ኣሃዳዊነት እና ፌዴራላዊነት በኢትዮጲያ የፓለቲካ መድረክ ፍጥጫ

(አማኑኤል አለማየሁ (ደጀና)

በኢትዮጲያ እየሆነ ያለው ፈጣን ፖለቲካዊ ለውጥ በጥሞና መገምገም እና የአገሪቱን እጣፈንታ በምን መንገድና ሁኔታ እየወሰነ እንዳለ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡

ኢህአዴግ አሁን እንደ ግንባር መንቀሳቀስ አቁሟል ትንሽ እንቅስቃሴ ቢኖረውም በዜሮ ማርሽ እንደሚንቀሳስ መኪና ሞትር አጥፍቶ ነገር ግን በነበረው የግፊት (inertia) እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ይህ አይነቱ እንቅስቃሴ ጠጠረም ቢሆን ሊያቆመው ይችላል፡፡

አሁን በኢትዮጲያ እየተደረገ ያለው እስርና ፍቺ አላማው ለብዙሃን ግልፅ እንዳልሆነው ሁሉ ለኢህአዲግ አባላትና አባል ድርጅቶችም ግልፅ አይመስለኝም፡፡ በመድረኩ ላይ ተፋጠው የበለጠ ህዝበኛ ድምፅ ለማግኘት እየሞከሩ ያሉት በባህሪያቸው ሊቀላቀሉ የማይችሉ ነገር ግን በአንድ የጋራ አጀንዳ የተሰባሰቡ ሃይሎች ናቸው፡፡

የኢትዮጲያ የፖለቲካ ስርዓት ምስረታው የፈለገው የዳቦ ስም ይውጣለት ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ ከመሆን በዘለለ ኢትዮጲያ እንደ አገር ጠብቆ ለመቆየት የሚያስችል ጉልበት/ ዓቅም የለውም፡፡

ብዝሃነትን ማስተናገድ የግድ ነው፡፡ ብዝሃት የብሄር፣ የሃይማኖት፣ የአስተሳሰብ ብሎም የፖለቲካ ፓርቲዎች በተጨማሪም የመንቀሳቀስ፣ ሃብት የማፋራት መብቶች ድፈጥጦ መኖር ስለማይቻል ተወደደም ተጠላም ኢትዮጲያ ውስጥ ሊገነባ የሚችለው ስርዓት ሂደት ዲሞክራሲያዊ መሆን አለበት፡፡ ዴሞክራሲያዊነትን ለጊዜው አቆይተን አንድነት ላይ ብቻ እንስራ ቢባል፤ የአንድነት ሃይሎች/ የአሃዳዊነት ሃይሎች በራሳቸው ብዙህነት ያላቸው ናችው ስለሆንም ያላቸውን ልዮነት ማስተናገድ ስለማይችሉ ወደ ሽኩቻ ብሎም እንደ 1960ዎች እና 1970ዎች ወደ መጠፋፋት ሊያመሩ ይችላሉ፡፡ ስለሆንም ልዮነት ማስተናገድ ለአሃዳዊ ሃይሎችም ቢሆን አስፈላጊ ነው፡፡ በዋናነት ግን ኢትዮጲያ ውስጥ ያለው እሳቤ (አገራዊነት እሳቤ) ሊሳካ የሚችለው ብዙህነትን አምኖ እና ብዙህነትን አስተናዶ መሄድ ነው፡፡

በተጨማሪም ይህ የፖለቲካ ስርዓት ግንባታ ልማታዊ መሆን አለበት፡፡ የተራበ፣ ሃብት ማፍራት የተከለከለ ዜጋ መብት ብሎ ነገር አይገባውም ስለሆነም ከራሃብ፣ ከስራ አጥነት እንደዚሁም ከሁሉም የልማት ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ልማት መምጣት አለበት፡፡ ስለሆነም ማንም ስልጣን ላይ ይወጣ ማንም እነዚሁን ሁለቱን ጥንድ እሳቤዎች በጠንካራ ተቋማዊ አፈፃፀም አስደግፎ ማምጣት ካልቻለ እንደ መንግስትም አገሪቱ እንደ አገርም ህልውናዋ አደጋ ላይ  ይወድቃል፡፡

