሉን እኩል የሚያገለግሉ የዲሞክራሲያዊ ተቋማትን (ለምሳሌ እንደ የሰብአዊ መብት ኮምሽን፣ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የሲቪል ማህበረሰብ ምዝገባ ኤጀንሲ፣ የምርጫ አመራር ቦርድ፣ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት፣ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ወዘተ …) ህገ መንግስታዊ ቁመና መሻሻል

መ. የዳኝነት ስርአት፡- በዋናነት የማያዳላ፣ ነፃ የሆነ፣ እና ድፍረት ያለው የዳኝነት ስርአት፣ የዳኞችን ሹመት ፍትሀዊነትን እና የዳኞች፣ የፍርድ ቤት ፕሬዜዳንቶችና እና አስተዳደር ሃቀኝነት እንዲሁም ሙስና

ሠ. የውህዳን አቃፊ ህገ መንግስታዊ ከለላ፡-   በአሁኑ ሰአት ባለው ብሔር ተኮር አግላይና ዲሞክራሲያዊ ያልሆነ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እና መሰባሰብን በሚያበረታታ የፖለቲካ ምህዳርን የሚያሻሽልና ቀላል የማይባሉ የብሄር ማህበረሰቦችን የደህንነት ስጋት የሚቀርፍ የፖለቲካ እርምጃዎችን ማጠናከር

ረ. ሚዲያው፡- በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያሉ፣ የህዝብ እና የግል፣ ባህላዊ እና አዲስ ማህበራዊ ሚድያን ጨምሮ ያላቸው የሚዲያ ነፃነት እና ያለባቸው ኃላፊነት

ሰ. የመቻቻል እና የብዝኃነት ባህል፡- ለምሉዕ ለውጥ የሚደረግ የህዝብ ተሣትፎ የሚከተሉትን ለመቅረፍ ይረዳል፡፡

* ያለመቻቻል ፖለቲካ እና የዜሮ ድምር ጨዋታ

* የፍርሃት፡ የቂም መያዝ እና የጥላቻ ፖለቲካ፣

* በትውልዱ መካከል እና ካለፈው ትውልድ ጋር በፖለቲካ ባህል እና ሌሎች የመቻቻል እና የብዝኃነት ባህሎች ላይ የሚታይን የውይይት እጥረት

2/ የብሄር ማንነት እና ፌደራሊዝም፡

ሀ. በማንነት እውቅና እና የብሄር ማንነትን ከመግለፅ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ግጭቶች

ለ. እንደ ዞን፣ ወረዳ በመሳሰሉ አስተዳዳራዊ ሁኔታዎች መሠረት የሚፈጠሩ ግጭቶች

ሐ. በአስተዳደር ወሰን ምክንያት የሚፈጠሩ ግጭቶች

መ. በውሃ እና መሬት ባለቤትነት ምክንያት የሚፈጠሩ ግጭቶች

ሠ. በማንነት ላይ የመወሠን ድምፅ አሰጣጥ

ረ. በአዲስ አበባ /ፊንፊኔ/ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች

3/ የመሬት አስተዳደር

ሀ. የመጣቱ መሬት ማጣት

ለ. የልማት ፕሮጀት ከቦታ መፈናቀል

* ትራንስፖርት

* ከተማዊነት – የከተማ እድሣት፣ የተቀናጀ የከተማ ፕላን

* የኢንዱስትሪ ፖርክ፣ የስኳር ልማት ኢንዱስትሪ ወዘተ

* የአካባቢ ማህበረሰብ ተጠቃሚነት

* ራስን ማስተዳደር እና ፌደራሊዝም

* በማንነት ጥያቄ መደራጀት (Overlapping with identity questions)

4/ ሙስና እና ታማኝነት በህዝባዊ አገልግሎት

ሀ. በህዝባዊ አገልግሎት ስር ያለ የሙስና ባህል /መሬት፣ የግንባታ ጨረታዎች፣ የአካባቢ አስተዳደር አገልግሎት፣ የፍርድ ቤት እና የፍርድ አስተዳደር ወዘተ../ የመሣሠሉ አገልግሎቶች ዙርያ