በኢህአዴግ እየተፈጠረ ያለው ክስተት፡-

ኢህአዴግ አሁን አሁን የግንባር ስሙን እንጂ የአራት ድርጅቶች ውህድነቱን ሽርሽሮ በዚሁ ከቀጠለ በውስን ጊዜ ውስጥ ወደ መበታተኑ እና የአራት ድርጅቶች ጥምረት መሆኑ ቀርቶ በኢትዮጲያ የፖለቲካ ፓርዎችን ቁጥር ቢያንስ በሶስት ወደ መጨመሩ ሊያመራ ይችላል፡፡

በኢህአዴግ መድረክ ላይ እንደስልት እና እንደ መፈክር ሁለቱ ድርጅቶች በተለይም ኦህዴድና ብአዴን ይዘውት የተነሱት የትግራይ እንዲሁም የህውሓት የበላይት የሚለው መፈክር ህውሓትን ጥግ እስከ ማስያዝ ወይን ህውሓት ከፌዴራል ጉዳዮች እስከ ማፈግፈግ በማድረሱ እና የዚህ የበላይት ዜማ አቀንቃኞች ኢህአዴግ ውስጥ የበላይት ያገኙበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በርግጥ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች የተለየ ስለተጠቀመ አይደለም በርግጥ ህውሓት የርእዮት አለምና የታሪክ ቅድሚ (claim) ይኖረው ይሆን እንደሆነ እንጅ ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ እንኳን የበላይት ሊኖረው ይቅርና ውስጣዊ አደረጃጀቱን በቅጡ መምራት የቻለ አልበረም ፤ ስለዚህ ህወሓት የበላይ ሊሆንበት ይችል የነበረውን እድል (የበላይ መሆን ባልደግፍም) ያመከነው ከ1983 ዓ/ም እስከዚህ 1993 ዓ/ም በነበረው ጊዜ ብሎም አቶ መለስ ማለት ህወሓት ማለት ነው ለሚሉትም በአቶ መለስ ዜናዊ ጊዜ ነው፡፤

በህወሓት/የትግራይ የበላይነት መፈክር የተሰባሰቡት ሁለቱ ሃይሎች በባህሪም በአምሳልም የሚመሳሰሉ አስተሳሰቦች ማራመድ የሚችል ፓለቲካዊ ፍጥረቶች (political entities) አይደሉም ነገር ግን ህውሓት ጠቅልሎ ተሸማቆ አስተሳሰቡን ከማራመድ እዲያፈገፍግ ደኢህዴንንም ከፖለቲካዊ ቁብ ሳያስገቡ የኢህአዴግ መድረክ የሁለትዮሽ ካደረጉ በኋላ እናስብበታለን ወዳሉት ቡድናዊ ግጭት የመግባት እድላቸውን እያሰፉ ያሉ ይመስላል፡፡

በጣም ትኩረት ሊደረግባቸው የሚጋባ መስለው የሚታዮኝ ክስተቶች፡-

1/ ህወሓት ከተጠበቀው ፍጥነት በላይ ፈጥኖ የፌዴራል መዋቅር ውስጥ የነበረውን ሚና በመተው ፊቱን ወደ ክልላዊ አጀንዳ ማዞር፡፡ ይህ እንቅስቃሴ በፀረ ህወሓትንት የተሰለፉት ሁለቱ ሃይላት የውስጣዊ ወይን የሁለትዮሽ ጥምረታቸው ቀጣይ ጥያቄዎች ከመዘጋጀታቸው በፊት በፍጥነት እንዲያነሱ እና አንዳቸው አንዳቸውን በጥርጣሬ አይን የሚያዮበት ሁኔታ ከገመቱት ቀድሞ እዲከሰት አድርጎታል፡፡

2/ የጠራ ርእዮት አለም አለመኖር፡- አሁን እየተነሱ ያሉት ፖለቲካዊ ጥያቄዎች እየተከተሉ በመንጎድ ለመመለስ መሞከርና ማለቂያውም ይሁን መዳረሻው ወደ ማይታወቅ ስርዓት አገሪቱን ወደ መውሰድ ደረጃ እየደረሰ ነው፡፡ ለምሳሌ ወንደም ሴትም መብታቸው እንዲከበር መደረግ አለበት ብሎ በህግ የተደነገገውን ህገመንግስት የጣሰ/የደፈረ እንዲሁም የህግ አስከባሪዎችን በጀምላ የገደለ፣ በተጨማሪም የሃገር ሃብትና ንብረት የዘረፈን ስው/ሰዎች ፈቶ ነገር ግን ሴት የደፈረን ብቻ ተጠያቂ የሚያደርግ እሳቤእያየን ነው (በርግጥ ሴት መድፈር አውሪያዊ ባህሪ ነው የሞት ቅጣትም ሲያንስ ነው)፡፡ ወንጀል ተጠያቂና ተጠያቂነት የሌለው የሚል እሳቤ ህዝበኝነት እንጅ የፖለቲካ አመራር መርህ አለመኖሩን ያሳያል፡፡ ህግ ስርዓት ማስከበር የማይችል መንግስት ዛሬ ያፈረሰውን ወይንም የበተነው ነገ መሰበሰብና መገንባት የሚቀል አይመስለኝም፡፡ ልክ ጎርፍ የሚወስደው ሰው ያገኘውን እንደሚጨብጥ ሁሉ ሁሉን ነገር ባንድ ጊዜ ለመንካት እየተሞከረ ያለ ይመስላል፡፡

3/ደጋፊ የመያዝ ሩጫና ሽኩቻ፡- አሁን እየታየ ያለው ማን ቀድሞ ነጥብ አስመዝግቦ የደጋፊን ቁጥር መቆጣጠር ቻለ የሚል ነው፤ ህዝብ ሊወደው ይችላል በብዛት ሊደመጥ የሚችል ቃል አለ ከተባለ ለመጠቀም መሞከር ይታያል፡፡ ለምሳሌ የብአዴን ሊቀመንበርና ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን “ቄሮ የለውጥ ሞተር ነው!” የሚለው አባባላቸው ቄሮ የኢህአዴግ ሊቀመንበር እንዳልመረጠ ስለጠፋቸው አይመስለኝም ነገር ግን ተሰብሳቢው ሊወደው ይችላል ተብሎ የተነገረ ነው፡፡ በሌላ አብነት ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አሕመድ በወንጀል የተፈረደበትን ይሁን ህዝብን እንደ ህዝብ መጥፋት አለበት ብሎ ሲሰብክ የሚውለውን የፖለቲካ አራማጅና ሚድያ ከክስና ከተጠያቂነት ነፃ በማድረግ ደጋፊ ማሰባሰብ ይችላል የሚለው እሳቤ ነው፡፡

አሁን የኢህአዲግን የበላይነት ለመቆጣጠር እየሞከሩ ያሉት ከሁለት ፅንፍ የሚነሱና በመደማመጥ በመነጋገር የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ መፍጠር የማይችሉ ሁለት እሳቤዎች ናቸው፡-

1/ ብዝሃነትን መሰረት ባደረገ ፌዴራሊዝም እጠቀማለሁ ነገር ግን እኔ ካልመራሁት ሞቸ እገኛሁ የሚለው ሃይል ነው፡፡ ይህ አይነት እሳቤ የሚያራምደው ሓይል ቁጥርን መሰረት ያደረገ እና የይስሙላ አሳታፊነት ተጠቃሚ በመሆኑ ምክንያት ትልቁ እይታው ስልጣን መቆናጠጥ እንጂ ስልጣን ከያዘ በኋላ ስለሚከሰተው ነገር ወይን ስለሚያጋጥመው ፈተና ብዙ ያሰበ አይደለም፡፡ ለምሳሌ በየክልሉ ያለው መሰረታዊ ጥያቄ የስራ እጥነት፣የመሰረተ ልማት አለመሟላት፣ የመልካም አስተዳደር እጦት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እነዚህን ችግሮች መፍታት የሚያስችል ተጨባጭ ችግር ፈቺ መፍትሄ ለመፈለግ ከመሮጥ ይልቅ የህዝብ ጩህት ማስታገስ ይችላሉ ተብለው የተገመቱ ነገር ግን ከእውነታው ጋር (objective reality) የማይገናኙ እርምጃዎችን ማስቀደም ነው፡፡ እነዚህ እንደ ትልቅ አጀንዳ አድርጎ እየወሰዷቸው ያሉትን እርምጃዎች በተጨባጭ የስራ እድል ሊፈጥሩ አይችሉም፣ በርግጥ የመልካም አስተዳደር ችግር ሊፈቱም አይችልም ምክንያቱም የስራ እድል ያልተፈጠረው አንዳርጋቸው ፅጌ ስለታሰረ አይደለም፣ የመልካም አስተዳደሩ ያሉና የነበሩ ሰዎች እነዚህን አቅፎ የያዘው ድርጅታቸው ባላቸው የበሰበሰ ፖለቲካዊ እሳቤና የአቅም፣ የግልፅ ራኢ እንዲሁም ከሙስና የፀዳ አመለካከት እጦት የፈጠረው ነው፡፡ በመሆኑም መሰረታዊ ነገሩን ሳይፈቱ በጨሁትና በጫጫታ ችግር ለማስታገስ መሞከር የፈስ ሽታን በጩህት ለመሸፈን ከመሞር አይለይም፡፡ የፈለግነውን ያክል ብንጮህ ፈሱ እደሆን መሽተቱ አይቀርም፡፡