ለ. የፌዴራል ስነምርባር እና ፀረሙስና ኮሚሽን

ሐ. የፌዴራል ኦዲተር

5/ የወጣቱ ጥያቄ

ሀ. ስራ ማጣት

ለ. ድምፅ አልባነት

ሐ. ስደት

መ. ዝቅተኛ /የማይጠቅም ችሎታ/

ሠ. የትውልድ መወራረስ/መግባባት አለመኖር

6/ ሀይማኖት እና ግዛት

ሀ. በሀይማኖት ምክንያት የሚነሱ ግጭቶች

ለ. የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥያቄ

ሐ. ሽብርተኝነት እና ፅንፈኝነት

7/ ትምህርት እና የቋንቋ ፖሊሲ

ሀ. የትምህርት ጥራት

ለ. የፌዴራሊዝም እና የቋንቋ ፖሊሲ

ሐ. አማራጭ የፌዴራል የስራ ቋንቋዎች

8/ አካታች/አቃፊ የሆነ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት እና የድህነት ቅነሳ፡-

ሀ. ድርቅ እና ረሀብ፣ የመቋቋም አቅም እና የማህበራዊ ደህንነት

ለ. ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት

ሐ. የእድገት አካታችነት /የጠብታ መዳረስ ኢኮኖሚ ወይስ የሃብት ክፍፍል ጥቅሞች) (trickle-down effect vs distributional benefits)

መ. የአካባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥ

ሠ. የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር

9/ የመከላከያ እና የፀጥታ ዘርፍ እና ህገ-መንግስታዊነት

ሀ. የመከላከያ ሰራዊት እና ህገመንግስታዊ የሲቪል ቁጥጥር

ለ. የመከላከያ ሰራዊት እና የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች

ሐ. የደህንነት የፌዴራል ፖሊስ እና ክልላዊ የፖሊስ ሀይሎች መሃከል የፖለቲካ ውግንና ያለመኖር

VI. የCEG ምዕራፎች እና ተግባራት

CEG የሚከተሉትን የተወሰኑ ተግባራት በሚቀመጠው ምዕራፍ እና የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ያደርጋል

ምዕራፍ 1. /January 2013/ CEGውን እና የሃገራዊ ምክክርን አፈፃፀም ስልቶች መንደፍ እና ማጠናከር

1/ የሃገራዊ ምክክርን አፈፃፀም ስልቶች (ይህንን ፅሁፍ ጨምሮ) መርምሮ መወሰን

2/ ለCEGው የአባላት ምርጫ መስፈርት እና የስነምግባር ደንብ መምረጥ እና ማፅደቅ (ዝርዝር ከታች አለ)

3/ ተጨማሪ አዳዲስ አባላቶች መምረጥ /ዝርዝሮችን ከታች)

4/ የመጨረሻ የCEG አባላቶችን ዝርዝር ማዘጋጀት እና አባላቶችን መጋበዝ

5/ ዋና ዋና ሀገራዊ ጥያቄዎችን መለየት እና በብሄራዊ ምክክሩ ወቅት በአጠቃላይ በጥሩ ሁኔታ ለውይይት እንዲቀርቡ ማድረግ

6/ ከሁሉም ፖለቲካዊ አስተሳሰቦች የተውጣጣ አነስተኛ የተወሰኑ ግለሰቦች ማዘጋጀት (ረቂቅ ዝርዝር ከታች አለ) እና CEGውን እንዲደግፉ ማሳመን/ማግባባት እንዲሁም የCEGው የትኩረት ነጥቦች በመሆን ከተሳታፊ ድርጅቶች/ሀይሎች ጋር (በምዕራፍ 2) ለማገናኘት የሚያመቻቹ እንዲሆኑ ማድረግ

7/ ለዋና አላማዎች ቁልፍ ተግባራትን መለየት

ዕራፍ 2 ከሁሉም ፖለቲካዊ ሀይሎች ጋር መመካከር / በAugust 2013/

1/ መደበኛ ያልሆኑ ግንኙነቶችን መፍጠር (በCEG አባላት በኩል)

2/ የትኩረት ነጥቦችን (አገናኞችን) ለውይይት መጋበዝ

3/ ከቁልፍ የመንግስት መሪዎች፣ መሪ እና ተቃዋሚ ፖርቲዎች እና ከሌሎች ደጋፊዎች ጋር የመጀመሪያ ዙር ምክክር

4/ ዋና የሀገራዊ ጥያቄዎችን መለየት፣ ማርቀቅ እና ለሃገራዊ ምክክሩ ማቅረብ

5/ በሃገራዊ ምክክር አፈፃፀም ስልቶች ላይ መወያየት እና ለምዕራፍ 3 ንድፍ ማውጣት

6/ ለምዕራፍ 3 የሚደረጉ የዝግጅት ስራዎች (አካሄዶች፣ ሰሌዳ፤ ዘዴዎች፣ አዳራሾች እና የአፈፃፀም ደንቦችን) ያካትታል፡፡

እራፍ III የሀገራዊ ምክክር ፎረሞች /በJanuary 2014 እ.ኤ.አ ይጀምራል/

1/ አጠር ያሉ የውይይት አቅም መገንቢያ ስልጠናዎች፤ ለመዳኘት እና እቅድ የሚደረጉ ጉዞዎች፤ የፅ/ቤት ድጋፍ

2/ በተመሰሳይ ጊዜም ፖርቲዎችን ከሚወክሉት የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር እንዲወያዩ እና መረጃ እንዲሰጡ ማበረታታት