2/አሃዳዊነት አቀንቃኝ እሳቤ፡- ይህ እሳቤ የኢትዮጲያ ብሄርና ብሄረሰቦች በህገመንግስት እውቅና ማግኘትም ይሁን በፖለቲካው መድረክ ለመጫውት ያላቸውን መብት በመካድ እና የኢትዮጲያ አንድነት ሊያረጋገጥ የሚችለው በብሄር/ብሄረሰብ እና አሰፋፈር ተኮር ፌዴራሊዝም ሳይሆን በአሃዳዊ አስተዳደር ነው፡፡ ብዝሃትን የተቀበለች አገር ከመመስረት በአንድ አስተዳደርና በአንድ ማንነት መሰረት ያደረገ የግዛት አስተዳደር ያላት አገር የሚመኝ እና የሚጥር እሳቤ አራማጅ ነው፡፡ የኢትዮጲያ ውስጠ ግዛት አስተዳደር ብሄርንና መልካአ ምድርን (ethno-geographic) መሰረት ከሚያደርግ መልክአ ምድራዊ ብቻ ሆኖ መቀረፅ ይገባዋል የሚል ነው፡፡ የዚህ አይነት አስተሳሰብ የሌሎች ህልውና በመካድ የሚጀምር በመሆኑ በተራ ቁጥር አንድ የገለፅኩትን እሳቤ ህልውና ሳይቀር የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ ይክዳል፡፡

እነዚህ ሁለት እሳቤዎች በኢህአዴግ ውስጥ ለመግነን ምክንያት ያደረጉት የህወሓት በኢህአዴግ ውስጥ የነበረው ታሪካዊ እና እሳቢያዊ (ideological) ህልውና ነበር፡፡ ሁለቱም ሃሳቦች ህወሓትን እና የትግራይ ህዝብ በጠላትነት ፈርጀው ለስልጣን ያደረጉት መሽቀዳደም እና ህወሓት ሳይጠበቅ እዲሁም ሳይንገታገት በፌደራል ደረጃ የነበረውን ሚና በተሸናፊነት ወይም በስልታዊ ማፈግፈግ በቦታው መቆየት ባለመቻሉ ምክንያት ጠላት ተብሎ የሁለቱ እሳቤዎች የጋራ ሊያደርጋቸው የሚችል መፈለግ አለበት አንዱ አንደኛውን በማሞገስ ማሰቢያ ጊዜ ማግኘት አለበት፡፡

1/ የፅንፈኛና የብሄር ብሄረሰቦች ህልውና እውቅና ማግኘት አጥብቀው የሚቃወሙ ሃይላትን ከእስር መፍታት ጀምሮ የሃገሪቱ ፓርላማ በአሸባሪነት የፈረጃቸውን ግለሰቦች ከፓርላማው እውቅና ውጭ ከተጠያቂነት ነፃ እንዲሆኑ መወሰን፡፡

2/ የአሃዳዊ አስተሳሰብ አራማጆች የሚወዱት እና አፍ ለማስያዝ የሚሞክር አሃዳዊ ስብከቶች ማዘውተር፡፡

3/ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ባማግለለ አግላይ ግንኝነቶች በማድረግ በጋራ የፀደቀውን ህገመንግስት በግላጭ እየጣሱ ተናጠላዊ ውሳኔ እየወሰኑ መሄድ የመሳሰሉት ጥቂት ማሳያዎች ናቸው፡፡

የሁለት ዝሆኖች ጠብ ለሳሩ ይተርፋል

አሁን ከላይ የጠቀስኳቸው ሁሉት እሳቤዎች በተፈጥሮአቸው በአንድ ወቅት በአንድ የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ሊኖሩ አይችሉም፡፡ ሁለቱም እሳቤዎ አንድ የሚያደርጋቸው ልክ እነደማንኛውም የፖለቲካ ፓረቲ ስልጣን ፈላጊነታቸው ነው፡፡ ያለው የስልጣን ቁንጮ ቦታ ደግሞ አንድ ቦታ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ሁለቱም ቦታው እኔ እይዝ እኔ እይዝ ወደሚለው የሁለት ዝሆኖች ጠብ መቀየሩ አየቀርም፡፡

የፍፁም አሃዳዊነት እሳቤ የሌላኛው የፌዴራሊስታዊ እሳቤ ህልውና ይሁን የህልውና መሰረቱ የሆነውን ብዝሃነትን ስለሚክድ እና ኢትዮጲያ መመስረት ያለባት በአንድ ህዝብ እሳቤ ነው፡፡ ስለዚህ ደማችን፣ አጥንታችን አንድ ነው ሌላው የውል ሃብታችን የሆነው ቋንቋችን፣ ባህላችን በዚሁ መሰረት የተገነባው ማንነታችን አያስፈልገንም ኢትዮያዊነት ብቻ በቂ ነው ብሎ የሚያምን ከመሆኑም በላይ በታሪክ ይህ አስተሳሰብ አገሪቱን ከመፍረስ አፋፍ ላይ አደርሷት የነበረና አሁን በሌላ ወገን ተቀናቃኝ ሆኖ እየቀረበ ያለው አስተሳሰብ መሰረት ያደረገበትን ፖለቲካዊ እሳቤ የሚንድ ነው፡፡ ስለሆነም እነዚህ ሁለቱ እሳቤዎች የሚፈጥሩት የስልጣን ግብግብ በምንም ተአምር በጉልበት ተፈቶ አገሪቱን በአንድነት ሊጠብቃት አይችልም ይልቁንም ሃገሪቱ ወደማትወጣበት የእርስበርስ ግጭትና ብዙ የኢትዮጲያ ብሄርና ብሄረሰቦች የመገለል ፣ የአድልዎ እዲሁም ከአገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር የመገፋት ብሎም አገሪቱን ወደ መበታተን ሊያደርሳት ይችላል፡፡

እነዚህ ሁለት እሳቤዎ የስልጣን ሽኩቻውን ሲጀምሩት ያገሬ ሰው እንደሚተርተው “በሬ ሆይ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ” እንደሚባለው ተደርጎ የተጀመረ ነው፡፡ አሁን በሚኬድበት መንገድ በተለይ አንዱ አንዱን ለማሰታገስ ብሎ የሚወሰዳቸው የማባበያ እርምጃዎች ቀስ በቀስ ህገመንግስታዊ ስርዓቱን እያፈረሰው ነው፡፡ ከላይ እንደገለፅኩት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የፓርላማውን ይሁንታ ሳይጠብቁ በምክርቤቱ በአሸባሪነት የተፈረጀን ድርጅት የሚመራ መሪ ክስ እንዲነሳ እንደዚሁም በኢትዮጲያ ህገመንግስት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በ ጁላይ 1/1949 እ.ኤ.አ በፈረመችበት በአለምአቀፍ የፀረ ዘር ማጥፋት ስምምነት (convention on the prevention and punishment of the crime of genocide)  አንቀፅ 3 C ሳይቀር የተከለከለን ወንጀል በመጣስ በአንድ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋትን ያወጀ የቴሌቪዥን ተቋም ከተጠያቂነት አንዲድን ክሱ እንዲቋረጥ ማድረጋቸው፡፡

በተለይ አሁን በቅርቡ በአንዳርጋቸው ፅጌ ዙርያ እተደረገ ያለው ፍፁም ኢ-ህገመንግስታዊ እና ህግን የጣሱ ተግባራት በቂ ማሳያዎች ይመስሉኛል፡፡

1/ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ዜግነታቸው እንግሊዛዊ ናቸው፡፡ ስለሆኑም በኢትዮጲያ ፖለቲካ ውስጥ ምንም ዓይነት መብት የላቸውም ኢትዮጲያ የእንግሊዝ መንግስት እገለብጣሁ ብሎ የመነሳት መብት እንደሌለው ሁሉ