3/ ከሀይማኖታዊ ተቋሞች እንዲሁም ከተለያዩ አካላት የህዝብ ጋር የማብራሪያ መድረኮችና እና ጠንካራ ግንኙነትን መመስረት

4/ ብዙ ዙር የብሄራዊ ምክክር መድረኮችን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት ማመቻቸት

5/ የዙሮቹን ውጤት እና ከመድረኮቹ የተገኙ የማሻሻያ ሃሳቦችን በይፋ ሰነድ ማቅረብ

VII. CEG አባልነት

ሀ. ለCEGው አባልነት ምርጫ መመዘኛዎች

የብሄራዊ ምክክሩ ስኬት በCEG አባላት የግል እና የወል ገፅታ፣ ታማኝነት፣ ታታሪነት ላይ ይመሰረታል፡፡ የአባልነት ምርጫውም የሚከተሉትን መመዘኛዎች ያካትታል፡፡

ሀ. አካታችነት እና የልዩነቶች መወከል፡- የCEGው አባላት መመረጥ ያለባቸው ከሁሉም የኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ አባላት ውስጥ፣ ሀይማኖታዊ፣ ዘር፣ እድሜ/ወጣት/ እና ፆታ/ሴት/ ውስጥ መሆን አለበት

ለ. ለሀገራዊ ምክክሩ የፖለቲካ ሀይሎች ተቀባይነት ማግኘት አስፈላጊ ነው፡፡ አባላቶች ለሀገራዊ ምክክሩ ከሁሉም ተሳታፊዎች እና ፖለቲካዊ ሀይሎች ጋር መነጋገር የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

ሐ. ያለማዳላት /ከገለልተኝነት የተለየ/ ፡-CEGው ሁሉንም ተሳታፊዎች በፍትሃዊነት እና በተመጣጠነ ሂደት ማስተናገድ እና እድሎአዊነትን ማስወገድ

መ. የመቻቻል መርሆች፡- ሁሉንም አይነት ፖለቲካዊ አስተሳሰቦችን ለማድመጥ የሚችል ሰፊ እና ክፍት አስተሳሰብ

ሠ. ሃቀኝነት

ረ. ሚስጥር ጠባቂነት

ለ. አሁን ያሉት የCEG አባላት

በአሁኑ ሠአት CEG የሚከተሉት አባላት አሉት፡፡ (ሊሰፋም ይችላል) በCEG የሚመረጡ ሊቀመንበር፣ ምክትል እና ፀሐፊ

VIII. የCEG የስብሰባ የአፈፃፀም ደንቦች

ሀ. የCEGው ስብሰባዎች መደበኛ መሆን እና ቋሚ ቀናቶች እና ቦታ ሊኖረው ይገባል

ለ. CEGው ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና CEGው በላቀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ ስብሰባው እንደተካሄደ እና ኃላፊነቱን እንደተወጣ የሚያረጋግጥ ፀሐፊ መምረጥ ይኖርበታል

VIX. የስነምግባር ደንብ     

1/የስነ ምግባር ደንብ

ሂደትና የአሰራር ስርዓት

ከ1-3 ወር

ከ4-8 ወር

ከ8-14 ወር

ከ14-20 ወር

ከ20-24 ወር

2/ የመሻሻያ ለውጥ

ምዕራፍ 3፡

ህዝባዊ/ህዝብ ነክ የውይይት መድረክ

ብሄራዊ የውይይት መድረክ

ምዕራፍ 2፡ የፖሊቲካ ፓርቲዎች የውይይት መድረክ

ምዕራፍ 1፡ ምክክር-የአገናኝ ቡድኖች

ጠቃሚ/ቁልፍ የፖለቲካ ሐይሎች

የCEG- አሳላጭነት ሚና

CEG- የአተገባበር እቅድ

**********

Dr. Mehari Taddele Maru, who is International Consultant on African Union affairs and Research Fellow at the NATO Defence College.

more recommended stories