2/ አቶ አንዳርጋቸው በምክትልነት ይመሩት የነበረው ድርጅት እስከ አሁኗ ደቃቃ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአሸባሪነት የተፈረጆ ድርጅት ነው፡፡

3/ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ኢትዮጲያ ውስጥ ሊያቆይ የሚችል ተገቢ () ቪዛ የላቸውም፡፡ ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የፓርላማውን ኢሚግሬሽንም ስራ አጠቃለው ራሳቸው ከአሸባሪነት መዝገብ ፋቂ፣ ራሳቸው ቪዛ ፈቃጅ በመሆን በቤተመንግስታቸው ጠርተው አቶ አንዳርጋቸው ማነጋገራቸው አሁን ቁጭ ብለው የሰቀሉት ህግ ጥሰትና ስርዓት አልበኝት በኋላ ቆመው ማስተካከል መቻላቸውን እጠራጠራለሁ፡፡

በግሌ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ተፈተው በቀጥታ ወደ አገራቸው ቢሄዱ አልቃወምም፡፡ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስተሩ ያደረጉት ድርጊት የሌላ አገር ዜጋ ሆነህ የተፈረደብህ አሸባሪም ብትሆን በቤተመንግስት የጀግና አቀባበል ይደረግልሃል ስለዚህ አሸባሪ መሆን ችግር የለውም የሚል መልእክትና ትምህርት ለልጆቼ ስለሚያስተላልፍ አጅጉን ያሳዝነኛል ትውልድ በካይ ተግባር ነውና፡፡

ህግ መጣስ እጅግ ቀላል ነው ህግ ማክበር እጅግ ከባድ ነው፡፡ ምክያቱም ህግ ማክበር እየተገነባ የሚመጣ ባህል ነው፡፡ አንድ ህግ በአስከባሪው ሲጣስ ግን ዜጋው ህግ እንደሚጣስ ነው የሚማረው የሚጣስ ህግ እያየ የሚያድግ ዜጋ አመክንዮ ያጠፋል/ያጣል በመሆኑም ስርዓት መገንባት አይችልም ሁሌም በቁጥቁጥ እንድንኖር ብሎም ወደ ስርዓት አልበኝነት ይወስዳል፡፡

ወደ ተነሳሁበት ለመመለስ የፍፁማዊ ህብረት/አንድት አራማጆችና  የበኛ ቁጥጥር ስር ያለ ፌዲራላዊነት ብቻ እሳቤ አራማጆች ፀብ ከፊት ለፊታችን የተደቀነ አስቀድመን ማሰብ ያለብን አደጋ ነው፡፡

የመፍትሄ ሃሳብ

1/ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በፍጥነት ስርዓቱን እና አገሪቱን ለማዳን ሙሉ ህገመንግስታዊ ስልጣኑን እና መብቱን መጠቀም አለበት

2/ ኢህአዲግ በፍጥነት ወደ አሳታፊ ፖለቲካ መድረክ መግባት አለበት

3/ አሁን እየተደረገ ያለው የስልጣን ሹኩቻ ኢህአዴግ ሊቋቋመው ስለማይችል በግልፅ ርእዮት አለም ልዮነት ኢህአዴግ መሰንጠቅ አለበት፡፡ በተለይም ፌዴራሊስታዊያን እና አሃዳውያን የየራሳቸው ንኡሳነ ኢህአዴግ ፈጥረው በፖለቲካ አማራጭነት መቅረብ ምርጫውን ለህዝብ መተው አለባቸው፡፡

4/ እስካሁን አጋር እየተባለ ከኢህአዴግም ይሁን ከፌዴራል መንግስት መድረኮች ተገለው ያሉ የክልል ፓርቲዎች በሚመርጡት አደረጃጀት አማራጭ ሃሳባቸውን ማንፀባረቅ የሚያስችለው መድረክ መፈጠር አለበት፡፡

5/ የአገር ሽማግሌዎች ፓርላማ ተቋቁሞ የሞራልና የግጭት መፍታት ሃላፊነት ተሰጥቶት አገር ከግጭትና ቅራኔ ከመንግስት ጎን ለጎን መጠበቅ አለበት፡፡

********

Guest Author

more recommended stories